myEthiopia.com
  • ደወል

የማንነት ቅኝት (መጋቢ ሰለሞን ጥላሁን)

7/24/2018

0 Comments

 
 ከሃይማኖተኛ ኢትዮጵያዊነትና ከመንግስትና ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት አንጻር
 
ኢትዮጵያዊነት፣አማኝ ወይም አላማኝ፣ ወንዶችና ሴቶች፣ ኦሮሞ፣ አማራና ሌሎች በርካታ ብሔሮች፣ ሃብታምና ደሃ፣ የተማረና ያልተማረ፣ ቆለኛና ደገኛ፣ ልጆችና ጎልማሶች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩነቶች አንድላይና ለየብቻ ሆነው የሚሰጡን ማንነት ነው፡፡ የእነዚህ ልዩ ልዩነቶች መሰባጠርና እያንዳንዱ ከያንዳንዱ በያንዳንዱ ለእያንዳንዱ በተቀባባይ ሳይጠፋፉ መኖር (Interpenetration)ጠንካራ ብሔራዊ ሹሩባ ይሆናል፣እንዲህምስለሆነየማሕበረሰባዊ  ሚዛናዊ ኑሮ  (Social homeostasis)መጠበቂያምስለሆነ አክብረን ልንይዘው ይገባል፡፡ 
----///-------//------
Picture
በያንዳንዱልዩልዩነቶቻችንውስጥየእርስበርስግንኙነቶችአሉን፣ሙስሊምሴትሆኜከኦሮሞብሔረሰብየሆንኩ፣ነገርግንያልተማርኩልሆንእችላለሁ፣ወይደግሞበደጋማውየአማራክልልየምኖርዝቅተኛኢኮኖሚያለኝጽኑክርስቲያንሃይማኖተኛልሆንእችላለሁ፣ወይከሙስሊምዐፋርአባቴእናከወሎዋአማራእናቴተወልጄበፌደራልከተማውስጥበህክምናአገልግሎትየምተዳደርያላገባሁወጣትየፕሮቴስታንትእምነትተከታይልሆንእችላለሁ፣ማንነትነጠላአይደለምድርብርብ(Nested)ነው፣በሃይማኖትብቻአይገለጽም፣በብሔርምበኢኮኖሚምደረጃሆነበትምህርትደረጃእናበጾታብቻአይገለጽም፣በዚህልዩሆኜበዚያልዩከሆነውጋርአንድላይነኝ፣ማንነትፓኬጅነው፣ተመሳሳያችንንብቻበፈለግንመጠንማንነታችንንነውየምንጎዳው።ማንነታችንተወልደንያለፈቃዳችንያገኘነውናከውልደትበኋላበሕይወትስምሪትያገኘነውንያደባለቀነው።በአንደኛውየመኩራትመብትአለንለፍተንስላገኘነው፣(ቢሆንምተገቢአይደለም) በተወለድንበትግን“እኮራበታለሁ” ብንልልክልንሆንአንችልም፣ምክንያቱምየተቀበልነውእንጂለፍተንያገኘነውስላልሆነ።የተወለድንበትንአንኮራበትም፣አንሸማቀቅበትም፣በቃዝምብሎ“ነን!” ብዬአምናለሁ።
----///-------//------
 
ማንነት ከሌላው የተለየው እኔነቴ ነው፣ ቢሆንም ማንነቴን የማገኘው ግን ከሌላው ጋር ባለው ግንኙነቴ ነው፣ የሚመነጨው ውስብስብ ከሆነው እኔና ሌላው ሰው/ሰዎች/ በስምምነት እርስ በርስ ከምናደርገው የመስተጋብር ታሪክ ውስጥ ነው። ስለዚህ የየግላችን ልዩታ አይደለም በስምምነት እንድንኖር የሚያደርገን፣ ይልቁንም ከሌሎች ጋር ራስን በመለገስ ስብስብ ውስጥ ስንሆን እንጂ። 
----///-------//------
 
ብሔራዊነት የጋራ ማንነት ነው፣ የብሔራዊነት ኃይል የሚፈልቀውም ከሕዝብ ባሕል፣ እምነት፣ ብሔር እና ሌሎች ብዙ ልዩነቶች ውስጥ ነው። ኢትዮጵያዊ መሆን ያለብዙ ልዩ ልዩነት ሊገለጽ አይችልም። “ያለሌላው የብቻ ዓለምን” የሚያስብ አስተሳሰብ ከሌላው ጋር በግጭት የመናቆሪያ ማእከል ይሆናል፣ እንዲህ ዓይነቱም አስተሳሰብ ሃይማኖትን ይጭናል እንጂ አባላቱን ወደ ሃይማኖት አይጋብዝም።  የዘር ማጥፋት ተግባራትም የሚወጡት እንዲህ ዓይነቱ ጽንፍ ከሚበዛባቸው አስተሳሰቦች ነው። እንዲህ ዓይነት አስተሳሰቦች እንኳን ሙሉ ሐሳባቸው አዝማሚያችው እንኳ ተቀባይነት ሊያገኝ አይገባም፣ እያንዳንዱ ከእያንዳንዱ ያለውን ተቀባባይነት በአመጽ ለማቋረጥና ወደ ጠባቡ ተመሳሳይ ስብስብ የሚወስዱ ጥረቶች ሁሉ ወደ ቅርጽ አልባ ባዶነት የሚከልሱ ኃይላት ከመሆናቸው ባሻገር “እግዜር አንድ ያረገውን እንግዲህ ሰው ይለየው” የሚሉ ገዳይ ኃይላት ናቸው!!! 
 
----///-------//------
ምንም እንኳ ትኩረቴ በክርስትናው እምነት ላይ ቢሆንም፣ በየትኛውም ማህበረሰብ የሃይማኖት መሪዎች እዚህ ጋ ይህንን አስተሳሰብን መቆጣጠርን በሚመለከት ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በማሕበረሰብ ውስጥ ማህበረሳባዊ ስትራተጂዎችን መቀየስ ግን የመንግስት እንጂ የሃይማኖት መሪዎች ሚና ሊሆን አይገባም። ሚናቸው ሊሆን የሚገባው ሰላማዊና ፍትሐዊ የማሕበረሰብ ወኪል (ግለሰብን) ማስገኘት ብቻ ነው። ከሌሎች ማህበራዊ ተቋማት በተሻለ አንድ የሞራል ወኪልን ማስገኘት የሚያስችል ራስን የመስጠትና የትኩረት አቅም አላቸው፣ የመኖራቸውም ውጤት ይኸው ነው። ማህበራዊ አደረጃጀትና ማሕበራዊ አደረጃጀትን የሚከውኑ ወኪሎች (ግለሰቦች) መካከል ጥብቅ ማስተጋብር/ቅብብሎሽ አለ፤ መንግስት የማሕበራዊ አደረጃጀት ችግሮች ላይ ሲያተኩር የሃይማኖት ተቋማት ደግሞ አመኔታ የሚጣልባቸውን ማሕበራዊ ወኪሎችን በማስገኘት መንግስት የሚፈጽመውን ማሕበራዊ አደረጃጀት በሰላማዊ መልኩ የሚፈጽሙ ወኪሎችን (ሰዎችን) ያስገኛሉ ማለት ነው።  
----///-------//------
 
እስካሁን በአገራችን ያሉ የሃይማኖት ተቋማት ይህንን አስገኝተዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ በአማካይ አዎ ሊባል ቢችልም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖተኛነት አንጻር ስንመለከት ሰላማዊና ፍትሐዊ የማሕበረሰብ ወኪል እንደሚገባ አለማስገኘታቸው ግልጽ ነው። ምክንያቱ ብዙና ውስብስብ ቢሆንም ጎላብሎ የሚታየን ግን በቀድሞው ዘመን የነበረው የመንግስትና የቤተ ክርስቲያን እጅና ጓንትነት ቤተ ክርስቲያንን ለሰብአውያን መንግስታት አዳሪና የጨቋኙ ስርአት ተባባሪ ሲያደርጋት በኮምኒስት ቆይታ ዘመን ደግሞ ለህልውናዋ ታጋይ አድርጓት ቆይቷል፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ደግሞ የነጻነትን ገፈት በውስጧ ብልሽት እያስተናገደች ሲሆን በቤተ እምነት ደረጃ ወንጌላውያኑ ደግሞ የስደቱ ተቃራኒ የሆነ የመንግስት ቅርርቦሽ ይታይባቸዋል።  ብዙ ሊባልበት የሚችል ቢሆንም ማለፉን እመርጣለሁ። ይሁን እንጂ የመንግስትንና የቤተ ክርስቲያንን መሰረታዊና ቋሚ! ልዩነቶች ማወቅ፣ አውቆም ከወዲሁ አቋም መያዝ የአማኞችና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሁሉ ኃላፊነት ነው።
----///-------//------
 
መንግስት መርሆውም ሆነ የአመራር መስፈርቱ ተለዋዋጭ ነው፣ መሪዎች በስምምነት ወይም በግድ የሚመሩበትን መንገድም (ተግብሮት) ሆነ የሚመሩበትን መርህ ሊለውጡት ይችላሉ፣ ይህንን ማስፈጸሚያ ኃይላቸው ቀጥተኛ የሆነና ቀጥተኛ ያልሆነ አስገዳጅ ኃይል ነው፤ መድረካቸውም የሕዝብ አማልክት የሚፋለሙባቸው ስፍራ ናቸው፣ ሰውም በዚህ ስፍራ አንዱ አምላክ ነው፣ መሪዎች በመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ሆነው ለሚጫወቱት ሚና “ዳግም ተወላጅ” መሆን አይጠበቅባቸውም ቃሉም እንኳ ስፍራ የለውም፣ መንግስት የሚተዳደረው ሙሉ በሙሉ ሕዝብ በተስማማበት ወይም የተወሰኑ ክፍሎች በሚጭኑት “ሕገ-መንግስት ነው፣” መሪዎች ወይ በጡጫ ወይ በምርጫ ይለወጣሉ፣ የነኳቸው/የሚሰለጥኑባቸው ተቋሞች ሁሉ በሥራቸው እንዲሆኑ ይፈልጋሉ፣ አለዚያ ይሰጋሉ፣ ከሚታየው ተዳሳሽ ዓለም ውጪ ያለው ጕዳይ አጀንዳቸው አይደልም፣ ለማድረግ በተሞከረም ቍጥር ወይ አጀንዳው ይበላሻል ወይ መንግስት ይበላሻል። 
----///-------//------
 
ቤተክርስቲያንግለግንዛቤዋን(self-understanding)የምታገኝበትመርህአይለዋወጥም፣ትክክለኛመሪዎቿስሱ/ለጥቃትየተጋለጡ(vulnerable)፣ናቸው፤ የምትመራበት መርህ ሊለወጥ አይችልም፣ መሪዎቿም ይህንን አይለወጤ መርህ የማስፈጸሚያ ሰብአዊ ኃይልም የላቸውም፣ በየተገኘችበት መልክአምድርና ባህልም እጅግ በጣም የውጨኛው ገጽታዋ ዐውዷን ይምሰል እንጂ በምንነቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ  ከቶውንም ልትለዋወጥ አትችልም። በመድረኳ ላይ ልታስደስታቸው የምትጣጣረው የአባላቷ የተለያዩ አማልክት ፍልሚያ የለም፣ ሁሉ ነገር ትኩረቱ ፈጥሮኛል፣ ባለቤቴ እርሱ ነው ወደምትለው አንድ አምላክ ብቻ ነው፣ ሰው በዚህ ሰፍራ እርስ በርስ ያለ አንዳች ልዩነት ሁሉም እኩል አንዱን ብቻ አምላኪ ነው፣ መሪዎቿም ከሁሉ በኋላ የመሆን ግዴታ አለባቸው፣ የሚመሯትም ሆነ “ዜጎቿ”  የመጀመሪያው የአባልነት መስፈሪያቸው “ዳግም መወለድ” ነው፣ መሪዎቿ ከዚህ መስፈርት በተጨማሪ በዓለም አተያይ ውርደት ሊባሉ የሚችሉ የጠነከሩ መስፈሪያዎች አሉባቸው፣ ከነዚህ ውስጥም አንዱም ሰውን የማስደሰት ዓላማ የለበትም፤ እንዲያውም ሰውን ማስደሰት ቀዳሚ ድርሻቸው ሲሆን የእግዚአብሔር አገልጋይ ያለመሆን ምልክት ነው፣ ትክክለኛ መሪዎቿ በሕዝብ ስምምነት ባልተገኘው፣ መለኮታዊ ቃል እስትንፋሰ መለኮት በሆነው ቃሉ ትክክለኛ ምጋቤ ይመሯታል፣ ይህንን በማድረጋቸውም እንደ ፓርላማ አባላት ያለመከሰስ መብት አያገኙም፣ይልቁንም “የበለጠ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።” አንዳንዴ የአገልግሎት ጥሪአቸው ግዜ ገደብ ኖሮት ቢታይም፣ ምንም የማያሰልስ የአገልግሎት ሕይወት ይጠበቅባቸዋል፣ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሰጠችው ማንም ግለሰብ በስሯ እንዲሆን ሳይሆን አብሯት እንዲሆን ትፈልጋለች፣ ስጋቷ ሙሉ በሙሉ ተልእኮዋን ከመወጣትና አለመወጣት አኳያ እንጂ የሕልውና ስጋት የላትም፣ በታሪኳ ሊያጠፏት በተሞከረ ጊዜ ሁሉ እጅግ የበዛች ተቋም ናት፣ መንግስት ስለደገፋት አትቆምም ስለገፋትም አትወድቅም፣ ከሶስት ነገሮች ጋር ስትነካካ ግን ጤና ይጎድላታል፣ ከበዛም ከአካባቢው ይሰውራታል፣ ዓለማዊነት፣ የአባላቷ ሥጋዊ ባሕሪያትና የእነዚህ አጋፋሪ ዲያብሎስ። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ብትገኝም የምትሰጠው ተስፋ ስለሚመጣው አዲስ ዓለምና ተስፋ በመሆኑ ከምድር ተቋማት ጋር መሰረታዊ የግብ ልዩነት አላት!!! 
----///-------//------
 
እንግዲህ መንግስትና ቤተ ክርስቲያን ሊጋጩ የማይገባቸውና አንድላይ የመኝታ ጓደኞችም ሊሆኑ የማይገባቸው ናቸው። በቃ ለየብቻ ናቸው! በአንዳንድ ተግባሮች ለመንግስት ህልውና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ልታደርግ የምትችል ብትሆንም፣ የተግባሯ ተነሳሽነት የሚመነጭበት ምንጭ ፈጽሞ የተለየ በመሆኑ የእውነት ራሷን ለመሆን ስትነሳ ከሁሉም ተቋም ይልቅ መንግስትን ልታስደነግጥ የምትችል ተቋም ናት። የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚንቀሳቀስ መንግሥት የተባለ ተቋም በብዙኻን ድምጽ የሚወስነው ውሳኔ ሊተገብረውና ከለላ ሊሰጠው የሚችል ውሳኔ ነው፣ ይኽንኑ ውሳኔ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ከማንነቷና ከተልእኮዋ ጋር ሲጋጭ፣ ውስጥሽም ካልገባሁ ሲላት እምቢ ትላለች፣ ያን ጊዜ ለመንግስት የማትገዛ ትሆናለች፣ አሁን በምእራቡ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እያሳለፈች ያለችው ስደት ይህንንኑ ነው። 
----///-------//------
 
አሁን አሁን አንዳንድ አዝማሚያዎች ቤተ ክርስቲያን የላእላይ መዋቅሮችን ብትቆጣጠር ዓላማዋን ለማስፈጸም ያስችላታልና ይህንን ለማድረግ ማንኛውንም ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል የሚል አስተሳሰብ እና ተግባርም ይታያል፣ አዲስ አይደልም፣ ከዚህም በበለጠ ቤተ ክርስቲያን ሲሶ መንግስትም ሆና ታውቃለች፣ በአውሮፓም ነገስታትን ሿሚና ሻሪም ሆና ለመቶዎች ዓመታት ቆይታለች ግን ውጤቱ ብስባሴና የመንፈስ ቅዱስንና የጸጋ መገለጫዎችን ማጥፋት ሆኖ ቀረ። ባንዲራ የአገሮችን የፖለቲካ ኃይል የሚወክል ነው፣ የባንዲራ ጀግኖች የሚባሉትም ገዳዮች ናቸው፣ መስቀል ደግሞ የክርስትና ኃይል ምልክት ነው፣ የመስቀል ጀግኖች ደግሞ፣ መሲሓቸውን መስለው በሰማእትነት የሚያልፉና ሲኖሩም “በሚሞት ሕይወት” የሚኖሩ ናቸው። ሁለቱ አይዛመዱም!!! መዘውሩን ደጋግሞ ወደ ታሪክ ብልሽት መመልስ ምን ይጠቅማል?  
----///-------//------
 
ከላይ በክባዊ የስእል ማሳያ ለመግለጽ እንደሞከርኩት (ለመረዳት ማየት ግድ ይሏል)፣ “የክርስቶስ ፖለቲካ” የሆነው ብሉይ ወአዲስ ሻሎማዊ ሥርአት ስጋዊ ወመንፈሳዊ የሆኑ ክልሎችን ሁሉ የሚዳሥሥ ነው። ነገረ መለኮታዊው መርሕ ግን መተግበሪያው ማህበራዊ ኑሮ ነው፣ ተነሳሽነቱ ግን ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊ ነው፣ ግቡም ዘላለማዊ ነው። ቤተ ክርስቲያን ይህንን አስተምህሮ ያገኘችው ከራሷ ንጉስ ነው፣ ይህ ማንነቷም በውስጧ ተወልዶ ባሕሪዋ የሆነውም በሚደግፋት መንግስት መካከል ሆና ሳይሆን በሚያሳድዷት መንግስታት መካከል ሆና ነው። ከዚህ አንጻር ተነሳሽነታችንን መፈተሽ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው!!!
----///-------//------
ከወንጌል የሚገኝ ሻሎም/ሰላም
  • ጽድቅና  ፍትሕ
  • ጸጋ- ምክንያት ላይ የየልተደገፈ ቸርነትና ፍቅር
  • የኪዳን ታማኝነት
  • የእግዚአብሔር መንግሥት
  • የነገረ ፍጻሜ አዎንታዊተስፋ
  • ድነት
  • በጎረቤት ፍቅርና ጠላትን ከመጥላት ይልቅ በመውደድ የምንገለጠውለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር
  • በአማኙ ማኅበረሰብ መካከል እንዲሁም ከሌሎች ሰዎችና ሰው ካልሆኑ ፍጥረታት ጋር የሚኖረን የስምሙነትተና የእርቅ ኑሮ
ቤተ ክርስቲያን ማኀበራዊተሣትፎንበሚመለከትበታሪክመካከልሶስት አቋሞች ታይተውባታል፣ ታሪካዊ ጅማሬው ውስብስብና ጥንታዊ የሆነው ዓለማዊ ነክ ከሆኑ ጕዳዮች ሁሉ ማፈግፈግና ባለመነካካት፣ ጽድቅንና ቅድስናን መፈለግ፣ ባጭሩ የገለልታ አቋም፣ የማፈግፈግአቋም፣የብኅትውናአቋምሲሆን (ባለ ቀስቱን ስእል የግራውን ቀስት ይመልከቱ)
​ የዚህጽንፍየሆነውደግሞያለችበትንዓለምነባራዊሁኔታበመምሰል፣ለዓለምከአማራጭተቋማትአንደአንዱራሷንለገበያውበማቅረብየሰውንፍላጎትባተኮረመልኩየምትንቀሳቀስባጭሩየ“ተመሳስሎ” መርህን የምትከተል፣ዓለማዊት፣“አሁናዊት”፣“እዚሃዊት” የሆነች ዓለም እጇን ስትዘረጋላት ጓንት ለመሆን ፈቃደኛየሆነች፣ ተቋምስትሆን (ባለ ቀስቱን ስእል የቀኙን ቀስት ይመልከቱ) በሶስተኛ ደረጃ  ትክክለኛ አቋም ያንጸባረቀች ቤተክርስቲያንን የምናየው ከዓለም ተገልላ ሳታፈገፍግ፣ ከዓለም ጋርምአብራበመሆንሳትመሳሰል፣ነገርግንበዓለምውስጥራሷን ሆናየምትሳተፍ (Not out of the world, not of the world but in the world) ቤተክርስቲያንእንመለከታለን (ባለ ቀስቱን ስእል የመካከለኛውን ቀስት ይመልከቱ)። በዓለም ውስጥ ሆና የሻሎማዊውን ሥርዓት መርሆች የምትኖር ቤተክርስቲያን የምትከተለው የኢየሱስ ክርስቶስን ፖለቲካ ነው፣ ይህ ከብርሃንና ጨው አገልግሎቷ አንጻር ሲታይ ከዓለም ጋር አብራ በመመሳሰል በባሕር ውስጥ የተጣለ ጨው ሳትሆን ወይም ከዓለም በማፈግፈግ እጨው እቃ ውስጥ ብቻ የተቀመጠ ጨው ኢየሱሳውያን ማሕበረሰብ በመሆን አመጽ አልባ የሰላምና የፍትህ ማህበረሰብ የምትሆን በዓለም ውስጥ የምትሳተፍ ወይም በአገልግሎት ላይ ያለ ጨው ትሆናለች። 


ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ የሚሻላት ራሷን ሆና መኖር ነው! ግልጽና ጥርት ያለ ተልእኮዋ ላይ ማተኮር ብቻ! ሰዎችን የቤተ እምነት አባላት ማድረግ ሳይሆን፣ ደቀ መዛሙርት የሆኑ ዜጎች ማድረግ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የቤት ስራዋን ስትሰራ፣ ወደ ክርስቶስ በማምጣት እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ስታደርጋቸው፣ በውጤቱ አመጽ አልባ ማሕበረሰብ ታተርፋለች፣ ላለችበት አገርም በእርግጥ ይህንን አስተዋጻኦ ማድረግ የቻለች ቤተ ክርስቲያን ወደላይ እግዚአብሔርን ስታከብር ወደ ጎን ደግሞ ከየትኛውም ኃይል የበለጠ አገርን ትጠቅማለች፣ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ በመሆን የመልካም ሁሉ ኃይል ምንጭ በመሆን ክርስቶስን ታከብራለች። 
 
“...መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” 
​አሜን
0 Comments



Leave a Reply.

    Amharic

    Archives

    January 2022
    October 2020
    August 2020
    April 2020
    November 2019
    September 2019
    July 2019
    April 2019
    November 2018
    October 2018
    September 2018
    August 2018
    July 2018

    Categories

    All
    Current Affairs
    Sport
    The God Factor Forum

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል