ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝትዎ ብገኝም፤ ነገር ግን ዕድል አግኝቼ ልጠይቅዎት ያልቻልኩትን ጥያቄ ምናልባት ፈጣሪ ፈቅዶ ለጆሮዎ ይደርስ ይሆናል ብዬ ይህን ለመፃፍ ተነሳሳው። ጥያቄዬ የሚያጠነጥነው በአመፅ ተፀንሶ፤ በፍቅር የተወለደው ይህ የለውጥ ጅማሬ እንዴት እናስቀጥል እንችል ይሆናል ከሚል ጭንቀት ውስጥ የወጣ ነው። ሁላችንም በእርስዎ ድንቅ አመራር፥ የፍቅርና ትህትና አካሄድ ተማርከን የዛሬው ደስታችን ላይ አተኩረን በታላቅ ደስታ ላይ ነን። ግን ይህ ምናልባት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብቸኛውና የመጨረሻው ዕድል ሊሆን እንደሚችል እየተገነዘብን ከሚያንዣብበው አደጋ ለማምለጥ ለስህተት አንዳች ፈንታ እንዳይኖር ሁላችንም እርስዎን ጨምሮ ራሳችንን መፈተሽ የዕለት ዕለት ተግባራችን ሊሆን ይገባዋል።
1 Comment
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
"ኢትዮጵያ ትጠየቅ" በሚል ርዕስ የዛሬ ሁለት ዓመት የፃፍኩት ፅሁፍ ከዚህ በታች ይገኛል። ፈጣሪ የሰራውን ተዐምር እያሰብን እናመስግን። ደግሞም ገና በአምላክ ስር ያለን አንድ ቤተሰብ እስኪያረገን ድረስ ማመናችንን አንተውም! የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው?
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ፍቅራቸው የነካው ሽህ ዓመት ንገሱ ሲላቸው፤ ሌላው እንዴት መንግስት ይሸጋገራል ብሎ ሲያወጣና ሲያወርድ፤ ሌላኛው ደግሞ አምባገነን ስርዓት እየመጣ ነው ብሎ ሲቃወም ይታያል። ለማያስተውል ሰው የዶ/ር አብይ መንግስት ወዴት ይሄድ ይሆን ብሎ ግራ ሊገባው ይችላል። ለእርሳቸው በቂ ጊዜ ተልዕኳቸውን በሚመጥን መልኩ እንዲመሩን ዕድል እንስጥ። ይህ የእርሳቸው አመራር የለመድነው ፍሬ አልባ የሽግግር መንግስት ሲባል ያየነው ዓይነት አይደለም። የፅሁፌ ጭብጥ ሀሳብ፤ ይህ የእርሳቸው መንግስት ያልነበረ፥ ወደፊትም ሊኖር የማይችል፤ በዓይነቱ በዓለም የመጀመሪያው የሆነ የአዋላጅ መንግስት ስርዓት እንደሚሆን ላስረዳ እሞክራለሁ። ከዚያ በሁዋላ የሐቅ ምርጫ ዳኛ ይሆንልናል። ዶ/ር አብይ የአንድ መሪ በስልጣን ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከሁለት ምርጫ በላይ መሆን የለበትም ያሉት ያኔ ሕግ ስለሚሆን ሀሳብ አይግባን። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የሚወድዎትና እርስዎም የሚወዱት ዲያስፖራ ጋር ለመገናኘት፤ በመካከል ያለውን ፈተና አምላክ እንድንወጣ ያስችለናል ብዬ አምናለሁ። በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ባለው በኢትዮጵያ ቀን ላይ ተገኝተው ሊያዩን ቢፈልጉም አምላክ ስላልፈቀደ አልተሳካም። ሁላችንም እንደ አንድ ሆነን እርስዎን ለመቀበል እየፈለግን ሳለ፤ ግን ስለ መምጣትዎ በሚደረገው ዝግጅት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ መሰናክል እንዳይኖር ጥንቃቄ እናደርግ ዘንድ ይገባል። የእርስዎ መንገድ የተዋጣለት እንዲሆን ሁላችንም ለክቡርነትዎ ዘብ እንቁም። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የኢትዮጵያ አምላክ ስጦታ የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ የተነሱለት ራዕይ ከእኛ ኢትዮጵያውያን ተርፎ ለአፍሪካም በረከት የሚሆን ጭምር ነው። ፈጣሪ የሕዝብን የዘመናት ልመና ሰምቶ፤ ዛሬ በፍቅር ደስታ ተዐምር በሚያሰኝ ሁኔታ መላውን ሕዝብ አንድ እያደረገ ይገኛል። እኚህ ሰው ዲሞክራሲን አዋልደውና የአፍሪካን አንድ የመሆን ራዕይ ፈንጥቀው ከስልጣናቸው ዞር የሚሉ “ጉደኛና ታሪከኛ” መሪ እንጂ፤ አምላክ የሰጣቸውን የማያልፈው የኢትዮጵያ አባትነት ክብር፥ ለሚያልፈው የስልጣን ጥማት የሚሸጡ አይመስለኝም። ስለዚህ እኚህን የፍቅር ስብዕና የተካኑትን ጠ/ሚ፤ ለሁሉ ፍቱን መድሃኒት የሆነውን ተወዳጅ የመደመር አስተሳሰብ ማደናቀፍ በታሪክ የማይሽር ጠባሳ በራስ ላይ ያመጣል። ይህ ዓይነት ጠባሳ ኢትዮጵያዊ በሆነ ሁሉ ላይ እንዳይመጣ ሁላችንም የቻልነውን ያህል የማሻገር ስራ እንድንሰራ እንነሳሳ። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በቅድሚያ የፍቅር ሐዋርያና የኢትዮጵያ ማንዴላ ለሆኑት ዶ/ር አብይ፤ በሕይወታቸው የተቃጣውን እኩይ ሴራ ስንመለከት፤ ከደጋፊነት አልፈን በፍጥነት ወደ ረዳትነት መሸጋገር ሀገራዊ ግዴታ እንደሆነ መገንዘብ ይገባናል። ለማመንታት ጊዜ የለም። በቃ። በዚህ የመደመር መርሀ ግብር ውስጥ መከናወን ያለባቸው አራት አብየት ጉዳዮች አሉ። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ዶ/ር አብይ አህመድን ምን እንላቸዋለን? ከአሁን በፊት መሪዎቻችንን ለመግለፅ የተጠቀምንባቸውን ቃላት ሁሉ የሚያልፉ ሆኑብኝ። ጉደኛ የሚለውን ቃል የመረጥኩት፥ ያልተለመደና ያልታየ ነገርን ስለሚገልፅ ነው። በሌሎች ስንቀና የኛም ተራ ደርሶ ይሆንን? ደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ነበራት፤ ሕንድ ማህተመ ጋንዲ ነበራት፤ አሜሪካ ጆርጅ ዋሽንግተን ነበራት። ኢትዮጵያ ዶ/ር አብይ ደረሰውላት ይሆን? ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በ 44 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መሪ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ “ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” እያሉ ንግግርዎን ሲያሳርጉ አይቶ ሕዝበ ኢትዮጵያ በደስታ ተሞልቷል። እኔ ግን እያሉ ያሉት ይህ የማሳረጊያ ቃል በሕዝብ ፊት ብቻ ሳይሆን በአምላክ ፊት ምንና ምንን በሃላፊነት ሊያስጠይቅዎ እንደሚችል የነገሩ ክብደት እጅግ አሳስቦኛል። የፈጣሪ ስም ከተነሳ ዘንዳ፥ ይህ ፈጣሪ የሚሰጠን በረከት ምንነት ይታወቅ ዘንድ ያስፈልጋል። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” ሲባል ዝንተ አለም አሳልፈን ዛሬን ደረስን። እስከ ዛሬ “ትዘረጋለች” ከማለት አልፈን “ዘረጋች” ወደማለት ሳንሸጋገር ሦስት ሽህ ዓመታት ጠበቅን። በዚህ ፅሁፌ ይህ 3000 ዓመታት ያስቆጠረው ትንቢት ተፈፀመ የሚያስብለው ሁኔታ ምን እንደሆነና፤ የፈጣሪን በረከት የጠየቁት እርስዎ ስለዚህ በረከት ሊኖርዎት የሚገባውን ግንዛቤ ለመጠቆም እሞክራለሁ። የዚህ ጉዳይ ተጠያቂነት ሁላችንንም የሚመለከት ስለሆነ የኛን ድርሻም ለማመላከት እሞክራለሁ። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሁላችንም ካለንበት አጣብቂኝ ውስጥ መውጫ መንገድ አጥተን ተፋጠን ሰንብተናል። ስንነካከስ እንዳንጠፋፋ በሚያስፈራበት መልኩ ሁላችንም ግብ ግብ ስንገጥም እዚህ ደረስን። መንግስት በጉልበቱ ሲገፋበት፥ ሕዝብ በአመፁ ሲዘልቅበት፥ አማራጭ ኃይል በሁሉ አቀፍ ትግሉ ሲዘምትበት፥ አካሄዱ ሁሉ ሲያስፈራ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ያሰኝ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ ወደ አምላኩ ከመጮህ አልተቆጠበም። በአራቱም አቅጣጫ አንድነቷን እና ብልጽግናዋን በማይወዱ የተከበበች ሀገር ሆና ሳለ፥ ከውስጥ ደግሞ በነውጥ ስትናጥ ተስፋዋ እየመነመነ ጫፍ ደርሶ ነበር። ምን አልባት ታዲያ የማታ ማታ ፈጣሪዋ ኢትዮጵያን ከምጥ ሊገላግላት፣ ውጥረቷን አርግቦ ሰላምን ሊሰጣት አስቦ ይሆን ዶ/ር አብይ እርስዎን ወደ አመራር ያመጣዎት? ካለንበት አጣብቂኝ ለመውጣት ረዥም መንገድ መሄድ እንዳለብን እሙን ነው። ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ ዘብ በመቆምና እኛም ለእርሳቸው ዘብ በመቆም ይህን የተስፋ ጭላንጭል ጠላት እንዳያጨናግፍ ሁላችንም የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል። አሁን ከፊታችን የተደቀነው ወሳኝ ሰዓት እኛ ተመልካች ሆነን፥ ዶ/ር አብይ ደግሞ በፊታቸው ያለውን ፈተና ያልፉ እንደሆነ ለማየትና ብያኔ ለመስጠት በጥርጥር ዓይን የምንመለከታቸው አይደለም። ወይንም እኛ ሁላችን እሳቸውን የምናዋክብበት ጊዜ አይደለም፤ ነገር ግን እኛም ሆንን እሳቸው የመፍትሄው አካል ከመሆን እንዳንጎድል የምንጠነቀቅበት ጊዜ ከምን ጊዜውም በላይ አሁን ነው። ከዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሰሚ ያጣ ሕዝብ ብዬ የፃፍኩት ትዝ ይለኛል። ጆሮ ያለው ይስማ ብዬ የፃፍኩትም የእርስዎን ምርጫ በመመኘት ነበር። ዛሬ ፓርቲዎ ኢሕአዴግ ሕዝብን የመስማት አገልግሎት ለመጀመር እርስዎን በጠ/ሚኒስቴርነት መሾሙ ድንቅ የሚያሰኝ ነው። ከጦረኛ መንግስትነት ወደ አዋላጅ መንግስትነት መሸጋገር የእርስዎ ብቸኛ ትኩረትዎ እንዲሆን ማስተዋል እንዲበዛልዎት እመኛለሁ። አብዮት ከመወለዱ በፊት ኢትዮጵያ እንደገና እንድትወለድና ሁላችንም በእኩልነት የምንኖርበትና በዲሞክራሲ የምንዳኝበት አዲሲቷን ኢትዮጵያ ዕውን በማድረግ መንግስትዎንና ሀገራችንን ከጉድ ለማትረፍ ጥሪዎን እንዲወጡ ፀሎቴ ነው። አዋላጅ መንግስት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ በታች ለማስረዳት እሞክራለሁ። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሕዝብ ተነሳ። ይህ ከወትሮው የተለየ አነሳስ ይመስላል። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ይህ ሕዝብ ተነስቶ ሲያበቃ እድሉን ለልጆቹ በአደራነት ሰጥቶ ሲቀመጥ፥ መሪዎቻችን የስልጣን ርክክብ አካሄደው ሕዝቡን በዜሮ እየሰደዱት ስልችቶታል። ቁጭ ብድግ ማለቱ በቃኝ ያለ ይመስላል። አሁን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መነሳቱ፥ የስልጣን ርክክብ ለማካሄድ ሳይሆን፥ ዳግም እንደገና መነሳት በማያስፈልገው ሁኔታ ስልጣኑን ራሱ ወስዶ ተረጋግቶ ለመቀመጥ ነው። |