myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

ብቻውን ታምራት የሚያደርግ ይመስገን!

7/11/2018

0 Comments

 
Picture
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
"ኢትዮጵያ ትጠየቅ" በሚል ርዕስ የዛሬ ሁለት ዓመት የፃፍኩት ፅሁፍ ከዚህ በታች ይገኛል። ፈጣሪ የሰራውን ተዐምር እያሰብን እናመስግን። ደግሞም ገና በአምላክ ስር ያለን አንድ ቤተሰብ እስኪያረገን ድረስ ማመናችንን አንተውም!

የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው?
  • ሕዝቡ ነው።​
ታዲያ በሕዝቡ ስም (ኢትዮጵያ) ጥላ ስር መሪዎቻችን ሁሉ የማይሰባሰቡት ለምንድነው?
  • የታሪክ እስረኛ ሆነን በር በሌለው ጨለማ እስር ቤት ውስጥ በመታለል ቁጭ ስላልን።
  • ኢትዮጵያን መነሻ ሳናደርግ ኢትዮጵያ መድረሻ እንድትሆንልን ተመኝተን ጉም ስንጨብጥ።
  • ክልላችንን (አጥሩን) አፍርሰን እንዳንያያዝ አጥሩ ጎልያድ ሆኖብን ፍርሀት ስለሞላብን።
ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ምንድነው? 
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የጭቆና ሰለባ ሆኗል።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ደግና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ነው።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የተደባለቀና አብሮ ለዘመናት የኖረ ነው።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ተባብሮ ታግሎ መንግስታትን ጥሏል።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ተባብሮ ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆኗል።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ አንድነታቸውን ዛሬም እያንፀባረቁ ነው።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ሰብሳቢ ያጣ ቤተሰብ ሆኖ ተቸግሯል።
ሁሉም የሚገርመው የመሪዎች አባዜ ምንድነው? 
  • መንግስት ከፋፍሎ ይገዛል። ስልጣኑ ጥሞታል።
  • ተቃዋሚ ተከፋፍሎ ይታገላል። ለስልጣን ቋምጧል።
የሚገርመው እውነታ ምንድነው? 
  • እግዚአብሔር በተአምራቱ እስካሁን ብቻውን አንድነቷን እየጠበቀ ነው።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን በራሱ እያስተዳደረ ነው።
እግዚአብሔር አዲስን ነገር የሚያደርግበት ዘመን ሲመጣ የሚሆነው ምንድነው? 
  • ልጆቿ አጥርን እያፈረሱ ይያያዛሉ።
  • ምህረትና ፍትህ ይሳሳማሉ።
  • ቁርሾ በፍቅር ይሟሟል።
  • እውነት በእውን ይሰምራል።
  • አሮጌውን ክፉ ታሪክ የሚያስረሳ አዲስ ታሪክ ይሰራል።
  • ልትሞት ነው የተባለችው ኢትዮጵያ በትንሳኤ ትነሳለች።
  • የኢትዮጵያ እናትነት እንደ ንጋት ጮራ ብርሃኗ ይወጣል።
I am not Ethiopian first. 
I am not Ethiopian second.
I am Ethiopian.
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ተፃፈ Oct 16, 2016
0 Comments



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል