myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

ሳይጠየቅ የቀረ ጥያቄ ለዶ/ር አብይ

7/29/2018

1 Comment

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
በዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝትዎ ብገኝም፤ ነገር ግን ዕድል አግኝቼ ልጠይቅዎት ያልቻልኩትን ጥያቄ ምናልባት ፈጣሪ ፈቅዶ ለጆሮዎ ይደርስ ይሆናል ብዬ ይህን ለመፃፍ ተነሳሳው። ጥያቄዬ የሚያጠነጥነው በአመፅ ተፀንሶ፤ በፍቅር የተወለደው ይህ የለውጥ ጅማሬ እንዴት እናስቀጥል እንችል ይሆናል ከሚል ጭንቀት ውስጥ የወጣ ነው። ሁላችንም በእርስዎ ድንቅ አመራር፥ የፍቅርና ትህትና አካሄድ ተማርከን የዛሬው ደስታችን ላይ አተኩረን በታላቅ ደስታ ላይ ነን። ግን ይህ ምናልባት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብቸኛውና የመጨረሻው ዕድል ሊሆን እንደሚችል እየተገነዘብን ከሚያንዣብበው አደጋ ለማምለጥ ለስህተት አንዳች ፈንታ እንዳይኖር ሁላችንም እርስዎን ጨምሮ ራሳችንን መፈተሽ የዕለት ዕለት ተግባራችን ሊሆን ይገባዋል።

Read More
1 Comment

ብቻውን ታምራት የሚያደርግ ይመስገን!

7/11/2018

0 Comments

 
Picture
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
"ኢትዮጵያ ትጠየቅ" በሚል ርዕስ የዛሬ ሁለት ዓመት የፃፍኩት ፅሁፍ ከዚህ በታች ይገኛል። ፈጣሪ የሰራውን ተዐምር እያሰብን እናመስግን። ደግሞም ገና በአምላክ ስር ያለን አንድ ቤተሰብ እስኪያረገን ድረስ ማመናችንን አንተውም!

የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው?
  • ሕዝቡ ነው።​

Read More
0 Comments

ሀገር በቀል አዲሱ የኢትዮጵያ ርዕዮተ ዓለም

7/10/2018

0 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ፍቅራቸው የነካው ሽህ ዓመት ንገሱ ሲላቸው፤ ሌላው እንዴት መንግስት ይሸጋገራል ብሎ ሲያወጣና ሲያወርድ፤  ሌላኛው ደግሞ አምባገነን ስርዓት እየመጣ ነው ብሎ ሲቃወም ይታያል። ለማያስተውል ሰው የዶ/ር አብይ መንግስት ወዴት ይሄድ ይሆን ብሎ ግራ ሊገባው ይችላል። ለእርሳቸው በቂ ጊዜ ተልዕኳቸውን በሚመጥን መልኩ እንዲመሩን ዕድል እንስጥ። ይህ የእርሳቸው አመራር የለመድነው ፍሬ አልባ የሽግግር መንግስት ሲባል ያየነው ዓይነት አይደለም። የፅሁፌ ጭብጥ ሀሳብ፤ ይህ የእርሳቸው መንግስት ያልነበረ፥ ወደፊትም ሊኖር የማይችል፤ በዓይነቱ በዓለም የመጀመሪያው የሆነ የአዋላጅ መንግስት ስርዓት እንደሚሆን ላስረዳ እሞክራለሁ። ከዚያ በሁዋላ የሐቅ ምርጫ ዳኛ ይሆንልናል። ዶ/ር አብይ የአንድ መሪ በስልጣን ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከሁለት ምርጫ በላይ መሆን የለበትም ያሉት ያኔ ሕግ ስለሚሆን ሀሳብ አይግባን።

Read More
0 Comments

አደራ ዶ/ር አብይ፥ ከዲያስፖራ

7/7/2018

0 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
የሚወድዎትና እርስዎም የሚወዱት ዲያስፖራ ጋር ለመገናኘት፤ በመካከል ያለውን ፈተና አምላክ እንድንወጣ ያስችለናል ብዬ አምናለሁ። በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ባለው በኢትዮጵያ ቀን ላይ ተገኝተው ሊያዩን ቢፈልጉም አምላክ ስላልፈቀደ አልተሳካም። ሁላችንም እንደ አንድ ሆነን እርስዎን ለመቀበል እየፈለግን ሳለ፤ ግን ስለ መምጣትዎ በሚደረገው ዝግጅት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ መሰናክል እንዳይኖር ጥንቃቄ እናደርግ ዘንድ ይገባል። የእርስዎ መንገድ የተዋጣለት እንዲሆን ሁላችንም ለክቡርነትዎ ዘብ እንቁም።

Read More
0 Comments

ሕወሓት ይሻገር

7/3/2018

0 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
የኢትዮጵያ አምላክ ስጦታ የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ የተነሱለት ራዕይ ከእኛ ኢትዮጵያውያን ተርፎ ለአፍሪካም በረከት የሚሆን ጭምር ነው። ፈጣሪ የሕዝብን የዘመናት ልመና ሰምቶ፤ ዛሬ በፍቅር ደስታ ተዐምር በሚያሰኝ ሁኔታ መላውን ሕዝብ አንድ እያደረገ ይገኛል። እኚህ ሰው ዲሞክራሲን አዋልደውና የአፍሪካን አንድ የመሆን ራዕይ ፈንጥቀው ከስልጣናቸው ዞር የሚሉ “ጉደኛና ታሪከኛ” መሪ እንጂ፤ አምላክ የሰጣቸውን የማያልፈው የኢትዮጵያ አባትነት ክብር፥ ለሚያልፈው የስልጣን ጥማት የሚሸጡ አይመስለኝም። ስለዚህ እኚህን የፍቅር ስብዕና የተካኑትን ጠ/ሚ፤ ለሁሉ ፍቱን መድሃኒት የሆነውን ተወዳጅ የመደመር አስተሳሰብ ማደናቀፍ በታሪክ የማይሽር ጠባሳ በራስ ላይ ያመጣል። ይህ ዓይነት ጠባሳ ኢትዮጵያዊ በሆነ ሁሉ ላይ እንዳይመጣ ሁላችንም የቻልነውን ያህል የማሻገር ስራ እንድንሰራ እንነሳሳ።

Read More
0 Comments
    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል