myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

የኢትዮጵያ ትንታጎች ይነሡ!

9/19/2019

1 Comment

 
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ፖለቲካ ምድራዊ ነው።  ሃይማኖት ሰማያዊ ነው።  የምድሩን ማመስ አልበቃቸው ብለው፥ ተንጠራርተው ሰማይን መንካታቸው፥ እነርሱ ራሳቸው የሚበተኑበት ወቅት ጅማሬ መሆኑን ማን በነገራቸው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከዓለም ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ሌላውን በውጭ ያሉትን ኦርቶዶክስን ጨምሮ) ለየት ያለ ነው።  በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጥቅም ላይ የሚውለውን የግዕዝን ቋንቋ በመጠቀም፥ በግዕዝ ቅዳሴ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ ዛሬ በመጠበቅ፥ የተለያየ ቋንቋ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን በእኩልነት ባማከለ መንገድ ማገልገል የቻለች፥ በምንም የማትቀያየርና የማትለዋወጥ አዕማድ የሆነች ቤተክርስቲያን ናት። ከዓለም ብቸኛ የሆነች ይህች ቤተክርስቲያን ታቦትን በቤተክርስቲያን ውስጥ፥ ደግሞም ታቦትን እያወጣች (እያነገሰች) የምትገኝ፥ ለዓለም “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለውን የተስፋ ቃል የሚያስረግጥ፥ የቃል ኪዳን ሀገር መሆኗን ለፍጥረት ሁሉ በአደባባይ የምታውጅ ናት።  ኦርቶዶክስ እንደ እኔ ላሉ የወንጌላውያን እምነት ተከታዮች እንደ እናት ቤተክርስቲያናችን የምትታይ ብቻ ሳትሆን፥ ለኢትዮጵያ ሀገር እንደ እናት ሆና በፀሎት የምትማልድ የኢትዮጵያ ስጦታ ናት።
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የማንም ጥብቅና አያስፈልጋትም። የነካት ከመሠረታት አምላክ ጋር ይጋፈጣልና ተውት።
 
ኢትዮጵያዊነትን ለማለምለም ትንታጎች መነሳታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።  ታዲያ እነዚህን የኢትዮጵያዊነት መልክተኛ ሆነው የሚንቀሳቀሱትን ለማዳከምና ተስፋ ለማስቆረጥ የሚሮጡ ካሉ እግዚአብሔር ይታረቀቻው።  
 
አንዳንድ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ነን የሚሉ ወደ ልባቸው ተመልሰው፥ እነርሱ ባያውቁትም ያከበረቻቸውን ኢትዮጵያን ቢያቅፉና ለኢትዮጵያዊነት ልምላሜ ደፋ ቀና ቢሉ፥ ለሂስና ለትችት አይጋለጡም ነበር።  ሰውን የምንቃወመው ለመግደልና ለማጥፋት ሳይሆን ለመመለስ ነው።  ፅንፈኞችንና አክራሪ ዋልታ ረገጦችን የምንቃወመው፥ ኢትዮጵያን ከማፍረስ ሙሉ ለሙሉ ታቅበው፥ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ ጉዞ እስኪጀምሩ ድረስ ነው።  ከመካከላችን ለዘላለም ጠላታችን የሆነው ሥጋና ደም የሌለው ሰይጣን ብቻ ነው።  ከዚያ በተረፈ ሁላችንም የወንድማችን ጠባቂ መሆን ይገባናል። 
 
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
 
ኢሜል፥ Z@myEthiopia.com
1 Comment
Chernet
9/20/2019 03:03:28 pm

Selam Zelalem;
I totally agree with the main point of your article. Orthodox church and the History of Ethiopian is intertwined. No doubt the contribution of the Church to our beloved country is huge. And I also believe in one head of the church, Synodos.

However, at this stage of the history of the country and the period of globalization, I do not believe people to be asked to preach by the language they do not understand. They can preach with their language and follow the rule of the head of the church, Synodos.

Reply



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል