myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

Open Letter to those Oromo Elites

8/17/2018

0 Comments

 
Zelalem Eshete, Ph.D.
If we can’t accept each other as our own kind, based on the common denominator that we are all the same human beings, it is easier for us to be inhumane and do inhumane things to each other.  We are all guilty and we take responsibility for our actions and inactions.  Now, we all start to see each other as ones created in the image of God. There is no better honor for us to be identified than being known as God’s image bearer. 

I write this letter to those Oromo elites who have difficulty saying and meaning Ethiopia.  I want to make a case for their need for a transformed heart to see and reflect the beauty of Ethiopia, which comprises more than 80 ethnics with nothing but grace and love in their beings.  The fight among elites need to give way to the reality of the 100 million people who have a heart to see each other as beloved family.  The Oromo elites are now on sacred ground to rise up to the destiny heaven has bestowed in the name – Oromo. 


Read More
0 Comments

ከምርጫ በፊት ሀገር ይኑረን

8/12/2018

2 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
የሕዝብ መንግስት ለመመስረት ምርጫ ከማድረግ በፊት መንግስት የሚያስተዳድራት ሀገር ትወለድ። አሁን ያለን “ሀገር” ለቅርጫ ቀርባ ሁሉም ጎሣ ድንበሩን ለማስከበር ጦር እየመዘዘና ያልመዘዘው ለመምዘዝ አድፍጦ ጊዜ እየጠበቀ ነው።በቀረን ሁለት ዓመት ምርጫ ለማድረግ ከተነሳን፤ ሀገር እንድትወለድ መሰራት ያለበት ሥራ ለመስራት አንድ ቀን እንኳን ላይኖረን ነው። ባለ ሀገሩ ሀገር ሳይኖረው ንጉሶችን መምረጡ ምን ይፈይድለታል?ንጉሥ ለመሆን አራራ ያለው ካልሆነ በቀር፤ በሕዝብ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት ያለውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀገርን እንዲያዋልዱ መተባበር ትልቅ ክብር ነው።
 
ሀገሪቷ በጎሳ ተሸንሽና ሰላም ቢገኝ ኖሮ ሸንሽኖና ተለያይቶ መገላገል ይቻል ነበር። ግን ብዙ ንጉሶችን ፈጥሮ እርስ በርስ ያባላን እንደሆነ እንጂ መቼም ቢሆን የሰላም እንጀራ ልንበላ አንችልም። ምክንያቱም ተደበላልቀን ስናበቃ አሁን እንዴት ተሸንሽነን በድንበር ልንስማማ እንችላለን? የተደባለቅነው ወረቀት በእስፒል እንደተያያዘ ዓይነት ሳይሆን ወረቀት በሙጫ የተያያዘ ያህል ነው። በሙጫ የተጣበቁ ወረቀቶችን መለየት ፍዳ ነው። ከተሞከረ ደግሞ ሁሉም ይበጣጠሳል። 

Read More
2 Comments

​ፍቅር እንዲያሸንፍ ከራስ መውጣት ያስፈልጋል

8/9/2018

2 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
አዲስ የኦሮምያ ካርታ ማውጣት የጊዜው መልስ ነውን?
 
ፍቅር እንዲያሸንፍ ክርስቶስ ሰማይን ትቶ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ።  ያለዋጋ ፍቅር ሊያሸንፍ አይችልም።  ስለዚህ ፍቅር በምድራችን እንዲያሸንፍ፤ ሁላችንም ከቡድንተኝነት አስተሳሰብ ወጥተን፤ ለጋራ ኢትዮጵያዊነት ልዕልና መኖር እንድንችል መያያዝ መቻል አለብን። 
 
ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን የተባለው ትልቅ አባባል ነው።  ስንኖር ኢትዮጵያዊ ነን ከማለታችን በፊት ግን ለግላዊ ቡድንተኝነት መሞት ያስፈልገናል። ኢትዮጵያዊነትን ለመኖር ከፈለግን፤ ከተከፋፈልንበት አጥር ወጥተን መያያዝ መቻል የግድ ይላል።  ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊነትን በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ብቻ የምናወራው ነገር እንጂ፤ የምንኖረው የሕይወት ዘይቤ ሊሆን አይችልም። 

Read More
2 Comments
    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል