myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

​የኢትዮጵያ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው

10/27/2019

2 Comments

 
 ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ዕድሜ ልካችንን በመከራ ውስጥ አልፈን ስናበቃ፥ የብርሃን ጭላንጭል አሳይቶ እንቁልጭልጭ የሚጫወትብን ጨካኝ አምላክ የለንም። እግዚአብሔር በምድራችን የጀመረውን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርስ መንገድ ላይ አይጥለንም።  
 
እግዚአብሔር ያያል። 
እግዚአብሔር ይፈርዳል። 
ፈጥኖ ይፈርዳል። 
በቀናት ውስጥ ክብሩን ይገልጣል።
 
ዲያብሎስ የደገሰልን የዕልቂት እኩይ ሤራ ይገለበጣል። ኢትዮጵያ ወጀቡን አልፋ ትሻገራለች። 
ታበራለች። 
 
መከራ ያየነው ከዓለም በኃጢአት አንደኛ ስለሆንን አይደለም።  የቃል ኪዳን ሀገር የሆንነው ከዓለም በፅድቅ አንደኛ ስለሆንን አይደለም።  ያለፈው መከራችንም ሆነ የሚመጣው ጉብኝታችን ምክንያቱ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር እንዲገለጥብን ብቻ ነው።  
 
ጠላት ለኢትዮጵያ መበታተን ያጠመደው ክፉ ወጥመድ ለእኛ ጭንቀት ቢሆንብንም፥ ለፈጣሪ ክብሩን እንዲገልጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ምድር ሁሉ በኢትዮጵያ አምላክ አለ እስኪል ድረስ ሥራውን ሊሰራ ፈጣሪ ራሱ ይወርዳል።
ወጥመዱን ይሰብራል።
ኢትዮጵያንም ያስመልጣል። 
 
ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡
·      የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ
·      አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
·      ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
2 Comments
Gezahegn Bekele
10/28/2019 12:59:42 pm

Amen yihonal!! Egziabher yetenagerewin yadergal!!!

Reply
Geremew
10/29/2019 12:14:04 pm

Egzehabher yebarkih wondem alem!!!
Seletesfa kalu geta yemesgen!!!
Ahun yeminalfebet mekera kalefew aybisem.
Betesfa tsenu bemekera tagesu

Reply



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል