ላዕከ ታፈሰ
እረ ለመሆኑ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ “እንካ” ሞቶ ተቀበረ እንዴ? ፍቅርስ ማለት ባዶ የቃላት ጫጫታ ነው እንዴ? በየቦታው ወገኖቻችን እየተገደሉና እየተፈናቀሉ ናቸው:: ምነው ሀብታሞች: የሐይማኖት ተቋማት: የፖለቲካ መሪዎች: የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እጃችሁ ታጠፈ: ልባችሁ ጨከነ? የዶ/ር አቢይን የይቅርታና የፍቅር መልእክትን ወድጀዋለሁ: የእርሱን አመራር እደግፋለሁ ያለ ሁሉ ፍቅሩንና ይቅርታውን ማሳያ የሆኑት ወገኖቹ ሲቸገሩ ለምን ዝም አለ? ደጉ ሳምራዊነት በህግ ተከልክሏል እንዴ? ወይስ ሃላፊነቱ የክልልና የፌዴራል መንግስት ነው? ወይስ መንግስት መረዳዳትን ወንጀል ነው ብሎ ፈርጆታል? ወደ ቤተክርስቲያንና መስጊድ በየቀኑ የሚሄደው የኢትዮጽያ ህዝብ ከዚያ ሲመለስ ሌላውን መግደልና ማፈናቀልን ከማን ተማረው? የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወይ ፈጣሪህ የሚልህን ታዘህ የሰውን ልጅ በእኩልነት መመልከትና በተግባር መውደድህን አሳይ:: እሱንም ካልቻልክ የይስሙላ እምነትህን ትተህ የአገራችንን ህግ አክብር:: ዶ/ር አቢይ “ፓወር ፖይንት” አዘጋጅና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ መደመር: ይቅርታና ፍቅር ምን ማለት እንደሆነና ከእንግዲህ እያንዳንዱ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት: አንተም ከኛ ምን እንደምትጠብቅ እባክህ ንገረን:: ይህን በቶሎ አድርግልን:: ብዙ ሰው ይደግፍሃል እንጂ ፍልስፍናህን አልተረዳልህም ብዬ አምናለሁ::
1 Comment
Good Point. And hope leaders in the faith community take this observation to actton soon.
Reply
Leave a Reply. |
AmharicArchives
November 2018
Categories |