myEthiopia.com
  • ደወል

የዘላለም እይታዎች 

የኛ ዶ/ር አብይ

6/29/2019

2 Comments

 
ከዶ/ር ዘላለም እሸቴ
 
ሳይቸግርህ ነግሠህ
በእሳት ተጥደህ
ማን በደረሰልህ?
 
ሁሉም ተጠርጣሪ
ይፍረደን ፈጣሪ።
 
አንተ ቅን፥ ሕዝብ ቅን፥ ታዲያ ምን ያደርጋል?
በመካከላችሁ፥ ሴረኛው ሰልጥኗል፤
በትንሹ ምላስ፥ ሰውን እያባላ
የኢትዮጵያን ነገር፥ አሳጥቶ መላ፤
ለራሱ በሚኖር፥ ባይኖረውም ገላ
ሀገር ተቃጠለ፥ ምድራችንም ቀላ።
 
እኔ ፈርቻለሁ፥ እንዳይደክምህና
በነገር አዙሪት፥ ልብህ ይደማና፤
ስልጣንህን ለቀህ፥ ያሁላችሁ ብትል
አሰመሳይ ነህ ያሉህ፥ ያገቡናል ገደል።
 
/አንተማ/
ሀገር መምራት ሳያንስ፥ ቄሶቹን አስታርቀህ
ወንጌላዊ ባዩን፥ በላይ ጥበብ መክረህ
ሙስሊሙን አንድ አርገህ፤
እስቲ እርዱኝ ብትል፥ ሀገርን እናድን
ምንም አላየንም፥ ተባለ እንጂ አሜን።
 
አንድ ሰው መሆንህ፥ እውነቱ ተረስቶ
የከበበህ እሾህ፥ ያለምከው ተስቶ፤
/ጉድ እኮ ነው/
በራሱ ጣራ ስር ፥ፍቅር ቤቱ የለ
ተጣልቶ ከራሱ ሌላን ያገለለ
ጣቱን ቀሰረብህ፥ ሊፈርድም ፈጠነ
የራሱን ጉድ ትቶ፥ ያንተን ጉድ መዘነ
 
/እየዋለ ሲያድር/
የሚወጋህ በዝቶ፥ በግልፅ በአደባባይ
ደጋፊህ በድብቅ፥ በዝምታ ሲያይ፤
የደፈረ ወዳጅ፥ ቃልን ቢሰነዝር
በውርጅብኝ ብዛት፥ ቅስሙ ሲሰባበር፤
ብቻህን እንድትቀር፥ ሴሬኛው ሲያደባ
ሁሉም ቀስ በቀስ፥ ወጥመዱ ውስጥ ገባ።
 
/መቼ ነገስክና/
አጉሊ መነፅር፥ ለድካምህ
ላጲስ፥ ለብርታትህ፤
ድምፅ ማጉያ፥ ለረባሹ
የነገሠው፥ ጠብ መራሹ።
 
ፍቅር ብለህ ሞተህ፥ ተደመሩ ብትል
ሤራና ሸር ነግሶ፥ አላገኘህ ዕድል፤
አንዱን ስትገነባ፥ ሌላኛው ይፈርሳል
ቅንነት ስትዘራ፥ አረሙ ያንቀዋል፤
ቆመን ስናሞግስ፥ ቁጭ ብለን ስንተች
አረሙ አሸነፈን፥ ስንፈራ ያንን ተምች።
 
አለቀ ደቀቀ፥ እንዳይሆን ነገሩ
ወጥመዱ ይሰበር፥ ይነቀል ከሥሩ፤
ኢትዮጵያችን ታምልጥ
እጃችንን አንስጥ።
 
ሳይቸግርህ ነግሠህ
በእሳት ተጥደህ
ሕዝብ አለ ከጎንህ።
 
ኢሜል፥ Z@myEthiopia.com
2 Comments
ዳኛቸው
6/29/2019 08:08:18 pm

ዶ/ር ዘላለም ድምፅ ስለሆንክልን እኔ አመሰግናለሁ::
እግዚአብሄርአገራችንን ይባርክ!
መሪያችን ዶ/ር ዓቢይን ይባርክ- ይጠብቅልን!

Reply
Betty
6/29/2019 10:11:08 pm

Dr Zelalem,

Impressive. I stand with PM Dr Abey. God bless Ethiopia

Reply



Leave a Reply.

    Picture

    Archives

    December 2022
    August 2021
    July 2020
    November 2019
    October 2019
    September 2019
    August 2019
    July 2019
    June 2019
    April 2019
    February 2019
    December 2018
    October 2018
    August 2018
    July 2018
    June 2018
    May 2018
    April 2018
    October 2016

    Categories

    All

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል