myEthiopia.com
  • ደወል

my Ethiopia Forum - Pastor Worku Legesse

8/20/2018

0 Comments

 
0 Comments

አገሬ መቼ ነው የማዜመው?

8/20/2018

0 Comments

 
ኤፍሬም ፈለቀ
(ያቤጽ ከዳንግላ)

ከ540 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ገደማ ይኖር የነበረ የአይሁድ ምርኮኛ ሕዝብ፤ በአገሩ ናፍቆት ውስጡ ተናውጦ፣ ክብሩን አጥቶ፣ የዜማ ቃላት ከአንደበቱ ጠፍቶ፤ ታሪኩ ተተርኮለት ሰምቶ፥ በአይኖቹ ተዓምራትን አይቶ ተደምሞ፣ የአገሩ ክብርና የማንነት መኩሪያ መለያ ምልክት የነበረው፣ በአገሩ አፈር የአምላኩን ክብር እያየ የሚኖረው ኑሮ እንደሰማይ እርቆበት፤ ተክዞ ባለበት የባእድ የምርኮ ምድር፤ የክብር የዜማውን እቃ ሰቅሎ በተቀመጠበት፣ የማረኩት ባእዳን መጡና በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉ፥ ምርኮኛ መሆኑን አውቀው፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምርልን አሉት። ሕዝቡን አላወቁትም ለካ፣ ታሪኩን እንደሚያውቅ አልተገነዘቡም ገና፣ የሚዘመረውም ዜማ መቼ፣ ለማን እና ለምን እደሆነ አልተረዱም፤ የሰቀለው የክብሩን የዜማ እቃ ክብሩ ሲወርድ ብቻ እንደሚወርድ አላወቁም።        

ያን ጊዜ ምርኮኛው ባለበት በባዕድ የስደት አገር እንዲህ እያለ በለቅሶ ምሬት ተቀኘ፥

በወንዝ አጠገብ ማዶ ተቀምጠን፣
ክብርሽን ስናስብ እጅግ አለቀስን።
ዝማሬ እርቆናል ከአንደበታችን ጠፍቶ፣
በዛፍም ተቀምጧል ተሰቅሎ ማስንቆ።


የማረኩን አሉን ፈንጥዙ ዘምሩ፣
የክብርሽን ዝማሬ በሆታ አውጁ።
አይዘመር ላንቺ ሆነሽ በውርደት፣
አይታሰብም ከቶ በባዕዳን ምድር።


አልረሳሽም እኔ እያለው በቁሜ፣
ከረሳሁሽ ደግሞ ይኸው ትርሳኝ ቀኜ።
ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፣
አንቺ ብቻ ስለሆንሽ የደስታዬ ማዕረግ። . . . 


ብዕሬ ከነጠፈች እና ወረቀቴን ከሰቀልኩ አመታትን አስቆጥሬአለሁ። የአገሬ ኢትዮጵያ ናፍቆትና ክብርዋ ተመልሶ የማየቴ ጉጉት ለሆድ እቃዬ የእሳት ፍም፣ ለእግሮቼም የእሳት ውስጥ እረመጥ ከሆነ ቆይቷል። የአይሁዶቹን የለቅሶ ምሬት ቅኝት በለቅሶ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለኢትዮጵያዬ ወደ አምላኬ በመጮኽ አዝሜዋለሁ። ድቅድቅ ባለው ጨለማ ውስጥ ሆኜም የብርሃን ጭላጭል ለማየት ብዙ መንገድ ተጉዣለሁ። የአምላክ ጉብኝትንም ለሀገሬ እንዲደርስ እና በአይኔ ለማየት አምላኬን ተማጽኛለሁ። እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከቅርብ ወራት በፊት እየታየ ያለውን የተስፋ ጭላንጭል በማየት፣ ለአገሬ የመጉብኛዋ ጊዜ ደረሰ እንዴ? በማለትም ጠይቄአለሁ። 

እንደማንም ጉጉ ለውጥ ፈላጊ የየእለት ጉዞውን ስመለከት እና ሳጤን ግን፤ ልንጓዝ ያለንበት የጉዞ መስመር እረዥምነት፣ ከውስጣችን መነቀል ያለበት የመርዝ እሾክ ጥልቅነት፣ እና አሽሮን ሊወጣ የሚገባውን የተጣባንን ጥገኛ ተውሳክ ብዛት ሳይ እና ስመለከት፤ ለሀገራችን የምናዜምላት የክብርዋ ዜማ ጊዜ እጅጉን እራቀብኝ። የማየው ነገር ሁሉ ድብልቅልቅ አለብኝ። ማን ምን እንደሆነ እና ምን እንደሚያስብ ግራ ገባኝ። የሰው ልጅ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ መሆኑ አስጨነቀኝ። ጭብጨባው፣ ጩኸቱ እና እልልታው የድል ይሁን የሽንፈት መለየት ተሳነኝ። አንግሰው አና ስቀለው የሚለው ተመሳሰለብኝ።

አባካችሁ አትሸንግሉኝ፣ የዜማው ጊዜ አሁን ነው እያላችሁ በባዕድ ምድር እያለን ክብርዋ ሳይመለስ፣ የክብርዋን ዜማ ዘምረው አትበሉኝ። የሰው ስብዕና ተዋርዶ፣ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ በጥይት ተደፍቶ፣ ከልካይ በሌለበት በአውራው ጎዳናው ላይ የሰው ተክለ ሰውነት በእሳት ሲቃጠል፣ ምስኪኑን እረኛ በበግ መመለሻው በትር ተቀጥቅጦ ሲገደል፣ የፈጣሪ ፍርሀት ከውስጡ ተሰልቦ የገዛ ወንድሙን አደባባይ ሰቅሎ፤ አብሮ አደግ ወገኑን ውጣልኝ እያለ ደብድቦና ዘርፎ፣ የዘረኝነት አባዜ ናላውን አዙሮ፣ ደግሞም የባሰበት በመገናኛ ብዙሀን የጥላቻውን መርዝ እየረጨ እያለ፣ ጊዜው ነው አትበሉኝ ጊዜው መቼ ደረሰ። ጊዜው የለቅሶ እና የዋይታ እንጂ የዜማ መች ሆነ። ኢትዮጵያዬ መቼ ነው ክብርሽ ተመልሶ ዳግም ማዜምልሽ? የመለያሽን ዝማሬ በአፈር በመሬትሽ ላይ ቆሜ ዳግም የማዜምልሽ። ትንሳኤሽም ሆኖ እልል የምልልሽ። ደግነት ርህራሄ ከምድሪቷ ጠፍቶ፣ አምላክንም መፍራት ከእኛ ዘንድ እርቆ፣ ሁሉም እያደባ ሰይፉን እየሳለ፣ ሰላም ነው አትበሉ ሰላም መቼ አለ። የሰው ልጅ ከራሱ ገና መች ታረቀ። ትናትን እንዳማ ጉድ ነው! ጉድ ነው! እያለ፣ ገና አልገባውም እርሱ ራሱ ዛሬ ያማውን ትላንትን እየደገመው እንዳለ። የጠባውን የኢትዮጵያን ጡት እየነከሰ፣ በዘር በነገዱ ሁሉ እየተሸሸገ፣ ግንድን መጣበቅ ትቶ ቅርንጫፍ የያዘ፣ ረሳው ወገኔ ቅጠል ብቻ እንደሚሆን ብቻውን ከቆመ። ኢትዮጵያዬ መቼ ነው ክብርሽ ተመልሶ ዳግም ማዜምልሽ? የመለያሽን ዝማሬ በአፈር በመሬትሽ ላይ ቆሜ ዳግም የማዜምልሽ። ሰው በሰውነቶ ተከብሮ በምድርሽ፣ ክፉ ዘረኝነት ዳግም ላይመለስ ተነቅሎ ጠፍቶልሽ፣ እኩልነት ሰላም ፍቅርና ይቅርታ በአየርሽ ሰፎብሽ፣ በዘር መታወቁ ቀርቶ ለሁሉ ኢትዮጵያዊነት ሆኖ የመለያው አርማ፣ ኢትዮጵያዬ መቼ ነው ክብርሽ ተመልሶ ዳግም የማዜምልሽ? የመለያሽን ዝማሬ በአፈር በመሬትሽ ላይ ቆሜ ዳግም ማዜምልሽ? አምላክ ተለመነን ጸሎታችንን ስማ፣ ለውጡን የእውነት አድርገው ስቃያችን ያብቃ። መዘመር ናፍቆናል ምድራችን በክብር ተሞልታ።​

ነፍሴ በሁለት መንታ ስሜት ተወጥራ የጣር ሲቃ እየናጣት አሻግራ ታልማለች ተስፋም አልቆረጠች። የወጣችውን የአዲሷን ፀሐይ ጮራ ከሩቅ እያየች፤ ለውጡ ያመጣው የመልካምና የብሩህ ዘመን የመአዛ ሽታ ጠረኑን ነፍሴ ወዳዋለች። ለተጀመረው ጅምር የበኩልህን አድርግ ተሳተፍ ትለኛለች። ነፍሴም በታላቅ ድምጽ ከውስጥ ትጮሀለች፥ “የተንኮለኞቹን የጨለማ ሰራዊት ድምጽ አትስማ፣ የጦጲያና የሰበላጥ ድምጽ አያስተጓጉልህ፣ በወኔ መነሳትህን ሊሰልብ ሊያጨነግፍ የወጣ፣ የተንኳሾች ስውር ሴራ አንተን ለማደናቀፍ በመንገድህ የተቀመጠ ጋሬጣ፤ ጥቂት ሆኖ ሳለ በኃይል የሚጮህ ሰንካላ፤ ተወው አትዘናጋ ጉዞህ እረዥም ነው። ፈጣሪ ከሰማት እምዬን ኢትዮጲያ፣ ቆርጦም ከተነሳ ሊቆም ከእርስዋ ጋራ፣ አትዛል ወገኔ ሰልፉ የአምላክህ ነው፣ ለጠላትህ ሳይሆን መንበርከክ ለአምላክ ነው። ሰልፉ እንኳን አይሎ ቢመስል የበረታ፣ አይዞህ አትዘናጋ ከአንተ ጋር ያለው ይበልጣል ከሌላ። የሕዝቡን ጸሎት ሰምቶ ለመለሰ ጌታ፣ እንማጸነው አሁንም የጀመረውን ለውጥ እንዲሆን የጸና።
0 Comments

my Ethiopia Forum - Professor Berhanu Mengistu

8/14/2018

0 Comments

 
0 Comments

ደጉ ሳምራዊነት በህግ ተከልክሏል እንዴ?

8/12/2018

1 Comment

 
ላዕከ ታፈሰ 
​
እረ ለመሆኑ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ “እንካ” ሞቶ ተቀበረ እንዴ? ፍቅርስ ማለት ባዶ የቃላት ጫጫታ ነው እንዴ?

በየቦታው ወገኖቻችን እየተገደሉና እየተፈናቀሉ ናቸው:: ምነው ሀብታሞች: የሐይማኖት ተቋማት: የፖለቲካ መሪዎች: የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እጃችሁ ታጠፈ: ልባችሁ ጨከነ?

የዶ/ር አቢይን የይቅርታና የፍቅር መልእክትን ወድጀዋለሁ: የእርሱን አመራር እደግፋለሁ ያለ ሁሉ ፍቅሩንና ይቅርታውን ማሳያ የሆኑት ወገኖቹ ሲቸገሩ ለምን ዝም አለ? ደጉ ሳምራዊነት በህግ ተከልክሏል እንዴ? ወይስ ሃላፊነቱ የክልልና የፌዴራል መንግስት ነው? ወይስ መንግስት መረዳዳትን ወንጀል ነው ብሎ ፈርጆታል?

ወደ ቤተክርስቲያንና መስጊድ በየቀኑ የሚሄደው የኢትዮጽያ ህዝብ ከዚያ ሲመለስ ሌላውን መግደልና ማፈናቀልን ከማን ተማረው? የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወይ ፈጣሪህ የሚልህን ታዘህ የሰውን ልጅ በእኩልነት መመልከትና በተግባር መውደድህን አሳይ:: እሱንም ካልቻልክ የይስሙላ እምነትህን ትተህ የአገራችንን ህግ አክብር:: 

ዶ/ር አቢይ “ፓወር ፖይንት” አዘጋጅና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ መደመር: ይቅርታና ፍቅር ምን ማለት እንደሆነና ከእንግዲህ እያንዳንዱ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት: አንተም ከኛ ምን እንደምትጠብቅ እባክህ ንገረን:: ይህን በቶሎ አድርግልን:: ብዙ ሰው ይደግፍሃል እንጂ ፍልስፍናህን አልተረዳልህም ብዬ አምናለሁ::
1 Comment

my Ethiopia Forum - Interview Ato Abel Gashe

8/10/2018

0 Comments

 
አቶ አቤል ጋሼ የሁለት መፃህፍት ደራሲና በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ባለው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅዎ የሚያበረክቱ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የፃፏቸው መፅሃፍት The Wisdom Compass to Eternal Life እና GPS for America የሚባሉ ናቸው። 
0 Comments

my Ethiopia Forum - Interview Pastor Hailelehul Emiru

8/7/2018

0 Comments

 
Served in church planting, served in pastoral ministry for more than 20 years and still pastroing a congregation in Indianapolis, Indiana. Studied Theology, Greek and Hebrew languages and involved in Bible Translation.
0 Comments

    Amharic

    Archives

    January 2022
    October 2020
    August 2020
    April 2020
    November 2019
    September 2019
    July 2019
    April 2019
    November 2018
    October 2018
    September 2018
    August 2018
    July 2018

    Categories

    All
    Current Affairs
    Sport
    The God Factor Forum

    RSS Feed

Copyright © 1999 - 2023
  • ደወል