myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

​ፍቅር እንዲያሸንፍ ከራስ መውጣት ያስፈልጋል

8/9/2018

2 Comments

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
አዲስ የኦሮምያ ካርታ ማውጣት የጊዜው መልስ ነውን?
 
ፍቅር እንዲያሸንፍ ክርስቶስ ሰማይን ትቶ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ።  ያለዋጋ ፍቅር ሊያሸንፍ አይችልም።  ስለዚህ ፍቅር በምድራችን እንዲያሸንፍ፤ ሁላችንም ከቡድንተኝነት አስተሳሰብ ወጥተን፤ ለጋራ ኢትዮጵያዊነት ልዕልና መኖር እንድንችል መያያዝ መቻል አለብን። 
 
ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን የተባለው ትልቅ አባባል ነው።  ስንኖር ኢትዮጵያዊ ነን ከማለታችን በፊት ግን ለግላዊ ቡድንተኝነት መሞት ያስፈልገናል። ኢትዮጵያዊነትን ለመኖር ከፈለግን፤ ከተከፋፈልንበት አጥር ወጥተን መያያዝ መቻል የግድ ይላል።  ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊነትን በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ብቻ የምናወራው ነገር እንጂ፤ የምንኖረው የሕይወት ዘይቤ ሊሆን አይችልም። 
ዶ/ር አብይ ያለ ጊዜያቸው የተከሰቱ መሪ ሳይሆኑ አይቀሩም ብዬ እፈራለሁ።  ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዛሬ ላይ ተገኝተው ለኢትዮጵያዊነት መሞገት ብቻ ሳይሆን፤ ነገን አሻግረው አይተው አንድ አፍሪካን ሲሰብኩ፤ በሌላ በኩል ብዙ መሪዎች ትላንትና ላይ ተቸክለውና በጎሣ አጥራቸው ተገድበው፥ ከንግግር ያለፈና በተግባር ላይ የተመሰረተ መደመርና መሻገር ላይ ሲልቁ አይታዩም።
 
መሪዎችን ሁሉ ጨምሮ ሕዝበ ኢትዮጵያ ሰማያዊ ጥበብ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ያስፈልገናል።  የምስራችን ብስራት ሰማን እንጂ በምስራች ውስጥ ለመገለጥ ብዙ ፈተና በፊታችን ተደቅኗል። በለመድነው አካሄድ መሄድ መሰናከል ካልሆነ በቀር ለድል አያበቃንም። 
 
በእውነት ከራሳችን ወጥተን፤ በፍቅር ለጋራ ኢትዮጵያዊነት እሴት መኖርን ዋና ነገር ለማድረግ እንንቃ። ዶ/ር አብይ እንዳሉ ስንደመር ከ “እኔና” ከ “አንተ” ወጥተን፤ ወደ “እኛ” እንሻገራለን። ለራሳችን ስንሞት የምንጎዳ ይመስላል፤ ግን በ “እኛ” ውስጥ የምናገኘው በረከት ከ “እኔነት” ከምናገኘው እጅግ በብዙ ይበልጣል።  ይህ የፍቅር ህግ ነው።  ያኔ የፍቅር አሸናፊነት ዕውን ሆኖ በምድራችን ይታያል።  ኢትዮጵያም በፈጣሪ ስር ያለች አንድ ቤተሰብ እንደሆነች ዕሙን ይሆናል። 
 
ጊዜው የሚጠይቀው ስለ ጎሣችን ካርታ ለመሳል የምሽቀዳደምበት ሳይሆን፤ ዲሞክራሲ እንዲወለድ ሁሉም የኢትዮጵያ ነፃ አውጭ መሆን ነው።  ይህንን ባለማስተዋል ዕድሉ ካመለጠን፤ ይቅርታ የሌለው ሃጢያት እንደ መስራት ይቆጠራል። 
 
ለሁላችንም ቅን ልቦና ይስጠን!
2 Comments
Berhanu Mengistu
8/9/2018 12:34:36 pm

Excellent piece.

Reply
Kejela Gemtessa link
8/14/2018 09:24:06 am

Dear Dr. Zelalem;
I am glad reading your articles starting some six months back. Even I gave my comment to a person blindly criticizing your academic level. Forgive him because, he does't know you are the gold medalist. I told him about this in my feedback to his comment.

Now coming to your comment/question about new map of Oromia, I assure you that there is no new map of Oromia. it is as old as of the 1970s map drawn by the then rebels. I also assure you that no Oromo has an interest in a separated Oromia as long as there is free and democratic Ethiopia. If there is no Democracy in Ethiopia even under the new leadership, you will be the first person to come up with a new Map of Amhara. Democracy is the base for everything. As long as Ethiopia is democratic country and equal for her all 110 million people, regional maps will fade definitely. I am sure you guys now living in a democratic USA can teach us what really democracy is. Let us support Dr. Abiy's leadership and see how it goes in the future. We can learn about tolerance and democracy from India. Currently, India has more than 1.355 billion population with multi ethnic, language, and religion. At the same time India has more than 29 regional states. Every Indian people are enjoying democracy and proud of being an Indian. So why not we? As long as there is basic human rights like freedom of speech, freedom of writing, freedom of participating in any political affairs, etc and finally election using one person one vote, definitely regional maps will not be our concern. Abiy is saying "Medemer", meaning H2+O= H2O. H and O can not replace each other. Rather both elements should be there to get water. No one should push H to be an O or vice-versa to get water. This is simply our elementary chemistry we learned from Mr. Mulugeta (Bohr) of our Chemistry teacher at Alemaya.

God bless you.
Kejela Gemtessa


Reply



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል