By Zelalem Eshete, Ph.D.
In the heated atmosphere of Ethiopian politics, a crucial voice remains largely unheard—the voice of the silent majority. These are ordinary citizens who are not driven by an appetite for political power or ideological battles. Instead, they desire something far more essential: peace, unity, and the sustained well-being of their nation. Yet this majority has no effective platform to express its aspirations. Public discourse is often monopolized by polarized factions, with one side passionately cheering for the government and the other side relentlessly tearing it down. These opposing forces, locked in a tug-of-war, dominate the national narrative. In the process, they drown out the steady, sober voice of those who simply want to see a peaceful and united Ethiopia. This silent majority is not apathetic; they are deliberate. They are teachers, farmers, entrepreneurs, students, and elders—people who understand the cost of conflict and the value of harmony. They are not neutral, but they are measured. Their voice could serve as a moral compass in guiding both the government and the opposition away from destructive extremes and toward the common good. The Role of National Dialogue The upcoming National Dialogue Forum presents a historic opportunity to bridge this gap. For such a platform to fulfill its promise, it must go beyond being a stage for the usual political players. It must actively seek out and amplify the voices of the silent majority. This means creating space for civil society, faith leaders, youth, and local communities to speak—not merely as observers, but as active participants in shaping Ethiopia’s future. If designed and implemented with integrity, the National Dialogue Forum could provide what Ethiopia so desperately needs: a center of gravity rooted not in political ambition, but in civic wisdom. It could become the avenue through which the country’s heart—the everyday people—finally speaks. A Compass for the Nation The silent majority does not claim to have all the answers. But what it does offer is invaluable: a longing for peace that transcends party lines, a hunger for unity that defies ethnic divisions, and a vision for national well-being that includes all Ethiopians. Their voice, if given room to speak, can help recalibrate the direction of national policy and public discourse. They can serve as a compass—guiding Ethiopia not left or right, but forward. Let us not underestimate the quiet ones. In their silence lies a deep wisdom. And in their awakening lies the hope of a nation. By Zelalem Eshete, Ph.D.
The problems facing Ethiopia today are deeply complex. The ongoing conflict, relentless fighting, and widespread suffering feel overwhelming—like centuries of unresolved wounds, political turmoil, and mistrust have all collapsed into a single painful moment. It’s not just a crisis of governance or ideology—it’s a crisis of humanity. Yet, as daunting as the situation is, I do not believe the conflict is unsolvable. The tragedy lies not only in the violence itself, but in the silence where dialogue should have been. Conversations that might have built understanding were never given the chance. Listening has given way to shouting. Empathy has been drowned out by suspicion. Had there been real dialogue—humble, honest, sustained—we might have seen a way forward. Not an easy path. Not a quick fix. But a genuine, gradual journey toward peace. True peace is not born of silence or enforced submission. It emerges through courageous conversation and the willingness to see one another as human. We must pray that God raises voices of wisdom and softens hearts to hear again. The Noise Without Understanding In today’s Ethiopia, much of what passes for dialogue is little more than shouting. We raise our voices not to understand, but to accuse, to defend, to dominate. We do not pause to listen with empathy, nor make the effort to step into another’s shoes. And because we do not listen, we label. Labeling dehumanizes. Once someone is seen as “the enemy,” it becomes easier to justify harm. War becomes palatable. Killing turns into a twisted act of virtue. And the casualties—real people with families, dreams, and dignity—become mere statistics. But every number has a name. Every death is a story cut short. Every casualty is a soul. This is the cost of losing our ability to listen with love. We are bleeding because we have forgotten how to hear. And only a spirit of humility can break this cycle. Only a renewed vision of shared humanity can rescue us from dehumanization. We need peacemakers—not those who speak to be heard, but those who speak to understand. The Divine Call to Peacemaking Why should we bother advocating for dialogue when hope feels out of reach? Because to be a peacemaker is divine. Jesus said, “Blessed are the peacemakers, for they shall be called children of God” (Matthew 5:9). Peacemaking is not just a noble ideal—it is a sacred calling. It reflects the very heart of God. When we pursue peace, we step into our true identity as His children. At our lowest point—when human solutions fail and despair creeps in—God does not call us to escape, nor to resign in silence. He calls us to make peace. Not because it’s easy. Not because it guarantees results. But because it is right. Because it’s what children of God do. To be a peacemaker is to carry the heart of heaven into the brokenness of earth. Listening to the Voice of Blood So, what is our goal? At its most basic, it is to recover the lost art of listening. But not just listening to the loudest voices—the leaders, the ideologues, the power brokers. No. We must listen to the voice of blood. We must hear the silent cry of the fallen soldier on one side, and the fallen peasant on the other. The ones who bleed and die while those in power remain untouched. It is their blood that cries from the ground—and it is their voice we must heed. This is where our unity must begin: not with political alignment, but with shared compassion. We must stop dividing ourselves along the fault lines of leadership and ideology. Those who perish on either side are our brothers and sisters. They are not the enemy. They are family. We share a deeper bond than politics—we are united by our common humanity. A Way Forward Solutions demand dialogue. Dialogue requires conversation. And conversation begins when the blood stops crying out from the ground. This means we must seek a ceasefire—not just of weapons, but of hearts hardened by hatred. We must make space for listening. For compassion. For reconciliation. May God awaken a spirit of humility across this land. May He raise up peacemakers who speak less to win and more to heal. And may He grant Ethiopia not only political resolution—but moral restoration. Because the future of a nation does not rest in the hands of the loudest voices, but in the hearts willing to listen and the courage to choose peace. ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ግልፅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ሕዝበ ቤተሰብ። በደወል 1 ዘ ኢትዮጵያ በሚድን በሽታ ተይዛ ግን በሽታው እየገደላት ያለች ሀገር ኢትዮጵያን አየን። በደወል 2 ዘ ኢትዮጵያ፥ ለዚህ በሽታ ያልተጠቀምንበትን ቀዳሚው ፍቱን መድኃኒት ምን እንደሆነ ተመለከትን። አሁን በደወል 3 ዘ ኢትዮጵያ መድኃኒት መስሎን የምንወስደው ዘረኝነት ገዳይ መርዝ እንደሆነ እናያለን። ሰው የሚድን በሽታውን ለማሻል የሚያድን መድኃኒት ይወስዳል እንጂ ጭራሽ ለሞት የሚያጋልጠውን መርዝ በመድኃኒት ስም አይወስድም። ኢትዮጵያ ግን የብሔር ብሔረሰብን እኩልነት ለማምጣት ዘረኝነትን እንደ መድኃኒት እየወሰደች የማያቆም የስቃይ ድራማና ምስቅልቅል ያለ ጉዞ ተያያዝን። የኢትዮጵያ ሕልውናም ቦግ ድርግም እያለ፥ በቁልቁለት ጉዞ ፀሐይ እስክትጠልቅባት ድረስ የሚሄደው ለዚህ ነው። መፍትሄው አንድ ነገር ነው። የዐሳብ ልዕልና መውጫ መንገዳችን ነው። የዐሳብ ልዕልና ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፥ ሲያሸንፍ ዘለቄታ ያለው መፍትሄ ጭምር ሰጥቶ ነው። ለመግባባት አንድ መሠረት መኖሩ ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በብዝሀነት የበለፀገች ናት። የሁሉም ውበት ደምቆ እንዲወጣ፥ የሁሉም ስብዕና እና እሴቶች በሙሉ በእኩልነት እንዲታዩ፥ ከዚህ አልፎ ልዩነቶቹ እርስ በርስ እየተመጋገቡ እንዲጎለብቱና በዘለቄታ እንዲዘልቁ ከተፈለገ፥ ሁላችንም አንድ መሠረት ሊኖረን ያስፈልጋል። ያም መሠረት አብሮነት ይባላል። ግን ዘረኝነት አብሮነታችንን እየገዘገዘ ብትንትናችን እንዲወጣ መንገድ ይጠርጋል። ያኔ ባለጊዜና ያሸነፈ የሚመስለው ተረኛ፥ ራሱን መሠረት ለማድረግ ይሞክራል። በዚህ ሂደት ሁሉም ይከስራል። ይህ እንዳይሆን ያልታሰበውን ማሰብ መጀመር አለብን። ያልታሰበውን ማስብ፦ የዐሳብ ልዕልና ያልታሰበውን ለማሰብና የዐሳብ ልዕልናን ለመጨበጥ፥ እኛ ራሳችንን የምናይበትን ዕይታና ሌሎችን የምናይበትን ዕይታ መቀየር አለብን። ምክንያቱም በተለመደው ዕይታ ዘረኛው ሁልጊዜ ሌላኛው ነው እንጂ እኛ አይደለንም። ለአብሮነት መሠረት ደግሞ እንቅፋት የሆነው ዘረኝነት ነው። ቋንቋችን የሚደባለቀው እዚህ ላይ ነው። አንዱ ከሳሽ፥ ሌላኛው ተከሳሽ እየሆንን ስለ ቁምነገር መነጋገር አንችልም። ነፃ የሚያወጣን ሁላችንም ወርደን ታች ዝቅ ብለን እግዚአብሔር እኛን የሚያይበትን ዕይታ ማየት ነው። ያኔ ሁላችንም ዘረኛ እንደሆንን ይታየናል። ዘረኝነት በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው። ከዘረኝነት የምንወጣው በፍቃዳችን ነው። ያንንም በአሸናፊነት የምንወጣው፥ ሁላችንም አብረን ዘረኞች እንደሆንን ሁሉ፥ ሁላችንም ከዚያ ተላቀን ሰው መሆንን ስንፈቅድ ነው። አንዱ በብሔሩ ዘረኛ ሲሆን፥ ሌላኛው በዜግነቱ ዘረኛ ይሆናል። አንዱ ብሔሩን ሲያስቀድም፥ ሌላኛው ዜግነቱን ያስቀድማል። አንዱ የብሔር ዘረኛ የራሱን ብሔር ለብቻው ሊያገን ሲፈልግ፥ ለኢትዮጵያ አብሮነት መሠረት ውጋት ይሆናል። እንደዚሁም የዜግነት ዘረኛ ኢትዮጵያን ለብቻዋ እንድትገን ሲፈልግ፥ በጨለማ ላለ ጥቁር አፍሪካ ሕዝብ አንድነት ውጋት ይሆናል። አንድ ብሔር እንዲሰለጥን የሚፈልግ ዘረኛና፥ አንድ ኢትዮጵያን ለማግነን የሚፈልግ ዘረኛ፥ አንድ አፍሪካን ሕልም አድርጎ የሚያስቀር ነው። ይህን በማድረግ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን፥ ዓለምን ያጨልማል። በኢትዮጵያ ዘረኝነት እንደ መድኃኒት መወሰድ የተጀመረው በጭቆና ተሳቦ ነው። ጨቋኝ ሁልጊዜ ሕዝብ ሳይሆን የተረኛ መንግስት ውጤት ነው። የጨቋኝ እናት ደግሞ በጥቁር ሕዝብ ላይ የተፈፀመው ጭቆና ነው። ኢትዮጵያ በአድዋ የነፃነት ምልክት የሆነችውና ለፓን አፍሪካ መነሻ ያደረጋት፥ እንድትመፃደቅበት ሳይሆን፥ ለእውነተኛው ጭቆና መልስ እንድትሰጥ ነው። ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦችን ጭቆና ለመፍታት እስካልተነሳች ድረስ፥ ራሷን በራሷ ተጠላልፋ የብዙዎች እንቆቅልሽ መሆን ይሆናል እድል ፈንታዋ። ያለን ዘረኝነት የብሔር ዘረኝነት እና የዜግነት ዘረኝነት ነው። እዚህ ላይ መሀል ሰፋሪ የለም። መሀል ነኝ ብሎ የብሔር ዘረኝነትን ጠባብ የሚልና የዜግነት ዘረኝነትን አሕዳዊ የሚል ፖለቲካዊ ብልጣብልጥነት ነው። አሁን ሁላችንም ብንፋቅ ወይ የብሔር ዘረኛ ነን፤ አለበለዚያ ደግሞ የዜግነት ዘረኛ ነን። እውነተኛይቷ ኢትዮጵያ የምትገለጠው ልጆቿ የተፈጥሮ ዘረኝነትን በፍቃዳቸው ለመላቀቅ የሚያስችላቸውን ሃይል እንዲላበሱ የኢትዮጵያን ተልዕኮ ሲያውቁ ነው። በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ልጆች ከዘረኝነት ወጥተን ሰው በመሆናችን፥ ለጥቁር ሕዝብ ጭቆና መልስ መሆን ተልዕኳችን መሆኑን እንወቅ። ችግራችን የሚፈታው ከራሳችን በላይ ማሰብ ስንጀምር ነው። በዓለም እስካሁን ካልታዩት የተሻለ ሥርዓት ሊያመጡ የሚችሉ አቅም ያላቸው ልጆች እናታችን ኢትዮጵያ አላት። ከዘረኝነት የምንወጣው በፍቃዳችን እንጂ በተፈጥሯችን አይደለም። የራስን ባህል ቋንቋ እሴት ማዳበር ሰውዋዊነትና ኢትዮጵያዊነት ነው። ነገር ግን የብሔር ዘረኝነት ራስን መንከባከብ ላይ ብቻ አያቆምም። ራስን በሌላው ላይ ጭኖ መግነን ነው የሚፈልገው። ጨቋኝነት ከባለጉልበታምነት (ተረኛ ባለጊዜነት) የሚመነጭ ነው። ራስን በትዕቢት ከሁሉ የበላይ ነኝ የሚል መንፈስ የእኩልነት ጠላት ነው። የብሔር ዘረኝነት የብሔርን ክብር የሚያዋርድ ነው። ብሔር ክብሩና ውበቱ የሚገለጠው በእውነተኛ ኢትዮጵያዊ አብሮነት ውስጥ ነው። የአድዋ ታሪካችን ፈጣሪ ለጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ እንድንሆን ዕድል የሰጠን መሆኑን የሚያሳይ ነው። ለራስ ብቻ ከመኖር ለሌሎች ለመኖር እንድንፈልግ ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ እንጀራ እንዲወጣላት ከፈለግን ማወቅ ያለብን ነገር አለ። ያም ለአፍሪካ እንጀራ እንዲወጣላት ኢትዮጵያ እርሾ እንደሆነች ነው። ኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ትልቅ ካልሆነች፥ በእኛው ልክ ብቻ ከሰፋናት፥ እሺ ብላ አትሰፋልንም። ይልቁንም ትበጣጠስብናለች። ሰው መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ሰው ሰውን ገዥና ለሰው ተገዥ ሆኖ እንዲኖር በፈጣሪ አልተፈጠረም። ሰው ተፈጥሮን እንዲገዛ እንጂ። ሰው ግን ተባብሮና ተዋዶ ምድርን እየገዛ የምድርን በረከት ከመብላት ይልቅ፥ አንዱ ሌላውን ለመግዛት እየሮጠ እርስ በርስ መበላላትን መረጠ። ሰው መሆን ሲመነዘር በዜግነት የሚወሰን ሳይሆን በአህጉራችን ጥቁር ሕዝብነት ነው የሚታየው። ያኔ ነጭ ጥቁር ሳንል ለሰው ፍጡር ሁሉ ፈውስ ምክንያት እንሆናለን። አፍሪካ ስትድን ያኔ ሁላችንም እንድናለን። ይህንን መንገድ ካልመረጥን ግን በተናጥል እያንዳንዳችን በጠላት እንመታለን። አብረን ካልቆምን ለየብቻችን የዓለምን ተፅዕኖ አሸንፈን ከጨለማ አህጉርነት ወደ ብርሃን አህጉርነት አንሻገርም። ኢትዮጵያ ደግሞ ለዚህ በመሪነት እንድትቀደም በታሪክ አጋጣሚ ይሁን በፈጣሪ ፍቃድ ብቻ እሙን ነው። ዘረኝነት ራሱን አንደኛ ያደርጋል። የአብሮነት ድምፅ አልባ አጥፊ ነው። ዘረኝነት በመጨረሻ ሄዶ ሄዶ ከራሱ ጋር ይጣላል። ዛሬ ብሔሩን አስቀድሞ ከሌላው ብሔር ጋር የሚጋጭ፥ ትንሽ ቆይቶ ወደ ጎሳው ዝቅ ብሎ በብሔሩ ካሉት ከሌሎች ጎሣዎች ጋር ይጋጫል። ከዚያ እየወረደ ወደ ቤተሰብ ወርዶ ከቤተሰቡ ጋር ይጋጫል። በመጨረሻ ከራሱ ጋር ይጣላል። የዘረኝነት ሩጫ ወደ ውስጥ ነውና ሄዶ ሄዶ ከራሱ ጋር ይላተማል። የነገሩ ፍፃሜ ምንድነው? ምርጫችን የትኛው ነው? ለዘመናት “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ስንባል ቆየን። ይህ አጠራር የዜግነት ዘረኝነታችንን ያሳብቃል። ዘመን አመጣሹ “ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች” ብሎ ይጠራን ጀመር። ይህ አጠራር የብሔር ዘረኝነታችንን ያሳብቃል። ያልታሰበው ዐሳብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ቤተሰብ” ሊለን ይፈልጋል። ክፋቱ ፖለቲካችን ለራሱ ፍላጎት የሚጠቅመውን እንዲጭንብን ያደርጋል እንጂ ለሕዝብ የሚጠቅመውን አያደርግም። ኢትዮጵያ ራሳችን እንደሆንን በዚያ ማንነታችን እንታወቅ ዘንድ አልቻልንም (Ethiopia: To Be Known As We Truly Are)። ዘረኝነት ካመጣብን ከዚህ የማንነት ጭንብል ማን ይገላግለናል? “እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው” (መዝሙረ ዳዊት 62፡11)። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በደወል 1 ዘኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ በሚድን በሽታ ተይዛ ግን በሽታው እየገደላት እንደሆነ ተመለከትን። አሁን ደግሞ ይህንን በሽታ ተመልክተን እንነቃበት ዘንድ ደወል 2 ዘኢትዮጵያን እንመለከታለን። በሽታውን ስናውቅ መድኃኒቱ ይታየናል። ይህንን ለማድረግ በኢትዮጵያ ያሉትን ሦስት ገፀ ባህሪያት ለምሳሌነት እንውሰድ። አንደኛ የኢትዮጵያ ሕዝብን ተጠያቂ የሚያደርግ ሰሚ ያጣ ፈጣሪ አለ። ሁለተኛ የኢትዮጵያ ልሂቃንን ተጠያቂ የሚያደርግ ሰሚ ያጣ ሕዝብ አለ። ሦስተኛ ብዙ ሰሚዎችን ያገኙ የጠብ ገበሬዎች አሉ። ሰሚ ያጣ ፈጣሪ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠየቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኑሮ ጋር እየታገለ ቀን ያልፍልኛል በማለት ተስፋ የሚያደርግና ተስፋ ባለመቁረጥ የሚታወቅ ነው። ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው፥ ሰውን በሰውነቱ በማየት ከተለያዩ ብሔር ተወላጆች ጋር በጋብቻ የተገመደ ነው። አስቸጋሪ የሆነውን ኑሮ በአብሮነት እየተረዳዳና እየተደጋገፈ፥ ሃይማኖትና ዘር ሳይለየው ለዘመናት በፍቅር የኖረ ነው። ተረኛ ባለስልጣናት እየነገሱ ቢፈራረቁበትም፥ ሕዝብ ሁሉም ያለ ልዩነት የመከራን ገፈት እየተጋፈጠና ለሀገሩ ደሙን እያፈሰሰ ኢትዮጵያን እስካሁን ያቆየ ነው። ሲቸግረው አመፅ አድርጎ መንግስት ቢቀየር፥ ቤተመንግስት አይገባ ነገር፥ ወደ ቤቱ አደራ ሰጥቶ ይመለሳል። ይሁን እንጂ ባለ አደራው መንግስት አደራውን ቀርጥፎ እየበላ ሕዝብን ባዶ እጁን ያስቀረዋል። ይህም ሳያንስ መንግስት ሕዝብን ምረጥ እያለ ያታልለዋል። ሕዝብ ስልጣን ተሰጠኝ ብሎ ቢመርጥም፥ ወይ ምርጫው ይሰረቃል፥ አለበለዚያም በሐቅም ተመረጠ ቢባል እንኳ አደራው ይበላል። ኢትዮጵያ በመልካም ሕዝብ፥ በለምለም ምድር፥ በውብ የአየር ፀባይ ብትታደልም፥ እጣ ፈንታዋ ድህነት ሰቆቃና ሞት ሆነ። ሕዝብ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ፥ ሀገሩ እስር ቤት ሆኖበት፥ የቻለው ለመኮብለል ይናፍቃል። እንባውን ለፈጣሪ እያፈሰሰ ለዘመናት ኖረ። በሌላ በኩል ሰማይ ጥሪ ያቀርብልናል። ፈጣሪ እኛን እንዲሰማን እንደምንፈልግ ሁሉ፥ ፈጣሪም እርሱን እንድንሰማው ይፈልጋል። የሕዝብ ሀብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን የሚዘረፈው፥ የተስፋ ቃሉ እንኳን ሳይቀር በባለተረኞች ይሰረቃል። ኢትዮጵያን በከፍታ ስፍራ የሚያስቀምጣት ፈጣሪ ራሱ ነው። ግን በኢትዮጵያና በፈጣሪ መካከል እየገባ ቦታውን የሚወስድ ባለጊዜ ባለስልጣን ነው። ያንን ደግሞ ሳያውቅ የሚያደርገው ሕዝብ ራሱ ነው። የቀድሞ መሪን የይሁዳ አንበሳ ብለን ማስተጋባት ስናበቃ፥ የአሁኑን መሪ ደግሞ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ሙሴ ብለን አረፍን። የእስራኤልን ዓላማ ኢትዮጵያ መኮረጅ አትችልም። የእስራኤል ሕዝብ ጥሪ በአንድ ሰው ያውም በአብርሃም ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም ያዕቆብ እስራኤል በመሆን የቃል ኪዳኑን ሕዝብ መሰረተ። ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች [1] ማለት፥ ጥሪው የቀረበው ለሕዝብ እንደሆነ ያሳያል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጥሪ በሕዝብ ላይ የተመሰረተና ከእርሱ ጋርም የተያያዘ ነው። ለኢትዮጵያ ሙሴ ትላንት አልነበረም፥ ዛሬም የለም፥ ወደፊትም አይመጣም። ፈጣሪ ኢትዮጵያን በግለሰብ እጅ ሳይሆን በሕዝብ እጅ ያሻግራታል። ለዚያ ጥሪው የቀረበለት ደግሞ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያን የሚያሻግር የሰው ሙሴ እንደሌለ ሁሉ፥ ኢትዮጵያን የሚበታትን የሰው ሰይጣንም የለም። ለደጉም ለክፉም ግለሰብ ላይ መንጠልጠላችን ይቅር። ይልቁንስ የኢትዮጵያ ሕዝበ ቤተሰብ መለኮታዊ ጥሪውን ለመቀበል ይነሣ። ያኔ ፈጣሪም ይነሣል። ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይናገራል፦ “ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ” [2]። ሰሚ ያጣ ሕዝብ፦ የኢትዮጵያ ልሂቃን ይጠየቁ የኢትዮጵያ ልሂቃን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ የወጡና እሴቱን የሚያንፀባርቁ ናቸው። ራሳቸውን መስዋዕት በማድረግ ይህ ሕዝብ ያልፍለት ዘንድ እንደ ሻማ እያለቁ የሚያበሩ ናቸው። በጥበብና በዕውቀት የተካኑ ትልቅ ሰዎች ናቸው። ያም ቢሆን እስካሁን አልተሳካላቸውም። ብርሃኑ እንዳያበራ ንፋሱ ሻማውን ያጨልመዋልና። ሁሉ ከንቱ ሆኖባቸዋል። ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ትርፍ ለሌለው ነገር ማንከራተት ሆኖባቸዋል። ምንም ያህል ሐቀኛና ታታሪ ቢሆኑ የሚያመክናቸው ነገር መኖሩ ነው። ልፋት ብቻ። ሁሉ ነገር የአንድ ሰሞን ጉዳይ ሆነ። ብርታታቸው ራሳቸውን መስዋዕት ማድረጋቸው ነው። ድክመታቸው ደግሞ የራሳቸውን ግላዊ ራዕይ መሰዋት አለመቻላቸው ነው። ሰው ብዙ ዋጋ እየከፈለ ግን መነሻ አሳቡ ስህተት ከሆነ ኢላማውን አይመታም። ሰው ሊሞት ይችላል። ብዙ መከራ ሊቀበል ይችላል። ያም ሆኖ የግልን ራዕይ ጥሎ፥ በአንድነት ለኢትዮጵያ ባለመነሳቱ ብኩን ሆኖ ሊቀር ይችላል። ዋናው ቁምነገር ከጀርባው የሚገፋው ሃይል ከእኔነት መፅዳቱ ነው። በእኔነት ከተነዳን አንድ ሆነን መቆም አንችልም። አንድነት እንዲመጣ ራስን ክዶ፥ ከሌላው ጋር በትሁት ልብ ሆኖ፥ ለሕዝብ ጥቅም ሙሉ በሙሉ መሰጠት አለብን። ፍሬያማ የመሆን ምስጢር ያለው ለእኔነት ሞቶ፥ ከሌላው ጋር በአንድ ልብ መያያዝ መቻል ነው። በልብ እልከኝነት ያለ ፍሬ እንዴት ዕድሜያችንን እንጨርሳለን? አንቆ የያዘን ከእኛ ውጭ ያለው ሳይሆን፥ በእኛ ውስጥ የተደበቀው እኔነታችን ነው። አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸው የተለያየ መሆኑ ችግር አይደለም። ይህ የአሳብ ልዩነት ፀጋ ነው። ግን የዚህ የአሳብ ብዝሃነት ፀጋ የሚገለጠው መነጋገር ሲኖር ነው። መነጋገር ደግሞ ወደ መግባባት አምጥቶ ራሳቸውን የሰውለትን ለውጥ ማምጣት ያስችላል። ደግሞ መግባባት ችግር አይሆንም ነበር። ምክንያቱም በልባቸው ያለው ራዕይ ለሕዝብ ስለሆነ፥ ያ የጋራ ጥቅም ለማግባባት አቅም አለው። ውይይት ቢኖር ልዩነቱ ተጋጭቶና ተፋጭቶ መድኃኒት ይወጣው ነበር። አሁን የተያዘው መጮህ ነው። እንደ ገደል ማሚቶ። ጩኸቱን ሌላው አይሰማም። የሚጮህ ራሱ የራሱን ጩኸት ይሰማል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ታሪክ የሚቀየርበት ጊዜ አለ። ያም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጣሪን ሰምቶ ለተሰጠው መለኮታዊ ጥሪ ራሱን መልስ አድርጎ ሲቆም፥ ልሂቃንም እንደዚሁ ሕዝብን ሰምተው በአንድ ልብ ለመገለጥ ግድ ይላቸዋል። ብዙ ሰሚዎችን ያገኙ የጠብ ገበሬዎች ፈጣሪና ሕዝብ ባልተሰማበት ሁኔታ እነዚህ ግን ብዙ ሰሚዎችን አገኙ። እነዚህ ሰርጎገብ ናቸው። የኢትዮጵያ አይደሉም። የግላቸው ናቸው። ሁሉም ውስጥ ተደብቀው ሀገር እንዲታመስ ምክንያት የሚሆኑ ናቸው። የትም ከለላ ውስጥ ቢሆኑ የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር ነው። ያም ለግል ጥቅም የሚኖሩ ናቸው። ፖለቲከኛ ሽፋን ውስጥ ሲገኙ ራሳቸውን ለማኖር እንጂ ለሕዝብ ሊኖሩ አይደለም። ሃይማኖት ውስጥ ሲሸሸጉ ለፈጣሪ ክብር ሊያመጡ ሳይሆን ለራሳቸው ክብር ለማምጣት ነው። ሕዝብ ውስጥ ሲደበቁ ለሕዝብ ተቆርቁረው ሳይሆን፥ ብሔራቸውን መነገጃ ለማድረግ ነው። እነዚህ ኢትዮጵያን ለማቃጠል እሳት የሚጭሩ ክብሪት የሆኑ ናቸው። ሥራቸው የጠብ ግብርና ነው። የሚዘሩት ዘር ደግሞ ጠብ ይባላል። ቃሉ ስለነዚህ እንዲህ ይላል፡ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ” [3]። ፈጣሪ ከሃጢያት ሁሉ ይበልጥ ነፍሱ አጥብቃ የምትፀየፈው በወንድማማች መካከል ጠብ የሚዘራ መሆኑን ልብ እንበል። በወንድማማች መካከል የሚዘሩት ጠብ የሚያበቅለው ሁለት አይነት ፍሬ ይታጨዳል። በአንድ በኩል ሕዝብ አለመደማመጥና አለመግባባትን እያጨደ እርስ በርስ ይበላላል። በሌላ በኩል በሕዝብ ሰቆቃ ላይ የጠብ ገበሬዎች ሀብት ዝናና ስልጣን እያጨዱ ለራሳቸው ጥቅም ትርፋቸውን ይበላሉ። የነገሩ ፍፃሜ ምንድነው? ሲጀመር የሚሰማ ጆሮ ይኑረን። መሰማት ያለበትን አስቀድመን እንስማ። የሕዝብ ጆሮ ሰሚ ያጣውን ፈጣሪ ለመስማት ይከፈት። የልሂቃን ጆሮ ሰሚ ያጣውን ሕዝብ ለመስማት ይከፈት። ያንን ከሰማን ወደ እርስ በርስ መደማመጥ እንመጣለን። ስንደማመጥ ደግሞ ወደ መግባባት እንደርሳለን። ስንግባባ አብረን እንደ አንድ ሆነን እንቆማለን። አንድ ላይ አንድ ሆነን ስንቆም፥ ያኔ ከመድኃኒታችን ጋር እንገናኛለን። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። በተከታታይ መመልከታችንን እንቀጥላለን። በደወል 3 ዘኢትዮጵያ እንገናኝ። ተጠቃሽ፦ [1] መዝሙረ ዳዊት 68፡31 | [2] መዝሙረ ዳዊት 12፡5 | [3] መጽሐፈ ምሳሌ 6:16-19 ዶ/ር ዘላለም እሸቴ ይቅርታ፥ እርቅ፥ ምክክር፥ መግባባት። የማንለው የለም። ግን የሚደረግ ነገር የለም። ለምን? አንድ ነገር ለማድረግ ቀርቶ፥ ለመነጋገርም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነን። ማስረጃ ቢባል በሦስት ረድፍ ላስረዳ። አንደኛ ንግግር መጀመር አይቻልም። ሁለተኛ ንግግር ቢጀመር እንኳን መቀጠል አይቻልም። ሦስተኛ ንግግር መቀጠል እንኳን ቢቻል፥ መጨረስ አይቻልም። በዚህ ዓይነት የመፍትኤ ሀሳብ እንዳይወለድ (እንዳይሰማ) በሦስት ደረጃዎች መላን የሚያጨናግፍ ብዙ ጩኸቶች አሉ። 1ኛ/ ንግግር እንዳይጀመር ፈንጂ ተጠመደ
የተቀበረ ፈንጂ ስለማይታይ ሰላም ነው ብሎ በመሬት ላይ የሚራመድ ሰው ሁሉ ላይ አደጋ ያደርስበታል። ዛሬ ላይ የፈውስ ሀሳብን ማንሳት እጅግ የሚያስቸግርበት ሁኔታ እየሆነ ነው። የተናጋሪው ስም እንደ ታፔላ (ፈንጂ) ይሆናል። የሰው አስተሳሰቡ በራሱ እንዳይመዘን በማድረግ፥ የተናጋሪውን አስተሳሰብ እንዲመክን ይደረጋል። አንዱ የሚናገረው ነገር ጆሮ ለመክፈት እንዳይችል ፈንጅ እንቅፋት ነው። ገና ከመነሻው ሥር እንዳይዝ የሀሳብ ፍሰት ማጥለያ (filter) ይደነቀርበታል። ደግሞ የተወሰኑ ኮድ ቃላቶች እንደ ፈንጂ ያገለግላሉ። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተናጋሪው ሀሳቡን ሊያብራራ ይቅርና የሀሳቡን ርዕስ እንኳን ለመግለፅ እንዳይችል ያደርጋሉ። አንዳንዶቻችን ከነገሩ ጦም እደሩ ብለን በግል ሕይወታችን ላይ ብቻ እንድናተኩር ተገደናል። 2ኛ/ ንግግር እንዳይቀጥል ቋንቋ ተደበላለቀ በባቢሎን ከተማ ሰዎች ሰማይ የሚደርስ ሐውልት ሊሰሩ ተነሱ። ፈጣሪ ከዓላማው ጋር የሚሄድ ራዕይ ስላልሆነ ቋንቋቸውን ደባለቀ። አንድ ልብ ሆነው እንዳይሰሩ፥ ቋንቋ ተደበላልቆ መግባባት እንዳይችሉ አደረጋቸው። ከዚያ ሁሉን ትተው በዓለም ዙሪያ ተበተኑ። ይህ ታሪክ በእኛ ተደገመ፥ በፈጣሪ ሳይሆን በክፉው። ኢትዮጵያ በአብሮነት እንድንትገነባ በጎ ፍቃደኝነት እና ቅን ልቦና በኢትዮጵያ ልጆች ላይ አለ። ሁሉም የሀገሩ ነገር እንቅልፍ አሳጥቶት የሚታትርና የሚጥር እንደሆነ ይታወቃል። ግን ሁሉም የሚያውቀው ብዙ ዘርቶ ትንሽ ማጨዱን፥ ብዙ እየለፋ የሚታፈስ ነገር ግን ማጣቱን ነው። ኢትዮጵያን ለማዳን ላይ ታች በማለት በተስፋ ብንጠመድም፥ ትርፍ ሳይሆን ከዕለት ዕለት ኪሳራ ሆነብን። በዚህ ውስጥ አንዱ ንግግር መጀመር ከቻለ፥ የሚቀጥለው ፈተናው ደግሞ ንግግሩን መቀጠል ነው። ምክንያቱም ቋንቋ ስለተደበላለቀ ንግግሩን ያቆመዋል። አማርኛ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን ቋንቋችን ይደበላለቃል። አፋን ኦሮሞ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን ቋንቋችን ይደበላለቃል። ሌላውም እንደዚሁ። ቃላቶች ትርጉማቸውን ከደበላለቁብን፥ እንደ ባቢሎን ዘመን አልሆንምን? 3ኛ/ ንግግር እንዳይጨረስ በሰበር ዜና ፋታ ጠፋ የቁም ነገር ንግግርና ሚዛን የሚደፋ ሀሳብ የሚሰማ ጆሮ ብቻ ሳይሆን የሚያስተውል አዕምሮ ይፈልጋል። ለማስተዋል ሰከን ብሎ ማዳመጥና አውጥቶ አውርዶ ውሳኔ ለመወሰን ጊዜ መውሰድን ይጠይቃል። ታዲይ ሰብር ዜና ለዚህ ፋታ አይሰጥም። ከአንዱ ሰበር ዜና ወደ ሌላኛው እየተቀባበለ ለማሰብ ፋታ እንዳይኖረን ያደርጋል። እንደ ጉም በየጊዜው እየተነነ በማይጨበጥ ነገር እያደናገረን ጊዜያችንን ብቻ ሳይሆን እኛን ራሳችንን እየመዘመዘ ይበላናል። ሁልጊዜ እሳት ላይ እንደተጣድን ነው። እፎይታ የለም፥ ለማሰብ ፋታ የለም። ሰብር ዜና እኛን የሚሰባብር ዜና ቢባል ጥሩ ነበር። የነገሩ ፍፃሜ ምንድነው? የሁሉንም ጆሮ ቀልብ ይዞ አንድን አሳብ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ማድረስ ካልተቻለ፥ እየተነጋገርን አይደለም ማለት ነው። እስካልተነጋገርን ድረስ ደግሞ መግባባት ፈፅሞ አንችልም ማለት ነው። ካልተግባባን ደግሞ የሚድን በሽታችንን ማከም ስለማንችል፥ በሽታችን የምንኖር እስኪመስለን እያታለለን፥ ወደ ሞት ይወስደናል ማለት ነው። ታዲያ ምን ይሻላል? በተከታታይ እንመለከታለን፥ በደወል 2 ዘኢትዮጵያ እንገናኝ። |
ጤና ይስጥልኝ!ዶ/ር ዘላለም እሸቴ Archives
April 2025
Categories |