myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

​ዶ/ር አብይን በእውቀት እንወቅ

9/24/2019

4 Comments

 
 ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፤
አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው።
 
ብርሃን ፈነጠቀ ዶ/ር አብይ መጣ፥
ኢትዮጵያን ሊታደግ እርሱ እንቅልፍ አጣ፥
ሁሉም ደገፈና አንድ ላይ ሰልፍ ወጣ፥
ልናርፍ ነው ብሎ ከነበረን ጣጣ።
 
ቃሉ የሚጣፍጥ የሌለው ወደር፥ 
ትህትናው ግሩም ልዩ ከምድር፤
ፅናቱ የሚገርም ደግሞም እይታው፥
ድፍረቱ ትጋቱ እጅግ የሚደንቀው።
 
ጠላቱ እያደር እየበዛ ሲሄድ፥
ወደድኩህ ያለውም ሊያወጣው ከመንገድ፤
ከወዲህ ከወዲያ ሁሉም ሲጎትተው፥
ስምም እያወጣ ቢጎነታትለው፤
ዝም ብሎ ነጎደ አልተነቃነቀ፥
ሁሉንም እያየ አውቆም እያወቀ።
 
የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፥
አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው፤
ጠላቶቿ በዙ እጅግ ጨከኑባት፥
ስለዚህ ወረደ አምላክ ሊፈርድላት፥
ምድር ዝም ትበል ይታይ ሲለይለት።
 
ትዕግስት አይጠቅመንም ቶሎ ያልቃልና፥
ተስፋም አይረዳንም ስጋት ያንቃልና፤
ይልቁንስ እንይ የማይታየውን፥
በእውቀት እንወቅ አይለፈን ይህ ቀን።
4 Comments
Berhanu Mengistu
9/24/2019 08:51:43 am

Thanks for sharing.
The challenge for me on making comments on a media like this is that the communication is one way, no engagement in any form of dialogue.
I like the poem, just on target, but I have a question on the last four lines, the concluding stanza.
Thanks again for sharing and inspiring.

Reply
Lulsegged Abebe
9/24/2019 10:55:48 am

ዶ/ር ዘላለም፣ ጥሩ መልእክት የያዘ ግጥም ነው፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ የሰጠውን አስተያየት እጋራለሁ፡፡ በተለይ የሚከተሉት ሁለት ስንኞች፡

"ትዕግስት አይጠቅመንም ቶሎ ያልቃልና፥
ተስፋም አይረዳንም ስጋት ያንቃልና፤"

ትዕግስት አያልቅም፤ እየዳበረና እያደገ የሚሄድ ነው፤ በተለይም በእምነት እይታ ስንመለከተው፡፡ ሃሳብን ከማጎልበቻ መንገድ አንዱ ነው ብዪ አምናለሁ፡፡ ተስፋም እንደዚሁ፡፡ በትዕግስት ሰዎች ራሳቸውን እንዲመረምሩ ዕድል ያገኛሉ፡፡ በሂደት ወደ መቻቻል፤ መግባባት፤ ያደርሳሉ ፡፡

Reply
Zelalem Eshete
9/24/2019 11:06:12 am

በኢትዮጵያ በየዕለቱ የሚካሄደውን ድራማ ብቻ እያየን ብንታገስ ሩቅ ርቀት አንሄድም። ተስፋም እንደዚሁ። ትዕግቱም ያልቃል፥ ተስፋውም በስጋት ይታነቅና ይመነምናል። ግን የማይታየውን የኢትዮጵያ አምላክን ብናይና በዚህ እውቀት ነገሮችን ብንተረጉም፥ እውነተኛ ትዕግስትና እውነተኛ ተስፋ ኖሮን ዳር ያደርሰናል ለማለት ነው። አስተያየታችሁን ወድጀዋለሁ። ሁለታችሁንም እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

Dereje kifle
9/25/2019 01:03:10 am

ተስፉውን በትግስት መጠበቁን ባልጠላሁት ነበር:: እንደ ጎርቫቾቭ መስሎኝ ነበር እንዳይሉኝ ብዬ ባልፈራ

Reply



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል