myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

ይድረስ የፈጣሪን ስም ለጠሩ ለዶ/ር አብይ አህመድ

4/26/2018

0 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
በ 44 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መሪ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ “ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”  እያሉ ንግግርዎን ሲያሳርጉ አይቶ ሕዝበ ኢትዮጵያ በደስታ ተሞልቷል። እኔ ግን እያሉ ያሉት ይህ የማሳረጊያ ቃል በሕዝብ ፊት ብቻ ሳይሆን በአምላክ ፊት ምንና ምንን በሃላፊነት ሊያስጠይቅዎ እንደሚችል የነገሩ ክብደት እጅግ አሳስቦኛል።

የፈጣሪ ስም ከተነሳ ዘንዳ፥ ይህ ፈጣሪ የሚሰጠን በረከት ምንነት ይታወቅ ዘንድ ያስፈልጋል። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” ሲባል ዝንተ አለም አሳልፈን ዛሬን ደረስን። እስከ ዛሬ “ትዘረጋለች” ከማለት አልፈን “ዘረጋች” ወደማለት ሳንሸጋገር ሦስት ሽህ ዓመታት ጠበቅን። በዚህ ፅሁፌ ይህ 3000 ዓመታት ያስቆጠረው ትንቢት ተፈፀመ የሚያስብለው ሁኔታ ምን እንደሆነና፤ የፈጣሪን በረከት የጠየቁት እርስዎ ስለዚህ በረከት ሊኖርዎት የሚገባውን ግንዛቤ ለመጠቆም እሞክራለሁ። የዚህ ጉዳይ ተጠያቂነት ሁላችንንም የሚመለከት ስለሆነ የኛን ድርሻም ለማመላከት እሞክራለሁ።

Read More
0 Comments

VOA Interview: የአዋላጅነት ጉዳይ

4/18/2018

0 Comments

 
0 Comments

ዘብ ቆመናል ክቡር የኢትዮጵያ ልጅ ዶ/ር አብይ አህመድ

4/10/2018

0 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ሁላችንም ካለንበት አጣብቂኝ ውስጥ መውጫ መንገድ አጥተን ተፋጠን ሰንብተናል። ስንነካከስ እንዳንጠፋፋ በሚያስፈራበት መልኩ ሁላችንም ግብ ግብ ስንገጥም እዚህ ደረስን። መንግስት በጉልበቱ ሲገፋበት፥ ሕዝብ በአመፁ ሲዘልቅበት፥ አማራጭ ኃይል በሁሉ አቀፍ ትግሉ ሲዘምትበት፥ አካሄዱ ሁሉ ሲያስፈራ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ያሰኝ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ ወደ አምላኩ ከመጮህ አልተቆጠበም። በአራቱም አቅጣጫ አንድነቷን እና ብልጽግናዋን በማይወዱ የተከበበች ሀገር ሆና ሳለ፥ ከውስጥ ደግሞ በነውጥ ስትናጥ ተስፋዋ እየመነመነ ጫፍ ደርሶ ነበር። ምን አልባት ታዲያ የማታ ማታ ፈጣሪዋ ኢትዮጵያን ከምጥ ሊገላግላት፣ ውጥረቷን አርግቦ ሰላምን ሊሰጣት አስቦ ይሆን ዶ/ር አብይ እርስዎን ወደ አመራር ያመጣዎት? ካለንበት አጣብቂኝ ለመውጣት ረዥም መንገድ መሄድ እንዳለብን እሙን ነው። ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ ዘብ በመቆምና እኛም ለእርሳቸው ዘብ በመቆም ይህን የተስፋ ጭላንጭል ጠላት እንዳያጨናግፍ ሁላችንም የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል። አሁን ከፊታችን የተደቀነው ወሳኝ ሰዓት እኛ ተመልካች ሆነን፥ ዶ/ር አብይ ደግሞ በፊታቸው ያለውን ፈተና ያልፉ እንደሆነ ለማየትና ብያኔ ለመስጠት በጥርጥር ዓይን የምንመለከታቸው አይደለም። ወይንም እኛ ሁላችን እሳቸውን የምናዋክብበት ጊዜ አይደለም፤ ነገር ግን እኛም ሆንን እሳቸው የመፍትሄው አካል ከመሆን እንዳንጎድል የምንጠነቀቅበት ጊዜ ከምን ጊዜውም በላይ አሁን ነው።

Read More
0 Comments

ተስፋና ስጋት

4/4/2018

0 Comments

 
0 Comments

ግልፅ ደብዳቤ ለተከበሩ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

4/1/2018

0 Comments

 
ከዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ሰሚ ያጣ ሕዝብ ብዬ የፃፍኩት ትዝ ይለኛል። ጆሮ ያለው ይስማ ብዬ የፃፍኩትም የእርስዎን ምርጫ በመመኘት ነበር። ዛሬ ፓርቲዎ ኢሕአዴግ ሕዝብን የመስማት አገልግሎት ለመጀመር እርስዎን በጠ/ሚኒስቴርነት መሾሙ ድንቅ የሚያሰኝ ነው። ከጦረኛ መንግስትነት ወደ አዋላጅ መንግስትነት መሸጋገር የእርስዎ ብቸኛ ትኩረትዎ እንዲሆን ማስተዋል እንዲበዛልዎት እመኛለሁ። አብዮት ከመወለዱ በፊት ኢትዮጵያ እንደገና እንድትወለድና ሁላችንም በእኩልነት የምንኖርበትና በዲሞክራሲ የምንዳኝበት አዲሲቷን ኢትዮጵያ ዕውን በማድረግ መንግስትዎንና ሀገራችንን ከጉድ ለማትረፍ ጥሪዎን እንዲወጡ ፀሎቴ ነው።  አዋላጅ መንግስት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ በታች ለማስረዳት እሞክራለሁ።

Read More
0 Comments
    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል