ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሁላችንም የኢትዮጵያ ችግር እንዴት እንደሚፈታ ጭንቀት ይዞን ሀሳብ ለማመንጨት በሀገራችን ጉዳይ ተጠምደን ለሌላ ነገር ጊዜ አጥተናል። ብርቅዬ ምሁራን የኢትዮጵያ እንቆቅልሽ እንዴት እንደሚፈታ የመፍትሄ አሳብ እንደ ዝናብ ዘወትር ያሽጎደጉዳሉ። ያልተፃፈ የለም። ያልተባለ የለም። የኢትዮጵያ ልጆች ችግር ሲፈጥሩ እንዳይፈታ አርገው መቋጠር ይችላሉ። ያንኑ ያህል ደግሞ ውሉ የጠፋበትን እንቆቅልሽ ለመፍታት ብቃትና ብልሃት ያላቸው ብዙ ልጆች ኢትዮጵያ አሏት። በኢትዮጵያ ልጆች እጅ ያለ መፍትኤ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም ይተርፋል። ኢትዮጵያ እንዲህ ጥበብና መላን በማፍለቅ የበለፀጉ ልጆች ከቁጥር በላይ ቢኖራትም ያልታወቀላት ሀገር ናት። ይህ ብቻ ሳይሆን እውቀትና ጥበብ ሳይጎድለን እንደ ጎደለን ራሳችንን ቆጥረን፥ ሌላ መፍትሄ ሀሳብ ለማፍለቅ ከመፍጨርጨር ላንዴም ዕረፍት መውሰድ አልቻልንም። መፍትሄ እንዳናገኝ የያዘን በሽታችን ነው እንጂ፥ ጉዳዩ የጥበብ ማጣት ወይም ከእውቀት መጉደል አይደለም። በበሽታ ተይዛ የተኛችው ኢትዮጵያ ከበሽታዋ የምትፈወስበትን መድሃኒት ምርጫችን ከማድረግ ይልቅ፥ ከአልጋዋ ገና ተነስታ ወደፊት ስለምትሰራው ሥራ ዕቅድ በማውጣት ተጠምደናል። እግዚኦ! ያሰኛል። ታመናል። ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ታመናል። ፈውስ የሌለው በሚመስል በሽታ ታመናል። በሽታው ሳያንስ አሁን አሁን ደግሞ የቃላት ውጊያና ጫጫታ ጨምረንበታል። የድል አጥቢያ አርበኛው ሠርግና ምላሽ ሆኖለታል። በዚህ ሁሉ ግርግር ውስጥ ዛሬም እንቆቅልሽ የሆነብንን ውስብስብ የኢኮኖሚ፥ የፖለቲካ፥ የዘረኝነት የመሳሰሉትን ችግሮች ለመፍታት እንራወጣለን እንጂ እየሰመጥን እንደሆነ አላስተዋልንም። የነገሩን ክብደት ብናውቅ ነፍስ አድን ዘመቻን እናስቀድም ነበር። ግራ የሚገባው ችግርን ከመፍታት በፊት የህልውና ጥያቄ የሆነው በሽታና ውጊያ ስፍራውን ይለቅ ዘንድ አለመታሰቡ ነው። ስንኖር እኮ ነው ለችግራችን መፍትሄ የምንፈልገው። በሽታችን እየገደለን ባለበት ወቅት ቅድሚያ ለፈውስና ለተኩስ አቁም ክህሎት ቅድሚያ እንስጥ። ከቀን ወደ ቀን፥ በሽታችን ከውጊያው ትኩሳት ጋር ተደምሮ ከሰውነት ማንነት እያወጣን፥ እየጨረሰንና እያጫረሰን ባለበት ሁኔታ፥ ችግር ስለ መፍታት ማውራት ምን ይባላል? አውቀን ሳናውቅ አለቅን። ለበሽታችን መድሃኒት የሆነው ነገር፥ አንድ ሕፃን የሚያገናዝበው እውነት የሆነው አኳኋን (attitude) ነው። ከዚህ ቀላልና ተራ ከሆነ ነገር ብንጀምር፥ ጥበብ እያለን ጥበብ እንደሌለን ሆነን የምንኖረው አካሄድ ያቆማል። ይህ ትንሽ እውነት ወንድማችንን ከማጥፋት ላይ ፊታችንን አንስተን፤ ሁላችንም ፊታችንን ውስብስብ ወደ ሆነው እንቆቅልሾቻችን ዘወር እንድናደርግአቅም ይሰጠናል። የዚህ መድሃኒት ፍቱንነቱ በዋነኛነት የሚታየው ከሚያጠፋፋን ከእርስ በርስ ትንቅንቅ መገላገሉ ነው። ይህን ትንሽ ግርድፍ ሀቅ ንቀን፥ ትልቅና ረቂቅ የሆነውን ጥበባችንን የሙጥኝ ካልን፥ እያለን እንደሌለን ሆነን፥ ከድጥ ወደ ማጡ እንዳንዘቅጥ እፈራለሁ። እስቲ ለቅምሻ ያህል አስር አኳኋንን እንመልከትና ልባችንን በዚሁ መንገድ ላይ እናድርግ። ዐብይ ሲታይ: ዶ/ር ዐብይና የለውጥ ሃይሎች ተመከሩ አኳኋን (attitude) አንድ። ከመስማት ምንጊዜም አትቦዝኑ። ለሚቃወማችሁም ጆሮ አትንፈጉት። በተለይ የአመራር ትኩረታችሁ ፍፁም ፍትሀዊ እንዲሆንና በዚህ ጉዳይ የምትከሰሱበት አውድ እንዳይኖር ከሁሉ በፊት ያለ አድልዎ መሆንን ቅድሚያ ስጡት። አኳኋን (attitude) ሁለት። ለመስተካከልና ለማስተካከል ዘወትር ፍጠኑ። የሚሰራ ሰው ሁልጊዜ ይሳሳታል። ስለዚህ ምክንያት ሳትሰጡ ለስህተት ሃላፊነትን ውሰዱና በጊዜ አርሙት። ብድራታችሁን ዛሬ ከሚረዳችሁ የኢትዮጵያ አምላክ እና ነገ ከሚነገርላችሁ ታሪክ ጠብቃችሁ፤ ከትላንት በተሻለ ዛሬ ሁልጊዜ በአዲስ መንፈስ ለሥራ በፅናት መነሣትን አታሰልሱ። ሕዝብ ሲታይ: በመረዳት እንደግፈው እንጂ በጭፍን አንፍረድበት አኳኋን (attitude) ሦስት። እንደ አመፀኛ ዳኛ ፍርደ ገምድል አንፍረድ። ዶ/ር ዐብይ አንድ ሰው ነው። ዐብይ ማለት መንግስት ማለት አይደለም። ዶ/ር ዐብይ ያለበትን ጭንቅና ተግዳሮት አናውቅም። ራሳችንን ከጫማው ውስጥ እናስቀምጥና የተጣደበትን እሳት አግለን ለማንደድ ልባችን አይጨክን። ይህ ሲባል ዶ/ር አብይ ከሕግ በላይ አይነኬ ነው ማለት አይደለም። ሲሳሳት ማረም ሃላፊነታችን ነው። ቁም ነገሩ ስንናገር ሚዛናዊ መሆንና፥ በመልካም መንፈስ እርሱን ለማቅናት ካለን በጎ ፍቃድ የተነሣ፥ ቅንነትን መካከለኛ ማድረግ የሃላፊነታችን ሌላኛው ገፅታ መሆኑን ችላ እንዳንል ያስፈልጋል። አኳኋን (attitude) አራት። ሁሉንም በልክ እናድርግ። ዶ/ር ዐብይን እስክናመልከው በመውደድ ንጉሥ ማድረግም ሆነ፥ ሩቅ ቆሞ ጣት በመቀሰር ማጣጣል ሁለቱም ጤነኛ አይደሉም። እኛው ክበን፥ እኛው ንደን፥ ስራችን ሁሉ የዕብድ እንዳይመስል እንፍራ። ጠላት ሲታይ: ከማስተዋል እንዳንጎድል ሁልጊዜ እንንቃ አኳኋን (attitude) አምስት። የጠላትን ሤራ አንሳተው። ሰው ሁሉ ሰልፍ ሲወጣ፥ ዘፋኙ ሲዘፍን፥ ባለ ቅኔው ሲደረድር፥ ሴረኛው ከእኛ ጋር አልዘፈነም። ታዲያ ተንኮለኛው የት ነበር? ተንኮሉንና ሴራውን እንደ ቦንብ በየስፍራው እየቀበረ ነበር። ቀስ በቀስ እየሸረሸረ፥ ዶ/ር ዐብይን ከሚወደው ሕዝብ የሚነጥል ነፋስ በመካከል ይሰድ ነበር። የማይታየው ስውሩ ዕኩይ የሆነው ሤራው ሰምሮለት፥ እርሱ ምክንያት መሆኑ በሕዝብ ዕይታ እንዲሰወር ማድረግ ይሞክራልና እንንቃበት። አኳኋን (attitude) ስድስት። ለጠላት ሽፋን አንሁንለት። ኑሮ ማሸንፍ አነሳስቶን፥ የሤራ ንግድ ትርፍ አምጥቶልን፥ ሀገር በፈጠራ ተረት እያተራመስን የምናገኘውን ብርና ዝና ተንተርሰን የምንተኛ፥ ህሊናችንን ሸጠናልና ሳይመሽብን ወደ ልባችን ቶሎ እንመለስ። ሳናስተውል ቀርተን፥ የሴረኛው ፊትና ጭንብል ሆነን፥ አጥፊው ህቡዕ ሆኖ እጁ እንዳይታይ መተባበር ይቅርብን። እውነት እንናገር ካልን መኖሪያውን አትርፎበት ጠብ ከሚናገረው፥ ጠብ ጥሞት የሚሰማው ይበልጥ ይገርማል። አኳኋን (attitude) ሰባት። ጠላት መሆንን እንፀየፈውና እንተወው። እውነተኛው የኢትዮጵያ ጠላት ስጋና ደም ያለው አይደለም። እኛም የኢትዮጵያ ልጆች ነንና ከዚህ እኩይ መንፈስ መጠቀሚያ ከመሆን ራሳችንን እናስመልጥ። በሕዝብ ስም፥ በሕዝብ ላይ ቁማር መጫወት ምንም አይጠቅመንምና ይቅርብን። ከእልከኝነት ራሳችንን ታድገን፥ ለምን የግል ጥቅሜ ተነካ ብለን በሕዝብ ስም የሰይጣን እጅና እግር መሆንን አቁመን፥ ከመሃሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቀላቀል። ፈጣሪ ሲታይ: አሁንስ ተስፋችን ማነው? አኳኋን (attitude) ስምንት። ተስፋ ቆርጠን ያንኑ ተስፋ ቢስነት አንዝራ። የኢትዮጵያ አምላክ ስንት ጊዜ በተዐምር ኢትዮጵያን እንደታደገ እንዴት ተዘነጋን? አሁንስ የኢትዮጵያ ተስፋ ፈጣሪ እንደሆነ አናውቅምን? ኢትዮጵያ አምላክ እንደሌላት ምን ያቆዝመናል? የጨለመ የሚመስለው ይበራል። የተበላሸ የሚመስለው ሁሉም ይስተካከላል። አኳኋን (attitude) ዘጠኝ። ተዉ የተገላቢጦሽ አናድርገው። ቤተ እምነት መንግስትን በሞራል እየመራ ለመንግስት ሆነ ለምድራችን በረከት ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ፥ ዶ/ር ዐብይ ለሁሉም ቤተ እምነት በረከት ሆኖ አረፈው። ይሁንና አሁንስ ለአገር ድነት የማንነሳው እስከ መቼ ነው? ሃይማኖት ሳንለይ ኢትዮጵያዊ ከሆንን፥ ሁሉም የእምነት አባቶች በተቀናጀ መልክ ለኢትዮጵያ ፈውስ ቢያንስ አንድ ላይ ለወር ፆምና ፀሎት ሁሉም በየቤተእምነቱ እንዲያደርግ በምድራችን ላይ ማወጅ ለምን ተሳናቸው? ሰው ከአምላኩ ጋር በጥሞና እና በሱባዔ ልቡን ወደ ፍቅርና ይቅርታ መለስ እንዲያደርግ በር ይከፍቱልን ዘንድ አደራ እንላለን። እንዲህ ቢያደርጉ ወደፊት ለሚካሄደው ብሔራዊ እርቅና መግባባት መንገድ ጠራጊና ፋና ወጊ ይሆናሉ። የሁሉ ችግር ስርና መሠረት የሆነው መንፈሳዊው ነውና ፊት ፊት እየሄዱ እንዲመሩን ፀሎታችን ነው። አኳኋን (attitude) አስር። ፀሎት በሥራ ይገለጥ። አምላክን ለምነን ስናበቃ፥ የሚያዘንን በስራ ለመግለጥ ለምን አንነሳሳም? ብዙ ሩቅ ሳንሄድ አምላክ አገራችንን እንዲባርክልን እየጠቅነው፥ እርሱ ከሰጠን ገንዘብ አንድ ዶላር በየቀኑ ለደሃ ሕዝባችን ላለመስጠት ለምን ሰንካላ ምክንያት እንደረድራለን? ኢሜል፥ [email protected]
0 Comments
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በአስተዳደግ ኢትዮጵያዊነትን ኖረን፥ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ስብእና ሳይኖረን ቆይተን፥ በዘመናችን በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊም ሆነ አማራ መሆን ያልቻልን ሕዝብ ሆነናል። አቶ ጀዋር መሀመድ “ብሔርተኝነት ኒኩሌር ነውና አያያዙን ካላወቃችሁበት አደጋ አለባችሁ” እያለ እንዴት ብሔርተኛ መሆን እንደምንችል ሊያስተምረን ባለ ጊዜ ሆነ። ትላንት ኢትዮጵያ ትበታተን ሲለን የሞገትነው ወንድማችን፥ ዛሬ የብሔርተኝነት አሰልጣኛችን ሊሆንልን ፈልጎ ዝምታውን በዚህ ንግግር ሰበረ። መላው ምንድነው? ነፃ አውጭ ነኝ ብሎ ጫካ የገባ “የብሔር ፖለቲከኛ” ሁሉ አዲስ አበባ ገብቶ ሳለ፥ ዛሬ ደግሞ እኛ በተራችን ጫካ እንግባና ራሳችንን ነፃ እናውጣ? ደግሞስ ለዘመናት ለኢትዮጵያ ዘብ ቆመን፥ ዛሬ የኢትዮጵያን ግባተ መሬት እንጀምርና ሴራው ግቡን ይምታ? ከዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሳይቸግርህ ነግሠህ በእሳት ተጥደህ ማን በደረሰልህ? ሁሉም ተጠርጣሪ ይፍረደን ፈጣሪ። አንተ ቅን፥ ሕዝብ ቅን፥ ታዲያ ምን ያደርጋል? በመካከላችሁ፥ ሴረኛው ሰልጥኗል፤ በትንሹ ምላስ፥ ሰውን እያባላ የኢትዮጵያን ነገር፥ አሳጥቶ መላ፤ ለራሱ በሚኖር፥ ባይኖረውም ገላ ሀገር ተቃጠለ፥ ምድራችንም ቀላ። እኔ ፈርቻለሁ፥ እንዳይደክምህና በነገር አዙሪት፥ ልብህ ይደማና፤ ስልጣንህን ለቀህ፥ ያሁላችሁ ብትል አሰመሳይ ነህ ያሉህ፥ ያገቡናል ገደል። /አንተማ/ ሀገር መምራት ሳያንስ፥ ቄሶቹን አስታርቀህ ወንጌላዊ ባዩን፥ በላይ ጥበብ መክረህ ሙስሊሙን አንድ አርገህ፤ እስቲ እርዱኝ ብትል፥ ሀገርን እናድን ምንም አላየንም፥ ተባለ እንጂ አሜን። አንድ ሰው መሆንህ፥ እውነቱ ተረስቶ የከበበህ እሾህ፥ ያለምከው ተስቶ፤ /ጉድ እኮ ነው/ በራሱ ጣራ ስር ፥ፍቅር ቤቱ የለ ተጣልቶ ከራሱ ሌላን ያገለለ ጣቱን ቀሰረብህ፥ ሊፈርድም ፈጠነ የራሱን ጉድ ትቶ፥ ያንተን ጉድ መዘነ /እየዋለ ሲያድር/ የሚወጋህ በዝቶ፥ በግልፅ በአደባባይ ደጋፊህ በድብቅ፥ በዝምታ ሲያይ፤ የደፈረ ወዳጅ፥ ቃልን ቢሰነዝር በውርጅብኝ ብዛት፥ ቅስሙ ሲሰባበር፤ ብቻህን እንድትቀር፥ ሴሬኛው ሲያደባ ሁሉም ቀስ በቀስ፥ ወጥመዱ ውስጥ ገባ። /መቼ ነገስክና/ አጉሊ መነፅር፥ ለድካምህ ላጲስ፥ ለብርታትህ፤ ድምፅ ማጉያ፥ ለረባሹ የነገሠው፥ ጠብ መራሹ። ፍቅር ብለህ ሞተህ፥ ተደመሩ ብትል ሤራና ሸር ነግሶ፥ አላገኘህ ዕድል፤ አንዱን ስትገነባ፥ ሌላኛው ይፈርሳል ቅንነት ስትዘራ፥ አረሙ ያንቀዋል፤ ቆመን ስናሞግስ፥ ቁጭ ብለን ስንተች አረሙ አሸነፈን፥ ስንፈራ ያንን ተምች። አለቀ ደቀቀ፥ እንዳይሆን ነገሩ ወጥመዱ ይሰበር፥ ይነቀል ከሥሩ፤ ኢትዮጵያችን ታምልጥ እጃችንን አንስጥ። ሳይቸግርህ ነግሠህ በእሳት ተጥደህ ሕዝብ አለ ከጎንህ። ኢሜል፥ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ጀግና? ደግ ሰው እሺ። ትሁት ሰው፥ አዋቂ ሰው፥ አስተማሪ ሰው፥ ታታሪ ሰው፥ ቢባል ይሁን ያስማማናል። ግን አንዳንዶች ጀግንነትን ከዶ/ር አብይ ብርታት ጎራ አይመድቡትም። ይልቁንም የጀግነንት ማነስ ከድክመቱ ጋር ያያይዙታል። ጀግና አይደለም ይሉናል። ወሬ ብቻ ተባለ። እኔም ብሆን በዶ/ር አብይ ክስተት ተስፋ ሰንቄ፥ ከዚያ ፈንጥዤ፥ ደግሞም ተደናግሬ ሳበቃ የማታ ማታ የደረስኩበትን ላካፍላችሁ። ትንሽ በሞኝነቴ ታገሡኝና፥ ዶ/ር አብይን ለመግለፅ ጠቅላይ ገላጭ ቃል ቢኖር “ጀግና” ብቻ ነው። ሰውዬው በቃ ጀግና ነው ለካ። ቃሌን ጥቂት ላድርግና ለአንባቢ ህሊና ፍርዱን እተዋለሁ። ያለወትሮዬ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን “አንተ” ማለቴ በይቅርታ ይታለፍልኝ፥ ወደፊት አይለመደኝም። በወግና በባህላችን ጀግናን “አንተ” ማለት እንግዳ ስላልሆነ ቅር እንደማትሰኙ ተስፋ አደርጋለሁ። ኢትዮጵያ እንዴት ሰነበተች? 1ኛ/ በመጀመሪያ፡ ተስፋና ስጋት ተይዞ አብይ የኢትዮጵያ ሙሴ ሆነ ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ በሕዝብ ስነልቦና ያደረው ትልቅ ተስፋ ሲሆን፥ ካለው ፈተና ጋር በማገናዘብ የሚመጣ ስጋትም ጭምር ነበር። ያም ሆኖ ስጋት ቢኖርም በተስፋ ማነቆ ተይዞ ነበር። ተስፋና ስጋት ሞልቶን ዶ/ር አብይን እንደ ሙሴ ቆጠርን። ለዘመናት የተቆራኘንን ድቅድቅ ጨለማ የሚገፍና ወደ ብሩህ ተስፋ የሚያሻግረን ነብይ አድርገን ቆጠርነው። እኛ በእኛ ዓለም ተውጠን በተስፋና ስጋት ስንዋኝ፥ ጀግናው አብይ በሕይወቱ ተወራርዶ ራሱን አቀረበ። 2ኛ/ በመካከል ላይ፡ ተስፋና ስሜታዊ ፍቅር ተይዞ አብይ የኢትዮጵያ ንጉስ ሆነ አብይ አሕመድ በብርሃን ፍጥነት ለውጥን ሲያሽጎደጉድ ጉድ ተባለ። ትንፋሽ እንስኪያጥረን ድረስ በየማለዳው ትንግርት ማየት ጀመርን። በሕዝብ ልብ ውስጥ ገብቶ በአንድ ጀንበር ውስጥ ሀገር የወደደው መሪ ከአብይ ሌላ ይኖር ይሆን? ተስፋና ስሜታዊ ፍቅር አንሳፎን ዶ/ር አብይን ወደንና አወድሰን ስናበቃ አብይን ንጉስ ማድረግ ብቻ ቀረን። ከስብዕናው ከሚገለጠው መልዕክትና ከልብ የመነጩት የእውነት ቃላት ተወስደን ስናበቃ፤ ጅማሬ ላይ ያለን ሳይሆን መዳረሻ እንደ ደረሰ ሰው ተሰምቶን በራሳችን ዓለም በደስታ ሰከርን። ይህ ሁሉ ሲሆን ጀግናው አብይ እንቅልፍ አጥቶ፥ በራዕይ አርቆ የሚያያትን ኢትዮጵያ በፀጋ በተሞሉ ቃላት ከመግለጥ ባለፈ፥ ወደ ዕውን ለመቀየር በሙሉ እምነት ተሞልቶ ላይ ታች የሚራወጥ ጀግና መሆኑን አየን። ለዘመኑ ያለምርጫ በሙሉ የሕዝብ ልብ በጎ ፍቃድ ሀገር የሚገዛ መሪ ሆኖ ነበር። 3ኛ/ ዛሬ ዛሬ፡ ተስፋና ግራ መጋባት ተይዞ አብይ የኢትዮጵያ መሪ ሆነ የዶ/ር አብይ አመራር እንደ ፈጣን ባቡር ሽው እያለ ሲያስገመግም ሰንብቶ፥ ኮረኮንች መንገድ ላይ ደረሰ። ያኔ መንገጫገጭ ጀመረ። ሰው ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ከፍቅር ሰመመን ሲነቃ ማጣፊያው ቸገረው፤ ዱብ እዳ ሆነበት እናም ግራ መጋባት ሰፈነ። አሁን ሁላችንም ከደመናው ላይ ወርደን መሬት ረገጥን። እስካሁን ያልተቀየረ አንድ ስሜት ቢኖረን “ተስፋ” የሚለው ቃል ነው። ይህንን የስራ ጀግና በማየት እስካሁን ድረስ፥ በክፉም ሆነ በደጉ፥ ሕዝብ ተስፋን ፈፅሞ አልለቀቀም። ዛሬም በግራ መጋባት ዳራ ውስጥ ቢሆንም፥ ተስፋ ያንን ብዥታ ገርቶ ይዞታል። ይህ አይገርምም? አብይና ተስፋ አንለያይ አሉ። አሁን ያለንበት ጊዜ ግራ የመጋባት ስለሆነ ለዚህ ቃላት አላባክንም። ግን ይህም ስሜት ያልፋል። ከዚህ በኋላ የሚመጣውና በዘለቄታነት የሚቀጥለው ምን እንደሆነ ከመነጋገራችን በፊት፤ ሁላችንንም ወደዚህ አዲስ ቋሚ ስፍራ የሚወስደንን ቁምነገር መረዳት እንቻል። ወደዚያ የሚወስደን ደግሞ ባለ ሦስት ኮከብ ጀግና የሆነውን ጠቅላይ ሚኒስቴራችንን በአጉሊ መነፅር መመልከት ስንጀምር ነው። ባለ ሦስት ኮከብ ጀግና 1ኛ/ የጀግናው አብይ መገለጥ፥ በዓይነት የተለየውና በቁጥር የበዛው ሀሳቡ ፍቅር ያሸንፋል ብሎ በሀገር ደረጃ ለማስተዳደር የደፈረ ማነው? በይቅርታ እንሻገር ብሎ ያወጀ ደፋር ማን አለ? እንደመር ብሎ ምድርን ያነቃነቀ ፈላስፋ ማነው? ክርስቲያኑን ሙስሊሙን አቅፎ በፍጥነት ተሳክቶለት ከጥል ወደ ፍቅር ያደረሰ ማነው? ከኤርትራ ጋር ያለውን የጥል ግድግዳ በአንድ እጁ ነቅንቆ የደረመሰ አንበሳ ማነው? ሀሳቡ ወርቅ፥ የማይታሰበውን የሚያስብ፥ ለኢትዮጵያ የሚመጥናትን ለማለም ልቦናው የበራ ጀግና ኢትዮጵያ ማፍራት መቻሏ ያስደንቃል። በአደባባይ የሚናገረው፥ በልቡ ህሊና ያገናዘበውን ሲሆን፥ ጀግንነቱ ሩቅ አሻግሮ አይቶ የመጣው ይምጣ ብሎ ሁሉን ለእኛ መዘርገፉ ነው። እኛ ዛሬ ይሆናል ብለን የምጠብቀው ተዐምር በገሃዱ ዓለም የተገለጠው ዶክተሩ መናገር ስለቻለ ነው። አብይ የሚናገረውና የሚያስበው ግን እንዲሆን የትውልድ ርብርቦሽ የሚጠይቅ ነው። ዛሬ በምድር ላይ ያለን ሰዎች የዶክተር አብይን ሀሳብ በሙላት መገለጥ ሳናይ እንደምንሞት ማን ይንገረን? የምንደሰተው ለልጆቻችን መትረፉ እንደሆነ ብናውቅ ይበጀናል። አሁን አሁን ገደብ አበጅቶ ጋብ አለ እንጂ ያለውን ሁሉ ቢዘረግፍማ ጉድ ፈላ። መልካም ሀሳብ ማሰብ መቻል ብቻ ሳይሆን፥ ይቻላል ብሎ ለዓለም የሚያውጅ ጀግና አለን። መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ላይ ምን ያህል እምነት ቢጥል ነው? ጀግና ማለት እንዲህ ነው፤ ሕዝብ ላይ ተማምኖ ህልም የሚመስልና የማይታመነውን ለመግለጥ የሚራመድ። 2ኛ/ የጀግናው አብይ ጥሪ፥ አንዱ ብቸኛ ዓላማው ዶ/ር አብይ ሀሳቡ ብዙ ቢሆንም ዓላማው ደግሞ አንድና አንድ ብቻ ነው። ያም የዲሞክራሲ አዋላጅ መሆን ነው። ይህንን ታሪካዊ ጥሪ ለአንድ አፍታም አለመዘንጋቱ ግርም ይላል። ወደ ግራና ቀኝ የሚጎትተው ቢበዛም፥ የሚያዋክበው ጉዳይ ቢበረክትም፥ እሱ ግን አንድ ነገር ብቻ ላይ አነጣጥሮ ይመዘገዘጋል። ትኩረቱ ዲሞክራሲን በምድረ ኢትዮጵያ ማስፈን ነው። የበዛው ሀሳቡ ወደ ተግባራዊነት የሚመነዝረው አንድ መንገድ ቢኖር፥ ያ መንገድ ዲሞክራሲ ብቻ እንደሆነ ጠንቅቆ አውቋል። አሁን ያለውን የመሪነት ስልጣን ለዚሁ አንድ ዓላማ ብቻ ላይ ያነጣጠረ ነው። ብዙ መልካምና ውብ ሀሳብ ቢኖረውም፥ የሕዝብ ፍቅር ማዕበል ከወዲህ ወዲያ ቢንጠውም፥ እሱ ግን ዓይኑን ካነጣጠረበት አንድ ዓላማ ላይ ሊያስነሳው የሚችል ሃይል እስካሁን አልተገኘም። ተቃዋሚዎቹና ተችዎቹ ሁሉ ብዙ ምክንያት ይፈልጉበትና ያንን ውጋት የሚሰነዝሩበት፥ እሱ ራሱ ሊሞትለት ራሱን ለሰጠለት ዲሞክራሲን በመጠቀም ነው። ሁሉም ሰድቦት፥ ከፍና ዝቅ አድርጎት በየሚዲያው ሲጮህ፥ ዶክተሩ ሲተኛ ዓላማው እንዳልተዛነፈ እንዲያውቅ የሚረዳው ይመስለኛል። ሲያስብና ሲናገር ብዙ፥ ሲንቀሳቀስ ግን አንድ ብቻ። የሚገርም ጀግና ነው። በፍርሃትና በመደናገር ያንን ይዞ ሌላኛውን አይለቅም። መጀመሪያ የያዘውን ይዞ መሪውን እየመረሸ ነው። ውሎ ሲያድር እኛም ዓላማችን ዲሞክራሲ እንዲሆን አድርገን ብናግዘው ይበጀናል። ጀግናው ይጠራናል። 3ኛ/ የጀግናው አብይ ሃይል፥ ጥበብ ተኮር አመራሩ አብይ ጉልበትን ከመደገፍ ጥበብን መጠቀም መምረጡ ሌላው ጀግንነቱ ነው። የለመድነው “ዘራፍ!” የሚለውና የሚያቅራራውን ገዳይ ነው። አብይ ሰፊውን መንገድ ከመውሰድ ይልቅ፥ ማንም የማይወስደውን የጥበብ መንገድ መረጠ። የዶ/ር አብይን የፍቅር፥ የትዕግስት፥ የትህትና፥ የማስተዋል፥ የውይይት መንገድ እንደ ሞኝነት ቆጥሮ፤ ዶ/ር አብይን እንደ አቅመ ቢስ መሪ የሚያጣጥል ሰው አይፈረድበትም። ምክንያቱም በ “ቆፍጣና አፋኝና አምባገነን” መሪ ተቃኝቶ ያደገ ሰው የሚያወቀው ያንኑ ብቻ ነው። ጫማ በማይደረግበት መንደር ለመጀመሪያ ጊዜ ጫማ መሸጥ ከባድ ነው። ምንም እንኳን ጫማው ጠቃሚ ቢሆንም፥ ለማያውቁት ጫማ ገንዘባቸውን መስጠት ይከብዳቸዋል። ኢትዮጵያ ከሁሉም ይበልጥ የሚያስፈልጋት መድሃኒት ፍቅርና ይቅርታ ነው። ግን በመሪዎቻችን ዘንድ እነዚህ እሴቶች ባዕዳን ሆነው ባደግንበት ምድር፥ ዶክተሩ ይህንን እሴቶች ሊሸጥልን ድፋ ቀና ሲል፥ መዘባበቻ የሚያደርግ ሰው ቢኖር ምን ይገርማል? የዶ/ር አብይ ጀግንነት ከጥበብ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ ዘወር አለማለቱ ነው። የሚሰራ ሰው ሁሌ ይሳሳታል። ግን በጥበብ ለሚመላለስ ሰው ጥበብ ወደ ትህትና መርታ ታስተካክልና ወደ በረከት ታደርሳለች። የነገሩ ፍፃሜ ይህ ነው ሰውዬውን እንደ ነፃ አውጭ መሢህ፤ ወይም በፍቅሩ ተማርከን በራሳችን ላይ የምናነግሰው ንጉሥ፤ ወይም እንደ ወትሮው የለመድነው ዓይነት አንቀጥቃጭ የሀገር መሪ እንዲሆን አድርገን ማሰብ ይብቃ። ተስፋን ከስጋት እናፋታ። ተስፋን ከስሜታዊ ፍቅርም እናፋታ። በመጨረሻ ተስፋን ከግራ መጋባት እናፋታ። ተስፋን ከስሜታዊነት ነጥለን ስናበቃ ተስፋን ከሥራ ጋር አጋብተን ጠበቅ አድርገን እንያዝ። ተስፋን ከሥራ ጋር አዋህደን ከዶ/ር አብይ ጎን እንቁም። እርሱ ሰርቶ ምሳሌ በሆነባቸው ሥራዎች አብረነው እንሰለፍ፥ እንስራ። ጠቅላይ ሚኒስቴራችን በኢትዮጵያ አምላክ የተሰጠን ታላቅ ስጦታና፥ አይተን የማናውቀው “አገልጋይ መሪ” ነው። ሰሚ ያጣ ሕዝብ ሆነን ለዘመናት ኖርን። ታዲያ ጊዜ ተቀይሮ ዘመኑ የኛ ሲሆን፥ ዶ/ር አብይን በምድራችን የሚኳትን ሰሚ ያጣ አገልጋይ መሪ እናደርገው ዘንድ አይገባምና ይህ ከእኛ ይራቅ። ሲያጠፋ ተናግረን፥ ሲስት መልሰን፥ ሲዝል ደግፈን ደጀን እንሁንለት። የብዙ ዘመን ፀሎታችን ሲመለስልን፥ ትላንትን ረስተንና፥ በራሳችን ታብየን፤ የኢትዮጵያን አብይ ዕንቁ ሳንጠቀምበት ረጋግጠን ጥለን፥ ለበይዎችና አባይዎች ራሳችንን አሳልፈን እንዳንሰጥ በማስተዋል እንጠበቅ። ኢትዮጵያን በመንደር የከፋፈለውን አጥር እንዲያፈርስልን ከመጠየቅ ይልቅ፥ እስቲ እኛ በዙሪያው ደጀን ሆነን እንቁምለት። የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ በማያሻማ ሁኔታ ፍንትው አድርጎ አሳይቶ ካረካን፥ የዚህችን ኢትዮጵያ ትንሳዔ ለማድመቅ ሁሉም ወደ ሥራ ይሰማራ ዘንድ ይጠበቃል። ምክንያቱም ቀልባችንን የሳበችው ኢትዮጵያ ከዶ/ር አብይ በስጦታ የምንቀበላት ሀገር ሳትሆን፥ ከአገልጋዩ መሪያችን ጎን ቆመን በዲሞክራሲ አዋላጅነት የምትወለድ የዓለም ተስፋና የአፍሪካ ኩራት የሆነች ድንቅዬ እምዬ ናት። ለዚህ ግብአት እንዲሆን ዶ/ር አብይ የዲሞክራሲ አዋላጅነቱን በብቃት እንዲወጣ ሁሉም ራሱን የዲሞክራሲ ተማሪ ያድርግ። ፈጣሪ ይርዳው፥ እኛንም ይርዳን። እግዚአብሔር አሰበን እንወቅበት። ኢሜል፡ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ዛሬ ይቅርታ መጠየቅዎ የልቤን ቀልብ ሳበው። ትልቅ ሰው እንዲህ ነው። በዚህ ደብዳቤዬ ባለፈው ዓመት በደከሙበት ፈንታ በሚቀጥለው አዲስ ዓመት የሚልቁበት ይሆን ዘንድ ልሞግትዎ ነው። ይህ ሕዝብ አሁንም ዕድል እየሰጠዎት እንደሆነ በማወቅ በቃልዎ እንደሚተጉ አምናለሁ። ባለፈው ዓመት ብዙ ግሩምና ድንቅ ሥራ አደረጉ። በተጨማሪም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ደግሞ ግሩምና ድንቅ የተስፋ ቃል ሰጡን። በፊታችን ያለው አዲሱ ዓመት ደግሞ ከዚህ በፊት የተናገሩትን መልካም የፈውስና የአንድነት ተስፋ ቃል ወደ መሬት አውርደው በተግባር በመግለጥ ታሪክ የሚሰሩበት ይሆን ዘንድ ነው። እንግዲህ መደመርን የምናቀነቅነው ዜሮን እያዋጣን አይሁን። ሁሉንም በእኔነት እና በየኔነት አጥር እያጠርን፥ ለጋራዊ ኢትዮጵያዊነት ዜሮ መዋጮ ማዋጣት ይቅር። ከራሳችን ብሔር እንውጣ ሲባል በቃል ብቻ ሳይሆን በምግባር ይሁን። አዲስ አበባ ከእኛ አልፎ የአፍሪካ ናት ማለት ያልቻልን፥ በዚያ ፈንታ አዲስ አበባን በየኔነት አጥረን ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መዘከር ከንቱ ነው። አንድነት ከእኔነት ወደ እኛነት የማያሻግረን ከሆነ ትርጉሙ ምንድነው? በመደመር ዘመነ መንግስት እስክንድር ነጋ በምደረበዳ የሚጮህ የመደመር ድምፅ ሆኖ ሲገኝ እርስዎ ግራ መጋባትዎ ግራ ያጋባልና አንድ ይበሉ። ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኦ ብሎ በፍፁም ፍቅር እርስዎን ማወደሱና መደገፉ፥ የእርስዎን ታላቅነት ከማሳየቱ በላይ፥ የዚህን ሕዝብ የልብ ንፅህና እና ቅንነት የሚያሳይ ነው። ይህን የፍቅር ሕዝብ ከዘረኛ ፌዴራሊዝም ቀንበር አርነት አውጥተው፥ ወደ ቤተሰባዊ ፌዴራላዊ አስተዳደር ያሻግሩት ዘንድ ምድርና ሰማይ ይጮሃል። እባክዎን ጆሮ ይስጡ። እርስዎን የኢትዮጵያ ሙሴ ብሎ ሕዝብ ተስፋ አድርጎ ነበር። እናስተውልና ትምህርት ከጥንቱ ታሪክ እንውሰድ። እስራኤል ከግብፅ ባርነት ነፃ ሲወጣ በደስታ ነበር። ጥቂት ሳይቆይ የግብፅ ሰራዊት የእስራኤል ሕዝብን ሊገድል ከበስተዋላቸው ሲያሳድዳቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ተጨነቁ። በመጨረሻም አምላክ ጣልቃ ገባና እስራኤል የኤርትራን ባህር ተሻገሩ፥ አሳዳጁም ሰጥሞ ቀረ። አሁንስ ተስፋችን ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ኢሜል፥ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
እስረኞች ሁሉ ተፈቱ። ዴሞክራሲም ተወለደ። በደስታ ሰከርን። አሁን አሁን ግን የጫጉላ ጊዜ እየጨረስን ይመስለኛል። ዶ/ር አብይ የምንቅፍብዎት አንድ ነገር አለኝ። በሕግ የጊዜ ሂደት ሳይሆን ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ሕዝብን በወከባ ማፈናቀል የብርሃን ስራ አይመስለኝም። ጉዳዮን ወደ ፍርድ ቤት ይምሩትና ዜጎች መንግስትን ፍርድ ቤት ቆመው የሚሞግቱበት እውነተኛ ነፃና ፍትሀዊ ሀገር እንድትሆን ፈር ቀዳጅ ይሁኑ። ከዚያ ባለፈ ሕዝቡን ሜዳ ላይ ከመበተን፥ የሚያርፉበትን ስፍራ ጭምር ማሰብ ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊ የመሆን ክብር በምድራችን እንዲነግስ አድርገው ሲያበቁ፥ በእርስዎ ብሩህ ዘመን እንዲህ ዓይነት ጭካኔ የማይታሰብ ነው። ይህ ዓይነት ሥራ ከእርስዎ ስብዕና ጋር አይሄድም። በዝምታ ሊያልፉትም አይገባም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅና ለመፈናቀል ችግር ማስተካከያ በመስጠት ይሻገሩ ዘንድ እለምንዎታለው። ዶ/ር አብይ አህመድ ገና በኢሕአዴግ ሳይመረጡ “ጆሮ ያለው ይስማ” በማለት የእርስዎን ወደ ስልጣን መምጣት ስመኝ ነበር። ምኞቴ ሰምሮ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት መምራት ሲጀምሩ ከስጋት ይልቅ ተስፋ አይሎብኝ ብዙ ብዙ ብያለው። እስካሁን ድረስ እርስዎ መደመርን ሲሰብኩ፥ ዘራፍ ማለትን ወደ ጎን ትተው፥ በሀሳብ ልዕልና አሸንፎ መደመርን ለማሳለጥ ትዕግስትን ጨብጠው ነውና አከብርዎታለው። እኛ የለመድነው “ስንኖር ጎሣዊ”፥ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን አምክነን “አፈር” ነን ማለትን ነበር። እርስዎ ግን ብቅ ብለው “ስንኖር ኢትዮጵያዊ፥ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን” ያሉት ራዕይ ብርሃን ፈነጠቀ። በፍቅር ተደምረን በይቅርታ እንሻገር ብለው ያከናወኑት ድርጊቶች በታሪክ ቦታ አላቸው ብዬ አምናለሁ። እውነተኛ ምርጫ አካሄደው ከተሸነፉ ከስልጣን ለመውረድ ቁርጠኛ እንደሆኑ አልጠራጠርም። በእኔ ግምት የተጣለብዎትን የዲሞክራሲ አዋላጅ የመሆን ሃላፊነትዎን በብቃት እንደተወጡ አምናለሁ። ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ዛሬ ዛሬ እርስዎ ፊት የተጋረጠው እንቅፋት እጅጉን ያሰጋኝ ጀመር። ምክንያቱም ያስወለዱትን ዴሞክራሲ የሚገድልና ይልቁንም ወደ ብርሃን ከመሻገር ይልቅ ወደ ድቅድቅ ጨለማ እንድንዘፈቅ የሚያደርግ የዘራፍ ፈተና ውስጥ ለመግባት ዳዴ እያልን ስለሆነ ነው። እስካሁን እንድንኖር የተደረገው በየጎራችን ተከፋፍለን “ሁሉም ለራሱ” በሚል እሳቤ ነበር። ታዲያ “ስንኖር ጎሣዬ” ከሚለው አመለካከት በቃልና በስራ ሁላችንም ተግባብተን ወደ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ” ለመሻገር፥ አሻጋሪ መንገዱን የሚጠርገው ዴሞክራሲ ብቻ ፍቱን መድሃኒት እንዲሆን ታስቦ ዴሞክራሲ ተወለደ። ታዲያ ዴሞክራሲ ተወለደ እንጂ የተወለደውን ዴሞክራሲ ተጠቅመንና በቅንጅት ተደራጅተን ራዕዩን በሕዝብ ድምፅ አሸናፊነት ዕውን ለማድረግ እምብዛም ብዙ መንገድ አልሄድንም። እርስዎ ለማካሄድ የሚሮጡለት ምርጫ አዲስ የሕዝብ መንግስት ለመመስረት ብቻ ሳይሆን፥ የሚመረጠው መንግስት የሚያስተደዳድረው “ኢትዮጵያዊነትንም” በአብሮነትና በዴሞክራሲ ሂደት እንዲወለድ ለማስቻል ነው ብዬ አምናለሁ። ዶ/ር አብይ ዘራፍ የማይሉ መሪ መሆንዎ ያስገርመኛል፥ ያስደስተኛልም። አንዳንዴ ግን በዝምታ የሚሄዱት መንገድ ለእንቆቅልሽዎ መላ እስካልፈጠሩ ድረስ ረዥም አይሆንም ብዬ እፈራለሁ። ምክንያቱም ዘራፍ ማለት የተጠናወታቸው ፖለቲከኞችና አክትቪስቶች አሉንና። ሲሆን ሲሆን በተሻለ አሳብ ለመግባባት ወደ ውይይት፥ ካልሆነ ደግሞ በሕዝብ ድምፅ ለመዳኘት ወደ ፉክክር መግባት እንድንችል አቅም የሚሰጠንን ዴሞክራሲን ገና አልተዋወቅነውም። አሁንም የየግል አጀንዳዎቻችንን ሕዝብ ላይ ለመጫን ዘራፍ ማለት ይቀናናል። በምድራችን የተወለደውን ለጋ ዴሞክራሲ በመጠቀምና በማሳደግ ወደ መግባባት መሄድ የሚያስችለውን የዴሞክራሲ ጉዞ ፋታ እንዳያገኝ ደንቃራ መሰናከያ ድንጋይ እንፈጥራለን። የተወለደውን ዴሞክራሲ ገድለን ጡንቻ ማግነንን እንደ አንድ አማራጭ የያዝን ይመስላል። ምናለበት ዴሞክራሲ ይዳኘናል ብለን የምናምንበትን ሀሳብ ለሕዝብ ማስተማርና ሁሉንም ጉዳይ ለውይይት ማቅረብ ጊዜና ቦታ መስጠት ብንችልበት? ጥያቄው አሁን እንዴት ካለንበት አጥፍቶ ከመጥፋት፥ የመጠፋፋት ጨለማ ውስጥ ወጥተን፥ በፍቅር ብርሃን ተደምረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው። መልሱ ደግሞ ሲሆን ሲሆን ለተሻለ ሀሳብ ለመሸነፍ በዴሞክራሲ እሴት ወደ ውይይት መሄድ፥ ያ የሚያግባባ መፍትሄ የማያመጣ ከሆነ ደግሞ በሕዝብ ምርጫ ለመዳኘት በሁሉ መስክ ዴሞክራሲ እንዲገዛን ራሳችንን ለዴሞክራሲ መስጠትን መተግበር ነው። ይህም ዕውን እንዲሆን ደግሞ መቀናጀቱን ማጠናከር ያስፈልጋል። በዘራፍ አዋጅ ሀገር ለመንዳት ወይም እርስ በርስ ለማዋጋትና ለመዋጋት ከማሰብ፥ በመደመር ስሌት አካሄድ፥ ሲሆን በውይይት ሳይሆን በህዝብ ዳኝነት፥ መግባባት ላይ እንደርስ ዘንድ የዴሞክራሲ እሴት እንጠቀም። ከሚያጣሉን ጉዳዮች አንዳንዶቹን ለምሳሌ ያህል ከዚህ በታች መጥቀስ ይቻላል። 1ኛ/ ሕዝብን የማፈናቀል አባዜ መቼና እንዴት ይቆማል? 2ኛ/ የክልል ድንበር ጥያቄ መቼና እንዴት ዕልባት ያገኛል? 3ኛ/ ራስን በክልል መንግስት የማስተዳደር ጥያቄ መቼና እንዴት መልስ ያገኛል? 4ኛ/ በሃላፊነት ስፍራ የተቀመጡ ሰዎች የጎሣዎች ስብጥር ፍትሀዊነት አለው ወይ? 5ኛ/ የሕግ የበላይነትን የማስፈን ተግዳሮቶች እንዴት ይፈቱ? 6ኛ/ ሕዝብ የሚመርጠው ፕሬዚዳንት ይኑረን ወይስ ፓርቲ የሚመርጠው ጠቅላይ ሚኒስቴር ይኑረን? 7ኛ/ ባንዲራችን የትኛው ይሁን? 8ኛ/ አዲስ አበባ የማን ናት? 9ኛ/ የትኛው የፌዴራሊዝም ስርአት ለሁላችንም ፍትሐዊ ነው? 10ኛ/ ብሔራዊና የስራ ቋንቋዎች የትኞቹ ይሁኑ? 11ኛ/ ለአፍሪካ አንድነት ፋና ወጊ መሆንን እንደ ታሪካዊ ብሔራዊ ጥሪ እንውሰድ ወይ? 12ኛ/ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ የሚለውን ዘይቤ እንደ ሕዝብ ዕውቅና እንስጥ ወይ? ወዘተ ዶ/ር አብይን የምንደግፍም ሆን የምንቃወም ሁሉ አንድ ነገር እናስብ። ኢትዮጵያ ከዶ/ር አብይ በላይ ናት። እርሳቸው መልካም አደረጉም ክፉ ያልፋሉ። ኢትዮጵያ ግን ትቀጥላለች። ስለዚህ ኢትዮጵያን አስበን፥ ዶ/ር አብይ የሕዝብን ዳኝነት በሚፈልጉበት ሂደት ውስጥ በምርጫ ዴሞክራሲ ማሳለጥ ሥራ ሁላችንም እንድንተባበራቸው ያስፈልጋል። ከዚያ በተረፈ ኢየሱስ ክርስቶስን የመሰለ ስብዕና ያለውን በአንድ ወቅት ሕዝቡ ሊያነግሰው ሲፈልግና፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ ያው ሕዝብ ሊሰቅለው ሲፈልግ አይተናልና አምላክ ከዚያ ይጠብቀን። ይልቁንም ኢትዮጵያን ለመታደግ፥ ሌት ተቀን ያለ እረፍት ደፋ ቀና የሚሉትን እኚህን የኢትዮጵያ ልጅ በቃላችን ከማፍረስ ይልቅ፥ ሲያጠፉ በመምከርና ሲያለሙ ደግሞ በማበረታት፥ በሁለቱም ረገድ ሰውን መገንባት ስራችን ማድረግ የቅንነት ምልክት ነው። ከሁሉ በላይ በዴሞክራሲ ሜዳ ላይ ለመፋለም ሁላችንም በየፊናችን በሚያግባቡን ሀሳቦች ዙሪያ ተቀናጅተን ኢትዮጵያን ለመታደግ እንነሳ። እኛ የነገውን ዕድል ፈንታ እንደ ሕዝብ የምወስን እኛ ራሳችን እንደሆን አውቀን የዜግነት ግዴታችንን በንቃትና በመተባበር ካልተወጣን፥ ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያ ትንሣኤ መንገድ ላይ የተደነቀረውን ወጥመድ ጥሰው ኢትዮጵያን ማሻገር ተራራ ይሆንባቸዋል። ከሁሉ በፊት ሰብዓዊነት ይቀድማልና፥ የተፈናቀሉት ሰዎች ጉዳይ አደራ! እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አሰበ። እኛም እንወቅበት! እግዚአብሔር አፍሪካን ይባርክ። ኢሜል፥ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም በብሔር ወይም በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ነው እንዳልል ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔሮች ሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማካተት ቀርቶ ባብዛኛው እንኳን የማያሳትፍ ስለሆነ በተለምዶ የዘር (ethnic) ፌዴራሊዝም የሚባለውን አጠራር መጠቀም አልችልም። አሁን ያለው ፌዴራሊዝምን “የኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ” ከማለት በቀር ሌላ ቃል ላገኝለት አልቻልኩም። በዚያው መልክ ወደፊት እንዲኖረን የምሞግተው ፌዴራሊዝም በዓይነቱ አዲስ መሆን ያለበት ስለሆነ “የመደመር ፌዴራሊዝም ” በማለት ለመግለፅ ወድጃለሁ። በኢትዮጵያ ከ 80 በላይ ብሔረሰቦች ወይም ጎሣዎች እንዳሉ እናውቃለን። የኢሕአዴግ ፌድራላዊ መንግስት ጥቂት ጎሣዎችን አግንኖ እና ብዙ ጎሣዎችን ጨፍልቆ በክልል መንግስታት አደራጀን። በእውነት ሁሉንም ጎሣዎች በእኩልነት የሚዳኝና የሚያስተናግድ ስርዓት አይደለም። ከዚያም በላይ የኢትዮጵያን አንድነት ጥያቄ ውስጥ የሚከትና እርስ በርስ በማጋጨት የሚያፈናቅል ስንክሳር ሆኖ እየተገለጠ ይገኛል። ይህንን ውጥረት ለመፍታት የብሔር ፖለቲካና የዜግነት ፖለቲካ በሚያደርጉት ሩጫ፥ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ ራሳቸው የእርስ በርስ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። ያም የሆነው የኢሕአዴግ ፌዴራላዚም በሚያመጣው ተፅዕኖ ምክንያት ነው። ለዚህም ነው ይህ የኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም ራሱ ችግር መሆኑ ብቻ ሳይሆን፥ ሌላ መፍትሔም እንዳይመጣ ጭምር የሚያስረንና የማይድን የኢትዮጵያ በሽታ መስሎ የሚታየው። በብሔር ፖለቲካ እና በዜግነት ፖለቲካ መካከል ያለውን ፍጥጫ በስኬት ለመፍታት፥ መደመር ላይ ከተመሰረተው ሀገር በቀል የኢትዮጵያዊነት ርዕዮተ ዓለም ውስጥ አስታራቂ የመደመር ፌዴራሊዝምን ፈልቅቆ ማውጣት ያስፈልጋል። ይህ መደመር ብሎ ነገር፥ ከስሜታዊ ትርክቶች አልፎ መሰረታዊ የሆኑ የማንነት ጥያቄዎቻችንን የሚመልስና በብዝሃነት አንድነት አያይዞ ወደፊት የምንሄድበትን አቅጣጫ ማመላከት መጀመር ያለበት ወቅት አሁን ይመስለኛል። በአንድ በኩል ለእውነት እኩልነትና የማንነትን ጥይቄ በፍትሀዊነት ለመመለስ የመደመር ፌዴራሊዝም ስሌት መፍትሔ አለው። ደግሞም በልዩነት የማይበጣጠስ ግን በልዩነት የሚደምቅና የሚሰምር እውነተኛ አንድነት እንዲኖረን የመደመር ፌዴራሊዝም ፋይዳ ያመጣል። ይህም የሚሆነው የመደመር ፌዴራሊዝም የብሔር ፖለቲካንና የዜግነት ፖለቲካን አቻችሎ ሁለቱም አብረው እንዲያሸንፉ የመፍትሔ መውጫ አቅጣጫ ስለሚያስቀምጥ ነው። በዚህም ምክንያት እንድንነካከስና እንድንጠፋፋ ከተጠመደልን ወጥመድ ሰብረን በብልሃትና በትልቅ ጥንቃቄ አንድ ላይ ተያይዘን እንድናመልጥ የመደመር ፌዴራሊዝም አቅም ይሰጠናል። በአንድ በኩል ጎሣዎች የራሳቸውን እድል በራስ በማስተዳደር እንዲወስኑ እንፈልጋለን። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ጎሣዎች ስብጥርና በጂኦግራፊ አቀማመጥ ድብልቅ እንደሆነ እናያለን። ደግሞም 80 በላይ የሆኑ ጎሣዎች በእኩልነት እንዲወከሉና ሁሉም ድምፅና ተሰሚነት እንዲኖራቸው እንፈልጋለን። ለዚህ አንደኛው መድሓኒት ጎሣን በዞን ደረጃ መከለል ነው። ይህ አናሳ ጎሣዎች ሁሉ የየራሳቸው የዞን ክልል እንዲኖራቸው ዕድል ይሰጣቸዋል። ትላልቅ የሆኑት ጎሣዎች ደግሞ በየአቅራቢያቸው ዙሪያ በየቀጠናቸው እየሆኑ ከአንድ በላይ የዞን ክልሎች እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል። እያንዳንዱ ዞን ራሱን እንዲያስተዳደርና ለሕዝብ ተወካዮችም ከዞናቸው በመላክ በፓርላማ መሰየም ይችላሉ። ከዚያ ባለፈ እነዚህ በጎሣዎች የተዋቀሩት ዞኖች በመንግስታት ስር የሚከለሉት በጂኦግራፊ ይሆናሉ። ያ ማለት የደቡብ ክልል መንግስት፥ የሰሜን ክልል መንግስት፥ የምዕራብ ክልል መንግስት፥ የምስራቅ ክልል መንግስት፥ የደቡብ ምስራቅ ክልል መንግስት፥ የሰሜን ምዕራብ ክልል መንግስት፥ ወዘተ በማለት ማዋቀር ይቻላል። እያንዳንዱ መንግስት በውስጡ የተለያዩ ዞኖች ይዞ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በመሆን የገለጣል። ፓርላማ በዚህ ዓይነት የብሔር ማንነትን እና የዜግነት እኩልነትን ባስታረቀ መልኩ በሕዝባዊነት መሠረት ላይ ቢታነፅ መካከለኛ ቦታ ላይ ሁላችንንም ያገናኘናል ብዬ አስባለሁ። ይህን ዓይነት በጂኦግራፊ የተመሰረተ መንግስታት እንዴት ማድረግ እንችላለን እንዳንል፥ በፍርደ ገምድልነት አንዱን ብቻ ነጥለን የደቡብ ክልል መንግስት ብለን አናሣ ጎሳዎችን አንድ ላይ ደምረን መንግስት እንዲኖራቸው ለ 27 ዓመት ያደረግን ጉደኞች ነን። ያንን ለደቡብ ሕዝብ አድርገን ስናበቃ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ስንል፥ በዚያው መስፈርት ራሳችንን መዝነን በሁላችንም ላይ በፍትሀዊነት ለምን አላደረግንም? የሞራል ልዕልና ካለንና ራሳችንን ከሌላው በላይ አድረገን በእውነት ማየት የማንፈልግ ከሆነ፥ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ የመደመር ፌድራላዊ መንግስት ስር ያሉ የደቡብ፥ የሰሜን፥ የምዕራብ፥ የምስራቅ ወዘተ መንግስታት እያልን በፍትሀዊነት ማስተካከል ይጠብቅብናል። ይህን ስናደርግ መደመርን በተፈጥሯዊ(organically) እንዲያድግ እንፈቅዳለን። በመጀመሪያ ደረጃ በጂኦግራፊ በተመሰረቱት ክልል መንግስታት ውስጥ ያሉ የተለያዩ በጎሣ የተዋቀሩ ዞኖች መደመርን አቅራቢያቸው ካሉት ኢትዮጵያውያን ጋር ይለማመዳሉ። በሁለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ የመደመር ፌድራላዊ መንግስት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ መደመርን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሳልጣሉ። በሶስተኛ ደረጃ መደመርን ለአፍሪካ በመሸጥ ምስራቅ አፍሪካ ብሎም መላው አፍሪካ ወደ አንድነትና አብሮነት በመጠቅለል መደመር በጥቁር ሕዝብ ላይ ብሩህ ብርሃን ያበራል። በአራተኛ ደረጃ ለዓለማችንም ይህ የመደመር ህሳቤ ገፀ በረከት ሆኖ ይተርፋል። የኢትዮጵያ የመደመር ፌድራላዊ መንግስትን ደግሞ የሚመራ (ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዳንት) ሕዝቡ ራሱ እንዲመርጥ በማድረግ፥ የሚልቅ አሳብ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከአናሣ ጎሳም ጭምር ለመመረጥ ፍትሀዊነት ያለው ዕድል ይኖረዋል። በኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ጣጣ ምክንያት ብዙ ቁጥር ያላቸው ጎሣዎች ሊሂቃን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ተመልከተውና ለአናሣዎቹ ብሶት ጆሮ ዳባ ብለው የራሳቸው የሆነውን ለማግነን ተገደው ደፋ ቀና ይላሉ። ዛሬ እኩልነትን ስናቀነቅን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሆን ሆኖ እንዲሰራ ሳይሆን፥ ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ ሊሂቃን በየፊናው ራሳቸውን የበላይ የሚያደርጉበትን ስሌት ለመቀመር በራሳቸው ዘር ላይ እንዲያጠነጥኑ ይገደዳሉ። እነዚሁ ሰዎች ድሮ ድሮ ለጭቁን ሕዝብ ብለው ታግለው ንጉሱን የገረሰሱት በሰው መሆን ስብዕና ላይ ተመሰርተውና ተያይዘው እንጂ፥ እንደ ዛሬ በየግል ጎሣ አጥር ውስጥ ሆነው እየተራኮቱ አልነበረም። ከዚህ ከያዘን አባዜ የምንነቃው የኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ለሁላችንም የተለያየ መነፅር ሰጥቶንና በማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ከቶን የጭቅጭቅ ድራማ እንድንከውን ያደረገንመሆኑን አውቀን ራሳችንን ከዚህ ወጥመድ ስንፈታ ነው። መደመር ስሌት ላይ አተኩረን ተደምረናል ስንል የድምራችን ውጤት ዜሮ እየሆነ ያሳብቅብናል። መደመር ውጤታማ የሚሆነው ተደምረናል የምንለው ቀናሽ ቁጥር (negative number) እስካልሆንን ድረስ ብቻ ነው። አንዱ ሲተክል ሌላው እየነቀለ የደቦ ድምር ሆነን በዜሮ እንዳንጨርሰው እንጠንቀቅ። ከመደመራችን በፊት ቀናሽ ቁጥር (negative number) ከመሆን ራሳችንን እናፅዳ። ቀናሽ ቁጥር ላለመሆን ደግሞ ለራስ መቆም ብቻ ሳይሆን የወንድሞቻችን (በተለይ የተረሱትና አናሣ ለሆኑት) ፍፁም ፍትሀዊ የመሆን እሳቤ ያስፈልጋል። ኢ+ት+ዮ+ጵ+ያ = ፍቅር። ኢትዮጵያዊነት የፍቅር ቤት ነው። 1ኛ/ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ቤት መሰረት የጥቁር ሕዝብ አንድነት ፋና ወጊነት ሆኖ መገኘታችን ነው። ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የጎሣዎች ስብስብ በላይ ነው። ይህም የሆነው ኢትዮጵያዊነት በውስጡ የአፍሪካን አንድነት ያረገዘ ራዕይ ሰንቆ እንዲንቀሳቀስ ታሪክ ግድ የሚለው ስለሆነ ነው። 2ኛ/ የኢትዮጵያዊነት የፍቅር ቤት የማዕዘን ምሶሶዎቹ ብዙ ቁጥር ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ጎሣዎች ናቸው። እነዚህም የኢትዮጵያዊነትን ግዙፍ ራዕይ ክብደት የሚሸከሙና በመስዋዕትነት ኢትዮጵያዊነትን የሚያቆሙ ናቸው። 3ኛ/ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ቤት ግድግዳው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አናሣ ጎሳዎች ናቸው። እነዚህም እርስ በርስ በመያያዝና ከምሶሶዎቹ ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያዊነትን የፈጠሩ ናቸው። 4ኛ/ የኢትዮጵያዊነት የፍቅር ቤት ጣሪያው የኢትዮጵያ አምላክ ነው። ፈሪሃ ፈጣሪ ያለው ሕዝብ እርስ በርስ ሰላምታ በሰጠና በተቀበለ ቁጥር የፈጣሪን ስም የሚጠራ ሲሆን በረከትን ከሰማይ ይለምናል። ከስንት ጉድ እያወጣን ለዛሬው ብሩህ የተስፋ ጭላንጭል ቀን ያደረሰን ፈጣሪም ዳር ሳያደርሰን አተወንምና በስጋት ከመሽመድመድ ይልቅ ተስፋ በማድረግ መደሳሰት ይቀናናል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሰበ። እግዚአብሔር አፍሪካን ይባርክ። ኢሜል፦[email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ትላንትንና ዛሬን እያጣቀስን አዲስ አበባን በባለቤትነት ለመውረስ የምናደርገው ትርምስ ይገርማል። አንዱ የኦሮሞ ናት ሲል፥ ሌላኛው የአዲስ አበቤዎች ናት ይላል፥ ደግሞ ሌላኛው የኢትዮጵያ ናት ይላል። ዛሬ ላይ ቆመን ይህንን ማሰባችን አሁንም ነገን እያገናዘብን እንደማንራመድ ያሳያል። ነገ የሚሆነውን አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ከመነሳት ይልቅ፥ አሮጌ ታሪክ ወይም ዛሬው ያስረናል። ታዲያ መድረሻችንን የማናውቅ ሆነን ሳለ፥ በለውጥ ጎዳና ላይ ነን ማለት ጥቅሙ ምንድነው? አዲስ አበባ የኦሮሞ፥ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት መዲና ሆና ዛሬ እያገለገለች ነው። ነገን ብናይ ደግሞ አዲስ አበባ የእኛ አይደለችም። ነገ የምስራቅ አፍሪካ አንድነት ብሎም የመላው አፍሪካ አንድነት ህልውና ከሕልምነት ወደ እውንነት ስለሚለወጥ፥ አዲስ አበባ ለዚያን ወቅት እየተሞሸረች ያለች የጥቁር ሕዝብ ሁሉ ዋና ከተማ ልትሆን ያለች ናት። ነገን ዛሬ እንዳየ ሕዝብ፥ ሁላችንም አዲስ አበባን በዚህ መነፅር አይተን፥ አዲስ አበባን ለጥቁር ሕዝብ የምስራችና የድል ዜና አብሳሪና ተስፋ ሰጭ ማዕከል እንድትሆን እንፍቀድላት። የራሳችን ጎሣ እንደ ትንሽ ደሴት በልፅጎና አድጎ ለብቻው በጨለማው ኢትዮጵያ ላይ እንዲገን እንፈልጋለን? ኢትዮጵያ እንደ ትንሽ ደሴት በልፅጋና ተመንድጋ ለብቻዋ በጨለማው አፍሪካ ላይ ገና እንድትታይ እንመኛለን? ካለንበት አዘቅት አንዳችን በአንዳችን ላይ ተረማምደንና ሁሉንም ወደ ዋላ ጥለን፥ ራሳችንን ብቻ ይዘን ወደ ላይ መውጣት አንችልም። የራስ ጎሣ ተኮር ሆኖ ሁሉንም በዚያ መነፅር ማቀንቀን ጠባብነት እንደሆነ ሁሉ፥ ኢትዮጵያ ተኮር ብቻ ሆኖ ሁሉንም በዚያ መነፅር ማቀንቀን መጥበብ ነው። በኢትዮጵያዊነት ስም አብሮነትንና አንድነትን ስናስብ፥ ጥቁር ሕዝብ ሁሉ እንዲያሸንፍ እናልም። እኛ በጎሣ ተከፋፍለን እርስ በርስ ስንነካከስ፥ ልዩነታችንን እናገናለን እንጂ በዓለም ዕይታ ሁላችንም አንድ ጥቁር ሕዝብ ነን። የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ባስገባንበት ባሁኑ ወቅት፥ የአፍሪካን አንድነት ማሰብ ጅልነት ነው ይባል ይሆናል። ነገር ግን ነገራችንን ከአፍሪካ አንድነት ሳንጀምር ቀርተን፥ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ መነታረካችን፥ ለመራኮታችን ምክንያት ቢሆንስ? የተጠራንለትን ታላቅ ጥሪ ችላ ብለን፥ በመንደር ህሳቤ እርስ በርስ ስንበላላ እንዳንጠፋፋ ፈጣሪ ይርዳን። የነገው የምስራቅ አፍሪካ ብሎም የመላው አፍሪካ ዕምብርት ለመሆን ዕድል ያላት አዲስ አበባን ለዚህ ታላቅ ጥሪ እንድትመረጥ ታሪክ ስላደላት፥ ኦሮሞም ሆን፥ አዲስ አበቤዎችም ሆን፥ ኢትዮጵያውያንም ሆን፥ ሁላችንም በአዲስ አበባ ልዩ ታላቅ ጥሪ ልንኮራ ይገባል እንጂ፥ አሸናፊና ባለቤት ለመሆን እርስ በርስ አንጣላ። አዲስ አበባ ከእኛ በላይ የሆነች ለጥቁር ሕዝብ ምልክት ናት። ይልቁንስ ለአፍሪካ መድሃኒት ሆነን ራሳችንን እንድንፈውስ፥ ለጥቁር ሕዝብ ልዕልና ፋና ወጊ እንሁን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሰበ። እግዚአብሔር አፍሪካን ይባርክ። Email: [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሕዝቡ መሪውን ራሱ እንዲመርጥ የሚያስችለውን አሠራር (ፕሬዚዳንታዊ መንግስት) ወይም ደግሞ እንደ አሁኑ ፓርቲው መሪውን እንዲመርጥለት የሚያደርገውን አሠራር (ጠቅላይ ሚኒስቴራዊ መንግስት)፤ ከሁለቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ፈቃዱን እንዲያስታውቅ ለሕዝቡ በሪፈረንደም ዕድል ይሰጠው ዘንድ ለመሞገት አራት ማስረጃዎች አቀርባለሁ። 1ኛ/ ሕዝቡ አዋቂ ነውና እናውቅልሃለን ከእንግዲህ አይሰራም እናውቅልሃለን የሚሉ ሊሂቃን አንዴ ንጉስ፥ አንዴ ፕሬዚዳንት፥ አሁን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እያሉ መንግስት መሰረቱ። የለውጥ አየር እየነፈሰለት እፎይታን በማጣጣም ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእሳት ተፈትኖ አዋቂ የሆነ ነውና፥ ዛሬ ላይ ቆመን ቀንበር እንደ በፊቱ ባናሸክመው መልካም ነው። ጊዜውን የሚመጥን አካሄድ በመከተል ሕዝቡ መሪዉን ብቻ ሳይሆን የመንግስቱን ዓይነት /system/ጭምር እንዲመርጥ ቢደረግ የሚመሰረተው መንግስት የሕዝብ መንግስት ለመሆኑ ዋስትና በመስጠት ያፀናዋል። ሊሂቃን የትኛው እንደሚበጅ በየፊናቸው ጥናታቸውንና አመለካከታቸውን ለሕዝብ በውይይትና በክርክር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከዚያ ባለፈ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቃት ባገናዘበ ሁኔታ፥ እኛ እናውቅልሃለን ብለው ከመወሰን ተቆጥበው፥ ፍርዱን ለሕዝብ እንዲተው ለሂሊናቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ይህን አዋቂና ትልቅ ሕዝብ በማክበር ሕዝቡ ያለው እንዲሆን ውሳኔውን ለሕዝብ ይለቃሉ የሚል እምነት አለኝ። 2ኛ/ ሕገ መንግስቱን ማስታመም ሕገ መንግስቱ ተዐማኒ እንዲሆን ሕዝብ በመረጠው ሞግዚትነት ይፈተሽ ዘንድ ይገባዋል። ስለዚህ የሕዝብ መንግስት እስኪኖረን ድረስ ወደድንም ጠላንም በዚህ ሕገ መንግስት ታስረናል። ዝም ብለን በዚህ ሕገ መንግስት ደግሞ ወደ ምርጫው እንዳንሄድ የሕዝብ መንግስት ለመመስረት ብቃት አይሰጠንም። ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ ምርጫውን በተመለከተ ሕገ መንግስቱ ይፈታን ዘንድ ማሻሻያ ማድረግ የግድ ነው። ይህን የምርጫ ማሻሻያ ለማድረግ ደግሞ ያለው ፓርላማ አሁንም የሕዝብ ስላልሆነ (በሀቀኛ ምርጫ) ውሳኔ ሊያስተላልፍልን አቅም የለውም። ስለዚህ ሕገ መንግስቱን የማሻሻያ አውድ ሕዝቡ ራሱ እንዲሰጥ የመንግስትን ዓይነት ለመወሰን (ፕሬዚዳንት ወይስ ጠ/ሚኒስቴር) የሚለውን እንዲረዳ ይህን ሪፈረንደም ማድረግ የሕዝብን መንግስት ለመውለድ ተዐማኒነት ይሰጣል። 3ኛ/ ሁሉ አቀፍ መግባባት ወሳኝ ነው ዶ/ር አብይ እንደ ሽግግር መንግስት ለማገልገል አሁን አይችሉም። በአሁን ወቅት ተልዕኳቸው የዲሞክራሲ አዋላጅ መሆን ብቻ ነው። ከአምባገነንነት ወደ ሕዝብ መንግስትነት የሚያሻግረን በመጀመሪያ ምርጫ የሚመሰረተው የሕዝብ መንግስት ነው። የመጀመሪያ የሕዝብ መንግስት ለወደፊቱ መሰረት የሚጥል፥ ሕገ መንግስቱን ሕዝባዊ የሚያደርግ፥ አሻጋሪ መንግስት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ምርጫ ወደፊት ከምናደርጋቸው ምርጫዎች የተለየና ፈር ቀዳጅ ነው። ስለዚህ ወደዚህ በዓይነቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዋላጅ ወደሆነው ምርጫ ስንሄድ ከሞላ ጎደል ሁሉ አቀፍ መግባባት መኖር አለበት። ለምሳሌ ፕሮፌሰር መራራ ምርጫ እንዳይራዘም ሲሉ፥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሊራዘምም ይችላል ሲሉ ይታያሉ። ሁለቱም የተፈተኑ ንፁህ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ ልባቸው ለኢትዮጵያ ደህንነት እንዲሆን በማለት ብቻ ይህንን ተቃራኒ አሳብ ያነሳሉ። ታዲያ ሪፈረንደም በሚደረግበት ጊዜ፥ ለዋናው ምርጫ ግብሃት የሚሆን መረጃ /data/ በሁለቱም ጎራ ለተሰለፉ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ይኖራቸዋል። ሪፈረንደም ሲደረግ የምናየሁ ሁኔታ ምርጫውን ለማድረግ መቼ መቻልን እንደምናገኝ ፍንጭ በመስጠት መግባባት ላይ ያደርሰናል። 4ኛ/ እንከን የለሽ ምርጫ የግድ ነው ከዚህ በፊት እንደጠቀስኩት የመጀመሪያው ምርጫ የተለየ ነው። እንከን የለሽ መሆን ያለበትና ውዝግብ የማያመጣ ፍፁምነትን የተላበሰ ምርጫ ማካሄድ እንዳለብን ለድርድር አይቀርብም። ታዲያ ከዚህ በፊት የተደረጉት ምርጫዎች ውሸት ስለነበሩ የምንማርበት ሆነው አይጠቅሙንም። ሪፈረንደም ብናደርግ ግን፥ ለወሳኙ ምርጫ መማሪያና ወደፊት ምርጫም ሲደረግ እንከን የለሽ እንዲሆን ቀደም ተብሎ ማስተካከያ ለማድረግ ዕድል ይሰጣል። ሪፈረንደም ማድረጉ ከታለመለት ዓላማ ተጨማሪ ድምፅ የመስጠት ልምድ የምንቀስምበትና ራሳችንን በብቃት ለምርጫ የምናበቃበት አድማስ ያሰፋልናል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሰበ። ይጎበኛታልም። Email: [email protected] Zelalem Eshete, Ph.D.
I never thought there would come a time where would I admire an Ethiopian prime minister over a United States president. It is a strange time. President Trump is stripping away inherited ideals that long existed in United States while PM Dr. Abiy Ahmed is instilling ideals in Ethiopia that didn’t exist in the first place. United States is founded upon timeless ideals. Yes, there is prejudice and racism but that doesn’t speak to America as a whole. Instead, that can be attributed to the fallen state of humanity. America has been on a journey to enlighten and deal with such ignorance. That progress is the beauty of America, one victory at a time. That is why America is an inspiration for the world, and a sanctuary for the persecuted. America’s soul speaks of such priceless identity. Now the president single handedly undermines those ideals to re-invent America and in doing so, he is making America lose her soul. It is an oxymoron for an immigrant president (albeit his ancestors) to turn around and label Mexicans that aspire to come here as drug dealers and criminals. Ensuring legal immigration through secure borders is a noble thing, but dehumanizing immigrants to sell his agenda by holding the united states hostage is insane. When the highest office in the land debases the ideals of America, it is an American identity crisis. Being the super-power of the world or the super-rich of the world is meaningless and short lived unless one can be the super model of the world. There have been many rises and falls of civilization in history: Axum, Egypt, Athens, Rome, Great Britain. America is not meant to join this list. America’s soul dictates that America will keep herself from the fall through wisdom and understanding. At the time wisdom and understanding is a hard commodity in the White House, we need to look for guidance at the faraway, unlikely place known as a “dark continent” (what the president calls “shit hole countries”). There, we find Ethiopia: grabbing the imagination of not only Ethiopians but Africans and the world at large. PM Abiy Ahmed espouses regional integration and openness to the world. He champions Ethiopianism within the context of “medemer” (coming together). His “love wins” philosophy had the power to end the twenty-year hostility with Eritrea, practically overnight. All political prisoners have been set free. All parties have put their arms to rest and are roaming Addis Ababa in freedom. Every morning, the impossible is becoming possible. There is distinct joy and aura of hope in the air. What has enabled each of these historic changes is one and the same: the fact that PM Dr. Abiy Ahmed is instilling timeless ideals for Ethiopia. That is what makes or breaks a nation. Zelalem Eshete, Ph.D.
Ethiopia is extremely diverse but intertwined. We think we have only two choices: either to stress unity at the expense of diversity or major on diversity neglecting unity. But we have a third way: Foster diversity on the foundation of building unity. This short article is about how this nation building can be realized. In the process, it makes a case for the rebirth timing of Ethiopia in three phases. The efforts undertaken by the PM Dr. Abiy to meet the 2020 election deadline is admirable. But building institutions that ensures fair and true elections is only a necessary condition, but not sufficient condition. There is more at stake. Initial Condition – the Power of Choice – rebirth of a People anew Where to begin? We can start implementing the indigenous world view coined by PM Dr. Abiy Ahmed: “በፍቅር ተደምረን በይቅርታ እንሻገር”. This demand resorting to the power of choice, motivated by proactively envisioning the Ethiopia we all aspire to have become. To this end, we need to articulate and formulate this world view in a way that invades our everyday lives. It requires focused efforts by the Ethiopian elites to expound this idea and lay out the foundation for its realization. Then implementation of its mandate with utmost excellence follows. This work can be the bedrock of the unity-foundation by initiating the healing process and bringing out our inherent unity to the light. This need TIME. Consensus Building – the Power of Democracy – rebirth of a Nation anew We build consensus by the help of democracy that enhances the progress of nation building. We need to accomplish two main prerequisites for the success of nation building under the auspices of democracy. First, imagine three or four political parties based on IDEAS providing alternative platforms for the people. Then the people can find clarity in the choices available for the direction Ethiopia needs to take. We have an opportunity for real practice of democracy in our land, and this first step is what makes democracy work. This need TIME. Second, we need informed citizens to make democracy grow. The media and the system need to be fair and equitable for all competing parties including the government. More than just having the means in place though, once the three or four parties are formed, they need to get their ideas out to the people and provide a forum for creating evolving ideas. This need TIME. National Election – the Power of We the People – rebirth of a State anew The state formation through the next national election is unlike any in the history of Ethiopia. It is unique, in that it is going to be the first ever state formation through democracy to highlight the government by the people and for the people. Therefore, it is very sacred. It cannot be rushed. It cannot be compromised. More than anything, it has to be done right. To do it right, the first two tasks mentioned above needs to be realized. This first state formation cannot happen in a vacuum. The people have to vote with their heart for Ethiopia first to lay the background for unity-foundation through the power of choice stated earlier under the umbrella of “በፍቅር ተደምረን በይቅርታ እንሻገር”. Then the people need to have real choices to cast the ballots, that necessitate three or four parties. And the people need to be informed and take part in shaping the ideas proposed by these parties. All these to say, this next election is special, and more is involved than just making sure the election is true and fair. In light of having a Prime Minister who is devoted to democracy and has the approval of the people of Ethiopia, why on earth one rushes election only to abort the miracle-chance bestowed on us from the heaven to spotlight the other face of Ethiopia: To Be Known As We Truly Are, a beacon of hope for the world, and a sign of African pride? The writer can be reached via email at: [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ግሩምና ድንቅ የሆነ አማራጭ የኢትዮጵያ ፓርቲ እንዲወለድ እስካሁን የሚታይ አንድ ምዕራፍ ፈቀቅ አለመባሉ ያሳዝናል። ተስፋ በተቆረጠበት ወቅት ላይ ቆመን ሳለን፥ ዶ/ር አብይ ብቅ ብለው ላለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተአምር አሳዩን። ዛሬ ደግሞ ይህንን ለውጥ ዳር የሚያደርስ አደራ ተቀባይ ፓርቲ ጠፍቶ፥ በስጋት ጨለማ ባለንበት በአሁኑ ሰዓት፥ ብርሃን የሚፈነጥቅ ባለ አደራ ታሪካዊ ፓርቲ ተቀናጅቶ በምድራችን ብቅ ብሎ የሚያስገርመን መቼ ነው? በድህረ ዶ/ር አብይ ጊዜ መሠራት ያለበትን ሥራ፥ ዛሬ ዶ/ር አብይ ካልሰሩ ብሎ ከማዋከብ፥ ዓይናችንን ከእርሳቸው ላይ እናንሣና ወደ የራሳችን ስራ እንግባ። ዶ/ር አብይ ለሁላችንም ዲሞክራሲን አዋልደው፥ ፈረሱም ይሄው ሜዳውም ይሄው ከማለት ያለፈ ሃላፊነት የለባቸውም። ምክንያቱም ፓርቲያቸው ሊሰራው የሚችለው ዕጣና ፈንታው ሽግግር መሆን ብቻ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው ፓርቲያቸው ሲጀመርም ለተስፋይቷ ኢትዮጵያ እንዲመጥን ተደርጎ ስላልተሰፋ ነው። በዚህ ምክንያት ትልቁ አንገብጋቢ ቁምነገር አንድ ብቻ ነው። ያም ዲሞክራሲ ኢትዮጵያን ሲያሻግር፥ የተስፋይቷ ኢትዮጵያ አደራ ተቀባይ የሚሆን ተቀናጅቶ የጊዜው ፓርቲ ለመሆን የሚችል መገኘቱ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ የዲሞክራሲ አዋላጅ ለመሆን ታሪክ የጠራቸው ሰው ናቸው። ያንን ጥሪያቸውን ከብቃት በላይ በመወጣት ላይ ይገኛሉ። ያመጡትን ዲሞክራሲ ተጠቃሚ እየሆንን፥ ነገር ግን በዚህ ዲሞክራሲ ምክንያት የሚከሰተውን ውጣ ውረድ እንደ እርሳቸው ድካምና ችግር መቁጠር ነውር ነው። ዲሞክራሲና ነፃነትን ማስተናገድ መቻላችንን ማሳየት የሁላችንም ሃላፊነት ነው። የማያግባቡን ነገሮች ቢበዙም፥ በሥራ የሚተገበረው ሀሳብ፥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዳኝነት የሚመረጥ ስለሆነ ዲሞክራሲ ፍቱን መፍትሄ ነው። ያም ሆን ይህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በዲሞክራሲ እየደመቀ ይሄዳል እንጂ አይደበዝዝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጠባቂ ከአምላክ በታች የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ስለሆነ ነው። ተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ዶ/ር አብይ የተጫነባቸው ዓይነት የኢህአዴግ ቀንበር የለባቸውም። በዚህም ምክንያት ለተስፋይቷ ኢትዮጵያ ለመታጨት ነፃ ናቸው። ነገር ግን የኢህአዴግን አጀንዳ እያራመዱ ከኢህአዴግ የተሻለ ፓርቲ ነኝ ብሎ መንቀሳቀስ ከእውነት ስለሚርቅ አይጠቅምም። ከኢህአዴግ የተሻለ ፓርቲ ለመሆን ዜግነትን አማክሎ መነሳት ይጠይቃል። ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ በይዘትም ሆነ በህልውና ልዩና የላቁ መሆን አለባቸው። ለአሮጌ አስተሳሰብ ያረጀው ፓርቲ ምናለና። ዶ/ር አብይ የዲሞክራሲ መንገዱን በትጋት እየጠረጉ የራሳቸውን ሃላፊነት እየተወጡ ይገኛል። ለዚህም የውጭ ሀገር ዜና ሳይቀር በማድነቅ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ደግሞ በመንገዱ ላይ የሚሄድ አማራጭ የኢትዮጵያ ፓርቲ ባቡር በመጠበቅ ላይ ትገኛለች። ጥያቄው ሌሎቻችን “ቅንጅት” ዳግም እንዲወለድ ምን ያህል ድርሻችንን እየተወጣን ነው? ፈጣሪ ይርዳን! Zelalem Eshete, Ph.D.
If we can’t accept each other as our own kind, based on the common denominator that we are all the same human beings, it is easier for us to be inhumane and do inhumane things to each other. We are all guilty and we take responsibility for our actions and inactions. Now, we all start to see each other as ones created in the image of God. There is no better honor for us to be identified than being known as God’s image bearer. I write this letter to those Oromo elites who have difficulty saying and meaning Ethiopia. I want to make a case for their need for a transformed heart to see and reflect the beauty of Ethiopia, which comprises more than 80 ethnics with nothing but grace and love in their beings. The fight among elites need to give way to the reality of the 100 million people who have a heart to see each other as beloved family. The Oromo elites are now on sacred ground to rise up to the destiny heaven has bestowed in the name – Oromo. ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የሕዝብ መንግስት ለመመስረት ምርጫ ከማድረግ በፊት መንግስት የሚያስተዳድራት ሀገር ትወለድ። አሁን ያለን “ሀገር” ለቅርጫ ቀርባ ሁሉም ጎሣ ድንበሩን ለማስከበር ጦር እየመዘዘና ያልመዘዘው ለመምዘዝ አድፍጦ ጊዜ እየጠበቀ ነው።በቀረን ሁለት ዓመት ምርጫ ለማድረግ ከተነሳን፤ ሀገር እንድትወለድ መሰራት ያለበት ሥራ ለመስራት አንድ ቀን እንኳን ላይኖረን ነው። ባለ ሀገሩ ሀገር ሳይኖረው ንጉሶችን መምረጡ ምን ይፈይድለታል?ንጉሥ ለመሆን አራራ ያለው ካልሆነ በቀር፤ በሕዝብ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት ያለውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀገርን እንዲያዋልዱ መተባበር ትልቅ ክብር ነው። ሀገሪቷ በጎሳ ተሸንሽና ሰላም ቢገኝ ኖሮ ሸንሽኖና ተለያይቶ መገላገል ይቻል ነበር። ግን ብዙ ንጉሶችን ፈጥሮ እርስ በርስ ያባላን እንደሆነ እንጂ መቼም ቢሆን የሰላም እንጀራ ልንበላ አንችልም። ምክንያቱም ተደበላልቀን ስናበቃ አሁን እንዴት ተሸንሽነን በድንበር ልንስማማ እንችላለን? የተደባለቅነው ወረቀት በእስፒል እንደተያያዘ ዓይነት ሳይሆን ወረቀት በሙጫ የተያያዘ ያህል ነው። በሙጫ የተጣበቁ ወረቀቶችን መለየት ፍዳ ነው። ከተሞከረ ደግሞ ሁሉም ይበጣጠሳል። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
አዲስ የኦሮምያ ካርታ ማውጣት የጊዜው መልስ ነውን? ፍቅር እንዲያሸንፍ ክርስቶስ ሰማይን ትቶ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ። ያለዋጋ ፍቅር ሊያሸንፍ አይችልም። ስለዚህ ፍቅር በምድራችን እንዲያሸንፍ፤ ሁላችንም ከቡድንተኝነት አስተሳሰብ ወጥተን፤ ለጋራ ኢትዮጵያዊነት ልዕልና መኖር እንድንችል መያያዝ መቻል አለብን። ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን የተባለው ትልቅ አባባል ነው። ስንኖር ኢትዮጵያዊ ነን ከማለታችን በፊት ግን ለግላዊ ቡድንተኝነት መሞት ያስፈልገናል። ኢትዮጵያዊነትን ለመኖር ከፈለግን፤ ከተከፋፈልንበት አጥር ወጥተን መያያዝ መቻል የግድ ይላል። ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊነትን በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ብቻ የምናወራው ነገር እንጂ፤ የምንኖረው የሕይወት ዘይቤ ሊሆን አይችልም። |