ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሁሉም ስለ ኢትዮጵያዊነትና ስለ ብዝሃነት ያወራል። ግን እነዚህ ቃላቶች የሚሰጡት ትርጉም ግን ጭራሽ የሚቃረኑና የሚጋጩ ናቸው። ለዚህ እንቅፋት የሆነው እነዚህን ቃላቶች ለመተርጎም አህዳዊ/ፌድራላዊ በሚሉት ቃላት በመተርጎማቸው ነው። ይህ ደግሞ ፖለቲካዊ ማምታታት ነው እንጂ ለመግባባት እንድንችል ቃላቶቹን በራሳቸው ለመተርጎም ሳይቻል ቀርቶ አይደለም። አህዳዊና ፌድራላዊ የሚሉት ቃላቶች የምንተዳደርበት የመንግስት አወቃቀር ይገልጣል። ኢትዮጵያዊነት እና ብዝሃነት ግን በራሳቸው የሚቆሙ እውነቶች ናቸው። ግን ፖለቲካዊ ማምታት መሠረታዊ የሆኑ መግባባቶች እንዲኖሩ አይፈልግም። የግል ፖለቲካ አጀንዳ ሲኖር አህዳዊ/ፌድራላዊ የሚል ታፔላ ለጥፎ በተጣመመ ትርጉም የሚያምታታና የሚያደናግር ሁኔታ ለመፍጠር በመጀመሪያ ቋንቋ በማደባለቅ ለመግባባት እንዳይቻል ያደርጋል። ስለዚህ ይህን ፅሁፍ በኢትዮጵያዊነት ፌድራላዊ አስተዳደር አውድ ውስጥ ለመፃፍ ተነሣሣው። ዓላማውም ሆን ብሎ ቋንቋችንን ከሚያደባልቀው የፖለቲካ አካሄድ ወጥተን አገራዊ መግባባት እንዲኖረን ኢትዮጵያዊነትን እና ብዝሃነትን በራሳቸው እንተርጉም። ይህንን ለማድረግ ቋንቋችን ሲደባለቅ የሚፈጠሩትን ሦስት አላቻ ጋብቻዎች በምሳሌነት እንጠቀም። ኢትዮጵያውነት ከዘረኝነት ስንወለድ በምርጫችን ሳይሆን ፈጣሪ በወሰነልን በየጎሣችን ውስጥ ተሰይመን ነው። ስንኖር ግን በምርጫ በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነን ስንል ያኔ ኢትዮጵያዊነት ገብቶናል ማለት ነው። በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነን ስንል፥ አብሮነትን ማስቀደማችን ነው። ከጎሣችን እና ከሰፈራችን ወጥተን በአብሮነት ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ፋና ወጊ እና ለዓለም ተስፋ እንድትሆን መስራት የምንችለው ያኔ ነው። አለበለዚያ ኢትዮጵያዊነትን ከዘረኝነት ጋር አጋብተን በመጀመሪያ ጎሣችንን አስቀድመን ስለ ኢትዮጵያዊነት ብናወራ የምናወራው ከተግባራችን ጋር እየተጋጨብን ተደናግረን እናደናግራለን። ምክንያቱም ጎሣችንን አስቀድመን የምንይዘው ኢትዮጵያዊነት እግራችንን ጠፍረን ጠፍንገን አስረን ስናበቃ እንሩጥ እንደ ማለት ነው። ጥያቄው ጎሣችንን እንፍቃለን ሳይሆን ማንን እናስቀድማለን ነው? የምናስቀድመው ኢትዮጵያዊነትን ከሆነ አብሮነትን የመጀመሪያውን ቦታ ሰጥተነዋል ማለት ነው። ያኔ ከሁሉም ጎሣዎች ጋር ለመያያዝና በአብሮነት ሃይል እንዲኖረን ምርጫችን አቅም ሰጠን ማለት ነው። ከዚያ ውጭ ኢትዮጵያዊነትን ከዘረኝነት ጋር አጋብተን ከተጠቀምን ወደሚቀጥለው አላቻ ጋብቻ ይወስደናል። ብዝሃነት ከተረኝነት ኢትዮጵያዊነትን ከዘረኝነት ጋር ካጋባን፥ ትንሽ ሳንቆይ ብዝሃነትን ከተረኝነት ጋር እናጋባለን። ያ ማለት በብዝሃነት ስም ጎሣችንን በሌላው ላይ ለመጫን እንዲያስችለን ኢትዮጵያዊነትን አጣመን እንጠቀምበታለን። ያኔ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ሳይሆን ራሳችንን እና ሌሎችን ይዘን ወደ ጥፋት መንገድ እንገሰግሳለን። ከዘረኝነት የተፋታ ኢትዮጵያዊነት ግን ብዝሃነትን ከተረኝነት አፋትቶ በትክክለኛው መንገድ ይተረጉምልናል። በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነን ማለት አብሮነታችንን ማስቀደማችን እንደሆነና ብዝሃነት ለዚህ ምስጢር እውነተኛነት ምክንያት ነው። ለኢትዮጵያዊነት (አብሮነት) የሚረዳን ብዝሃነት ነው። ምክንያቱም በኢትዮጵያዊነት አውድ ውስጥ ብዝሃነት በእኩልነት እንድንስተናገድ ያደርገናል። አለበለዚያ ኢትዮጵያዊነትን ከዘረኝነት ጋር አጋብተን የጀመርነው ጉዞ፥ ብዝሃነትን ከተረኝነት ጋር ማጋባት ብቻ ሳይሆን ወደ ሦስተኛው አደገኛ አላቻ ጋብቻ ይወስደናል። አሰተዳደር ከሌብነት ሌብነት በአንዳንድ ሰዎች እጅ ሲሆን ሌብነትን ለማጥፋት ቀላል ነው። ግን ሌብነት ከአስተዳደር ጋር ከተጋባ፤ እኛ ሌብነትን ሳይሆን የምናጠፋው ሌብነት ነው ሁላችንንም የሚያጠፋው። ምክንያቱም ማሰርና መጠየቅ የሚችለው ባለስልጣን ሁሉ ሌባ ከሆነና ሌብነት ባህል እስኪሆን ታግሰን ስር ከሰደደ በየት በኩል ነው መፍትኤ የሚመጣው? በተለይ አስተዳደሩ ኢትዮጵያዊነትን (ኢትዮጵያን ማለትም አብሮነትን የማያስቀድም) እና ብዝሃነት (ሁሉም በእኩልነት የሚስተናገዱበት) ባልሆነበት አውድ ውስጥ ከሆነ ሌብነት ፍፁም ወደማይድን በሽታነት ይቀየራል። ለዚህ ሁሉ መውጫው መንገድ ከኢትዮጵያዊነት እና ከብዝሃነት ቃሎች ጀርባ ለቃላቶቹ ያለን ትርጉምና ግንዛቤ በእውነት ላይ የተመሠረተ ስናደርግ ነው። ያኔ የምንናገረውና የምንተገብረው ይጣጣማል፥ ደግሞም ከመደናገር አውጥቶን ግልዕ አቅጣጫ ይሰጠናል፥ አንድ ልብም ይፈጥርልናል።
1 Comment
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በዙሪያችን የምናያቸው ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብሎ ስለሚያስተጋባ፥ ስጋታችን ለባለ አዕምሮ ሰው ትክክል ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ በዓይነ ሥጋ ከሚታየውና ከሚሆነው ትዕይንት ጀርባ ያለውን እውነት ለሚያስተውል ሰው፥ የኢትዮጵያ ትንቢት ፍፃሜ ዋዜማ ላይ እንደሆንን ፍንትው ብሎ ይገለጥለታል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ሲባል ምን ጠብቀን ነበር? ኢትዮጵያ እጆቿን የምትዘረጋበት አውድ ሁለት ምዕራፍ አለው። አንደኛው ምዕራፍ በመጀመሪያ የሚሆን ሲሆን፥ ሁለተኛው ምዕራፍ ራሱ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሚወልደው ነው። ወደ እግዚአብሔር የመጀመሪያው እጅ መዘርጋት ምዕራፍ ለፈጣሪ መሸነፍንና በእርሱ መታመንን ያመለክታል። ሰው ተንበርክኮ እጁን ወደ ፈጣሪ ሲዘረጋ፥ መማረኩንና ረድኤትን ከላይ መጠበቁን ያሳያል። እጅ መዘርጋቱ፥ “ተስፋችን አንተ ነህ”ብሎ እርዳታ ከላይ እንደሚመጣለት ማወቁን ያመላክታል ። የዚህ የመጀመሪያው የእጅ መዘርጋት ምዕራፍ፥ ገሀዱ ዕይታ የሚያመለክተው ምስኪንነትን ነው። ፈተናችን ከአቅማችን በላይ ሆኖ ሲያንገዳግደን፥ እንዳንሻገር የሚከለክሉ ተግዳሮቶች በግራና ቀኝ ሲያይሉብን፥ የሚመለከተን ሁሉ በመፍረስ አፋፍ ላይ እንዳለን አድርጎ ሊቆጥረን ይችላል። በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ እጆቻችንን ወደ ፈጣሪ ዘርግተን በእምነት እንደምንሻገር ስንናገር አንዳንዶች የማይገባቸው ለዚህ ነው። በዚህ ጊዜ መደገፊያችን እና ትምክዕታችን ፈጣሪን አድረገን አንገታችንን ቀና ስናደርግ፥ ከትእቢት ይልቅ ትህትና እንደሚያሸንፍ የምናውቀውና፥ በዚህ የመጀመሪያው የትንቢት ፍፃሜ ምዕራፍ ውስጥ የሚያለመልመን በፈጣሪ ላይ ያለን እምነት ሲሆን፥ ያም እምነት ጉልበት የሚሆነን በእውነት መነፅር ኢትዮጵያን ማየት ስንችል ብቻ ነው። ይህን የጨለማ ጊዜ በመጀመሪያው እጃችንን የመዘርጋት ምዕራፍ በፈጣሪ ከተሻገርን በሁዋላ፥ ሁለተኛው እጅ የመዘርጋት ምዕራፍ ይወለዳል። ያም እጆቻችንን ዘርግተን በረከቱን የምንቀበልበት የመታደስ ዘመን ነው። በዚህ በሁለተኛው የእጅ መዘርጋት ምዕራፍ፥ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እንደ ምልክት አድርጎ እንድታበራ የሚያደርግበት የጉብኝት ወቅት ነው። ፈተናችን ሊያጠራን እና ወደ ከፍታችን ሊያወጣን እንጂ ሊያጠፋን የማይችለው ምክንያት፥ ፈጣሪ ስላለና ስለሚረዳን ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት ከመሬት ተነስተን፥ ማማ ላይ ስንታይ፥ ክብርን ለፈጣሪ እናመጣለን። እናት ምጥ ላይ ስትሆን በጭንቋ ተስፋ አትቆርጥም፥ ይልቁንም የሚወለደውን ሕፃን ለመታቀፍ ትናፍቃለች። እኛም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኩራት እና ለዓለም ተስፋ ሆና ከወደቀችበት ቀና ብላ ቆማ እጆቿን ዘርግታ ልትሞሸር ያለችበት ወቅት በደጅ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን፥ የዛሬው በስብራታችን እና በጨለማችን እጆቻችንን ወደ ኢትዮጵያ አምላክ መዘርጋታችን ነው። ዛሬን ተሰብረን ባዶ እጃችንን ሆነን እጆቻችንን ዘርግተን እርዳን ብለን ስንጮህ፥ ፈጣሪ ወርዶና ፈርዶ የተዘረጉትን ባዶ እጆች በበረከቱ ነገ እንደሚሞላ ሁሉም ይወቀው። ሦስት ሽህ ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ትንቢት ዛሬ በዓይናችን ፊት እየተፈፀመ እያየን፥ በድንዛዜ ሆነን ለምን እንጨነቃለን? አይሁድ የክርስቶስን መምጣት ለዓመታት ሲጠብቁ ቆይተው፥ ጌታ ሲመጣ የገባቸውና የሰማይ ደስታን የተቋደሱት ጥቂት እረኞችና መንገደኞች ነበሩ። ዛሬም ለዝንተ ዓለም ስንጠባበቀው የነበረው “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለው ትንቢት ለመጀመሪያ ጊዜ በገሀድ መፈፀም እየጀመረ መሆኑን እያየን ስለሆነ፥ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው ብለን በመጨነቅ ፈንታ፥ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ልትወለድ ነው በሚል እምነት እንፅና። ፈጣሪ ከመሬት ያነሳቸው የዘመናችን ታላላቅ ሀገሮች፥ ጀርባቸውን ለፈጣሪ በሰጡበት በአሁኑ ወቅት፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራ ትግራይ ኦሮሞ ጉራጌ ሶማሌ አፋር ወዘተ ሳይል ሁሉም፥ ግኡዙን ምድር ጨምሮ፥ የፈጣሪን ረድኤት በየዕለቱ በአደባባይ ሲማጠኑ ማየት ትልቅ ምስጢር ነው። የነገው ትልቅነት ዛሬን በፈጣሪ ተደግፎ ለቆመ ደካማ የተመደበ ሲሆን፥ የነገው ውርደት ደግሞ ዛሬን በትዕቢት ተነፍቶ ለቆመ ሃያል የተመደበ ነው። ይህን እውነት ለሚያስተውል፥ ወደ ብሩህ ተስፋችን እየተገፋን እንደሆነ ይታየዋል። ዋናው ቁምነገር ትንቢቱ የመፈፀሚያው ጊዜ ደርሶ፥ ፈጣሪን በአደባባይና በየቤታችን፥ በየቤተ እምነታችንና በየባለስልጣናት ሰፈር፥ ሃይማኖት ሳይለይ፥ ትልቅ ትንሹ ፈጣሪን እየተጣራ መሆኑ ነው። እኛ ከተሸነፍንለት፥ አምላክ እንደሚያሸንፍልን ለዘመናት የፀና እውነት ነው። እጆቻችንን መዘርጋት ላይ ስለደረስን፥ በዚህ ብቻ ደስ ይበለን። አምላክ የሚታመኑትን አሳፍሮ አያውቅም። ከሁኔታዎቻችን ላይ ዓይናችንን አንስተን፥ ሰዓቱ ሞልቶ እጆቻችንን የመዘርጋት ምዕራፍ መጀመራችንን እያየን፥ የፈጣሪን ክብር ለማየት በመጠባበቅ በደስታ ወደ የሥራችን እንሰማራ። ፍርሃቴ የመጎብኘት ዘመን አይመጣ ይሆናል የሚል ጥርጥር ሳይሆን፥ መጎብኘታችን የማይቀር የሚፈፀም የፈጣሪ ተስፋ እንደሆነ በማወቅ፥ እርግጠኝነት ላይ በመድረስ፥ ያኔ ስንጎበኝ እኛም በጊዜያችን ፈጣሪን እንዳንረሳ ነው። ለዚህም ይሆናል ምኞት አይከለከልምና የፈጣሪን ውለታ ማስታወሻ እኛ ደግሞ በሰንደቅ ዓላማችን ላይ የተዘረጉ እጆች እንዲያርፉበት እናደርጋለን ብዬ የምፀልየው። ኢትዮጵያ ታላቅ ስትሆን፥ ከመፍረስ ታድጎ ለታላቅነት ያበቃትን አምላክ ያኔ በክብር ታከብረዋለች። አምላክ ምልክት አድርጎ ለአርአርያነት ሲያበቃት፥ ያኔ እኛም በፈጣሪ ስር እንዳለ አንድ ቤተሰብ ሆነን እንገለጣለን። በእውነት መነፅር ኢትዮጵያን ስንመለከት፥ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብሎ ለመስጋት እንዴት ይሆንልናል? እውነት፥ ለውርደት የምትፈርስ ኢትዮጵያን ሳይሆን ለክብር የምትወለድ ኢትዮጵያን ያሳያልና! ለማግኘት፦ www.myEthiopia.com ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በፊታችን ያለው መንታ መንገድ፥ አንዱ መንገድ ዶ/ር አብይን እየደገፍን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የምንሄድበት መንገድ ነው፥ ሌላኛው ኢትዮጵያን ለመበተን ሌሎች የሚሄዱበት መንገድ ነው። ከዚህ ውጭ ሦስተኛ መንገድ ሊኖር አይችልም። የውስጥ ልዩነታችንን በምርጫና ምርጫ ብቻ እንዳኘዋለን። ከዚያ ባለፈ ራሱን ዶ/ር አብይን እንሞግተዋለን እንጂ በስመ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ አንጮህም። ምክንያቱም ሦስተኛው መንገድ አንድነት እንዳይኖር ውዥንብር የሚፈጥር ነውና አይጠቅመንም። ወደምንናፍቀው ከፍታ ኢትዮጵያን በቤተሰብነት አውድና ብልፅግና ውስጥ ሊያስገባት የሚያስቸለው መንገድ ራሱ ዶ/ር አብይ ባይሆን እንኳን ለዚያ በሚያበቃ ቁመና እንድንደርስ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደ ምርጫ ያደርሰናል። ዶ/ር አብይን ዛሬ ዛሬ የሚደግፈው ሰው አማራን ይበልጥ የሚወድ፥ ወይም ኦሮሞን ይበልጥ የሚወድ፥ ወይም ሌላ የራሱን ብሔር አብልጦ የሚወድ ወይም ኢትዮጵያን የሚወድ ሊሆን አይችልም። ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል? ብንል ከአጀማመሩ እንመልከት። የዶ/ር አብይን ንግግር ሰምቶ ያልወደደው ፍጡር የለም ማለት ማጋነን አይደለም። ንግግሩ ከስብዕናው የወጣና ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ራዕይ ሰንቆ፥ አርቆ በማየት ምን ማድረግና ምን መሆን እንደምንችል ፍንትው አድርጎ ሲተርክልን ያልተማረከ አልነበረም። ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉንም አስታርቆ፥ ዲሞክራሲን ላዋልድ ብሎ በጎነቱ ድክመቱ ቢሆንበትም ቅንነቱ ታይቶ፥ ተረት ተረት የሚመስለው የኤርትራ ዕርቅ እውን ሆኖ የኖቤል ሰላም ሽልማት አስጨብጦት፥ ጉድ ድንቅ እየተባለ ሳለ፥ ግና ተራ በተራ በየፌርማታው ወራጅ አለ እየተባለ ዛሬ መንታ መንገድ ላይ ደረስን። በመጀመሪያ በእርቅና መግባባት ፍቅር ማውረድ ሲቻል ሆን ተብሎ የታሪክ ዕዳ በጥላቻ ማወራረድ ተመረጠ። ሲቀጥል በሕወሃት ሃያ ሰባት ዓመታት አብሮነታችንን የሚሸረሽር መሠሪ ትርክት በትውልድ ላይ ተቆመረ። ይህ ሳያንስ በየተለያየ አቅጣጫ ሁሉም በየብሔሩ ጎራ ተሰልፎ ዶ/ር አብይን ወዲያና ወዲህ ይጎትታል። ያም ሆኖ ዶ/ር አብይ ሁሉንም ያመረቀነውን ራዕይ ወደ ተግባር ለመቀየር በሚሄድበት አዲስ ጎዳና በትልቅ ትዕግስት፥ ከስህተቱም እየተማረ እየነጎደ ይገኛል። ለምሳሌ ያህል፥ አንድ ሰሞን አዲስ አበባ የማን ናት ተባለና ተባላን። ጠቅላዮ ጭቅጭቁን ለእኛ ትቶ አዲስ አበባን ማስዋብ ጀመረ። አብሮነታችንን፥ ታሪካችንን፥ የተፈጥሮ ፀጋችንን በአማከለ ሁኔታ ምን ልንሆን እንደምንችል በአዲስ አበባ ከተማ ዘወትር በሥራ እየታተረ ይገኛል። በጊዜ ሂደት ልብ እንደምንገዛና አብሮነታችንን እንደምናገዝፍ በራዕዩ ሃይል የታመነ ይመስላል። ዶ/ር አብይ የኦሮሞን ጥያቄ አልመለሰም ብለው የኦሮሞ ሊሂቃን ይዋጉታል። ሌሎችም በብሔራቸው ቆመው እንደዚሁ ያደርጋሉ። የሚገርመው የዶ/ር አብይ አካሄድ የዛሬን ጥያቄ መመለስ ብቻ ሳይሆን፥ የነገን ጥያቄ በመመለስ ሂደት ላይ ጭምር ነው። ተላለፍን። እኛ ተፈትነን ስናንገራግር፥ የኢትዮጵያ አምላክ ዶ/ር አብይን እስካሁን ረድሔቱን አልሰሰተበትም። ወደቀ ስንል እየተነሳ፥ ኢትዮጵያ ጠፋች ስንል እያመለጠች፥ አባይም እየተሞላ፥ ወደፊት እየተባለ ነው። አሁን ላይ ግን ዶ/ር አብይን ለመውደድ፥ አብሮነታችንን መውደድ ብቻ እንደሚጠይቅ አያጠራጥርም። መንገዱ ተራራና ሸለቆ የሞላበት ነው። ተራራው ላይ ስንደሰት፥ ሸለቆ ውስጥ ስናዝን፥ መሄዳችን አሁንም አይቀርም። ግን ዶ/ር አብይን ለመደገፍ መንገዱን ሳይሆን አድራሻችንን (ራዕዩን) ማየት አለብን። በደመና ላይ ያንሳፈፈን ራዕይ፥ መሬት ሲወርድ ውጣ ውረድ አለው። በዚህ ላይ ሰው ነውና የዶ/ር አብይ ድክመት ተጨምሮ፥ ብዙ ፈተና አለው። በተጨማሪ ይህ ጉዞ ብዙ ጠላቶች መንገድ ላይ ሊያስቀሩን ምሽግ ይዘው የሚዋጉን ጭምር በመሆኑ እጅግ አድካሚ መሆኑ የታወቀ ነው። ታዲያ መዳረሻችን የሆነው ራዕይ ለሁላችንም የምትበቃ ብቻ ሳይሆን፥ ለአፍሪካና ለዓለም የምትተርፍ ኢትዮጵያን ለማየት ዶ/ር አብይን መደገፍ ኢትዮጵያዊነት ነው። ምርጫችን አብሮነታችን ይሁን። የአብሮነታችን መንገድ ደግሞ ዶ/ር አብይ ነው። ስለዚህ ያለምንም ማመንታት መደገፍ ይሁንልን። ስናመነታ እንዳንመታ። ፈጣሪ እንደሆነ ለኢትዮጵያ መድረሱን ቸል ብሎ አያውቅም። ድርሻችንን እንወጣ። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ሲጀመር ሁላችንም የአብይን ንግግር ወደን አብይን ደገፍን። አሁን ደግሞ ሁላችንም ኢትዮጵያን ወደን አብይን የምንደግፍበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ መጨረሻዋ ምን ይሆን ብለን ስንሰጋ መንታው መንገድ ላይ ደረስን። አንደኛው ኢትዮጵያ የምትቀጥልበት አቀበት ሲሆን፥ ሌላኛው ሞቷ የታወጅበት ቁልቁለት ነው። መሀል ሰፋሪ መሆን ከእንግዲህ አይቻልም። ፖለቲካ አያገባኝም ማለት ዘበት ነው። የምንደግፈውን ፓርቲ ወደ ስልጣን እንዲመጣ የምንሮጥበት ጊዜ አሁን አይደለም። የዛሬው ምርጫ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ላይ የሚወስን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያን ሊያጠፋ ከመጣ እኩይ ተንኮል፥ ወጥመዱ ተሰብሮ ኢትዮጵያ የምታመልጥበት ወሳኝ ሰዐት ነው። ስለዚህም ዶ/ር አብይን መደገፍ ኢትዮጵያን ማሻገር ነው። ሳይበላ እያበላን ያስተማረንን ድሀ ባለ አገሩን እናስብና ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም። ሀገር ከሌለ፥ እንዳለን አይቆጠርም። ስለዚህ በቃል በፀሎትና በሥራ ከጎኑ እንቁም። ኢያሪኮን ያፈረሰው ድምፅ ነው። ምክንያቱም ከድምፁ ጀርባ ፈጣሪ ነበርና። ለዶ/ር አብይ አጋርነታችንን ስናሳውቅ፥ ፍቅርን አብሮነትንና ቤተሰብነትን መምረጣችን ነው። ይህም ድምፅ ብርሀን የሆነ ነው። ጨለማ የሆነው የአጥፊውን ሴራ ስፍራውን የሚያስለቅቀው የብርሃን ድምፅ ነው። እኛ ተነስተን ድርሻችንን እንወጣ፥ ማዳን ከፈጣሪ ይሆንልናል። የሚንጫጫው የጥቂት ፅንፈኞች ድምፅ ፀጥ ይላል ብለን አንጠብቅ። ይልቁንስ አድፍጦ የተኛው ብዙሃኑ ዝምተኛ ድምፁ ይሰማ። አንበሳው ሕዝብ ያግሳ። ያ ጥቂት አጥፊ ድምፅ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስብዕና እንደማይወክል ይታወቅ። በቃ! ይሁን አሜን። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የኢትዮጵያ ችግር በሰው ሰራሽ ትርክት ኢትዮጵያዊነትን በመሳል ኢትዮጵያውያንን መመረዝና እርስ በርስ ማጫረስ ነው። በዚህም እኩይ ተግባር የተለከፉ፥ ጭራቅ እንኳን ሊሰራው የማይችለውን አሰቃቂ ግድያ ሲፈፅሙ ስናይ፥ የኢትዮጵያዊነት ማንነት የሆነው ፍቅርና ርህራሄ ላይ ያለንን ግንዛቤ እንዳይበርዙብን እንጠንቀቅ። ምርጥ ልጆቿን መቅበር እስከ መቼ እያልን ስንቆዝም፥ አይ ኢትዮጵያ! እንዳይታረቁ ሆነው የተጠመዱ፥ እንዳይፈታ ሆኖ የተቋጠሩ፥ እንዳይታይ ሆኖ የተሰወሩ ትርክቶች ተመርዛ ሞት እየሸተታት፥ እኛ ዲሞክራሲና ልማት ስንዘፍን ተዘናግተን፥ ፈጣሪ ደረሰልን! ከእንግዲህ መርዙ እስኪነቀል፥ ያልተፈታን ቋጠሮን መፍታት፥ ያልታሰበን አስተሳሰብ ማሰብ፥ ያልተሄደበትን መንገድ መሄድ ሥራችን ይሁን። የሕዝቡ ማንነት የሚገርም ነው። በመሪዎቻችን ማንነት ሕዝቡ ማንነቱን ተጠልፎ መነጋገሪያ የሆነው የሊሂቃን ትርክትነው። ማን ያውራ ስለደጉ ሕዝብ? ማን ያውራ በፍቅር ስለሚተሳሰበው ሕዝብ?ሲራብ አብልቶ፥ ሲጠማ አጠጥቶ፥ አብሮ ተቻችሎና ተጋብቶ ለዘመናት የሚኖረውና የሚያኖረው ሕዝብ ማንማንነቱን ያራግብለት? ያደከመን በመሪዎቻችን ማንነት ላይ የተመሰረተ የፊት ለፊት ወሬ እያወራን ስጋታችን መብዛቱ ነው። ሁሉም ዓላማውን የሚያራምደው ኢትዮጵያን የመሪዎቻችን ነፀብራቅ አድርጎ በመውሰድ ነው። ከላይ ላይ ከሚታየው ጀርባ፥ የተደበቀውና በጊዜ ተፈትኖ ያለፈው ትልቁ ጥልቅ እውነት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተሰብነት ነው። እኛ የወለድናቸው ልጆቻችን ለኢትዮጵያ ምን ሊያደርጉ ይቻላሉ ተብሎ ቢታሰብ ከአዕምሮ በላይ ነው። ልጆቻችን የእኛን መባላት ከማየት ይልቅ ፍቅራችንንና ሰላማችንን እንዲያዩ ብንፈቅድላቸው፥እነሱ ለኢትዮጵያ ለመድረስ ይበቃሉ። እኛ ሁሉን አይተን የዕድላችንን ሞክረን አንገት ለአንገት ተያይዘን ከመሬት አልተነሳንም። አሁን ግን ለልጆቻችን ዕድል ፈንታ እንሰጥ ይሆን? ዛሬ አዲስ ጅማሬ አቅቶን ተቸገርን። ነገር ግን ሌላው ቢቀር ነገ ልጆቻችን ኢትዮጵያን ሳትሰነጣጠቅ ማስረከብ እንኳን ብንችል፥ እነርሱ አዲስን ነገር ያሳዩን ነበር። ታዲያ ካለንበት አዘቅት ለመውጣት መተባበር አቅቶን ይህችን ኢትዮጵያ ሀገር እንዳትሆን እያደረግናት ይሆንን? እንዲያው አምሳአመት እንኳን ወስዶብን ከድሮ የተለየ አሰራርና አስተሳሰብ ለማሳየት ችለናልን? እንዲያው ይህችን ሀገር አጥፍተን ካልጠፋን አንነቃምን? ልጆችን የራሳቸው እድል እንዳይሞክሩበት መና ልናስቀራቸው ነውን? ኢትዮጵያ የሕዝቡ ውጤት እንጂ የመንግስታት ፍሬ አይደለችም። መንግስት ይመጣል፥ እንደመጣም ይሄዳል። ቋሚ ነገር ሕዝቡ ነው። እውነተኛውና የሚፀናውን ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጠው ሕዝብ ነው። የኢትዮጵያ ጠባቂ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያ ሕዝቡን ስለሚወክል በራሱ እፁብ ድንቅ ነው። ሕዝቡ የኢትዮጵያን የነገውን እጣ ፈንታ ይወስናል። ማንም ኢትዮጵያን ለማወቅ ሩቅ አይሂድ፥ እናቱን ይመልከት (ከአብራኳ ወጥቷልና)። ኢትዮጵያ ላይ ቆሞ፥ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ መርዝ እየረጩ፥ ስለ ኢትዮጵያ መፃኢ ዕድልና ፈንታ ማውራት የዲሞክራሲ መብት መጠቀም ሳይሆን፥ ሕግ አልባ በሆነ “ሀገር” መንደላቀቅ እንደሆነ የሚታወቅበት ጊዜ ያመጣ ፈጣሪ ምስጋና ይግባው። መሰሪዎችየሳሉልንን ትርክትይዘን ሰጣ ገባ ስንገባና ኢትዮጵያን ጥያቄ ውስጥ ስናስገባ፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት ለመቀበል እድልና ፈንታ እንዳይኖረን እያደረገን ነው። ይህንንም ስናደርግ ኢትዮጵያን ጥያቄ ውስጥ ማስገባታችን፥ሕዝቡን ራሱን ጥያቄ ውስጥ ማስገባታችን እንደሆነ ስለማናስተውል ነው። ለዚህም ስህተት የሚዳርገን፥ መሰሪዎቹ ትርክታችንንየሚመሰርቱትመንግስታት ባደረጉት ድርጊት ላይ የሚስሉልንንኢትዮጵያን ተመርኩዘን ስለሆነ ነው። ይህን ስናደርግ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከሕዝቡ ነጥለን መንግስታትን የኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ፈጣሪ አድርገን መፈረጃችን እንደሆነ ይታወቅ። ይህን በማድረጋችን፥ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነትሕዝቡ ያለውን አብሮነት ዋናውን ስፍራ አለመስጠት ይሆንብናል። የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ፅናት ግን የሕዝቡ ውጤት ነውና ሕዝብ እስካለ ድረስ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል። እውነተኛው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሊሂቃንበራሳቸው ዕይታ የሚስሉት ማንነት አይደለም። በራሱ በሕዝቡ የተገነባ ከመንግስታት ተነጥሎ በራሱ የቆመ ማንነት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ፈተና ላይ ጥሎ፥ የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ እያጠጡ፥ በዲሞክራሲ ስምኢትዮጵያን የመግደልዘመቻ ተነቃ። እውነተኛው ኢትዮጵያዊነት እኛ ወይም ሌላው በፍልስፍና የሚፈጥረው ነገር ሳይሆን፥ ራሳችንን (ሕዝቡን ማንነቱን) የሚተርክ እውነታ ነው። ያም የተዋበና የሚገርም ነው። እውነታው ስለ ሕዝቡ ይናገራል። የኛ ጥረት የሊሂቃንን መነፅር ከአይናችን ላይ አውልቀን የሕዝቡን ውበት እንደ ነበረና እንዳለ መመልከት መቻል ላይ ነው። ያኔ የተሰወረውን እውነተኛውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማወቅና ለማሳወቅ ይቻለናል። እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ለመተዋወቅ ከሕዝቡ እንጀምር። ሕዝቡ እውነተኛ ቅንና በጎ ነው። በጎና መልካም የሆነው ይህ ሕዝብ ማንነቱን ለማንፀባረቅና እርሱነቱን ለማብራት ያልቻለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ለዘመናት ያለው። ኢትዮጵያዊነትን ከሕዝቡ ስብዕና ላይ ተመርኩዘን ለማወቅ ብንጥር ቤተሰብነትን ያሳየናል። ስለዚህ ጥረታችንና ሕልማችን ይህንን እውነተኛውን ማንነታችንን ለማወቅ ይሁን። ልዩነታችን ውበታችን ሆኖ ይታየን። እኩልነት የእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ስርና መሰረት እንደሆነ ይታወቀን። ራዕያችን እንደሆነው እንድንታወቅ ይሁን። እንደ ማንነታችን ሁሉ አቅማችንም ያንን ያህል ታላቅ መሆኑ ይግባንና ለካ ምንም አልሰራንም ብለን እንቆጭ። በዚህም ቁጭት እውነተኛውን ራሳችንን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን እውነተኛው አቅማችንንም መግለጥ ይብዛልን። እስቲ የራሳችንን እውነተኛውን ማንነት ማወቅና መረዳትን እናስቀድም። የቤት ስራችን ኢትዮጵያዊነትን ማፍረስ ሳይሆን ያልተገለጠልንን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ማስተዋል ላይ ያተኩር።መሰሪዎችየሚስሉት ኢትዮጵያዊነት ላይ ተወስነን ኢትዮጵያዊነትን አንኮንን። ይልቁንም በሕዝቡ ልብ የተሰወረውንና በየዕለት ኑሮው የሚተገበረውን ኢትዮጵያዊነት ከሽፋኑ አውጥተን ለዓለም ለማሳየት እንጣር። ፍርሃት ሳይሆን ፍቅር የሚገዛው እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት እናውጅ። አለመተማመን የሚነዳንና የሚያናቁረን እንዳይሆን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ማወቅ ቤተሰብነታችንን አስረድቶን አዲስ ምዕራፍ ይክፈትልን። ቁምነገሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን የምንጥር ሳንሆን፥ ኢትዮጵያዊ ስለሆንን ያንን የማወቅ ጉዞ ላይ መሆናችንን ማስተዋል ላይ ነው። የሆንነውን ሆነን ለመገኘትና የተሰወረውን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት በገሃድ ለመግለጥ ራሳችንን እናነሳሳ። የኢትዮጵያ አንድነት የሚመነዘረው በሕዝቡ አንድነት እንጂበሊሂቃን ተብየዎች አይደለም። እርስ በርስ መያያዛችን ከራሳችን ከውስጥ የመነጨ ነው እንጂ ከውጭ ሌላው የሚጭንብን መከናወን አይደለም። መሰሪዎችበኢትዮጵያዊነት ላይ የጣሉትን ሽፋን ገልጠን፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት በማንፀባረቅ እንደ ሆንነው በዚያኑ እንድንታወቅ ራዕያችን ይሁን። ያም ለዓለም ድንቅና መገረም እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያዊነት ላይ ጎራ ይዘን ከምንተራመስ፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ የምንማርበትን ሂደት ላይ ግድ ቢለን መልካም ይሆንልናል። ይህ ቢበዛልን፥ የአፍሪካ ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ የዓለም ተስፋ እንድትሆን በር ይከፍትላታል። ስለ አንድ ኢትዮጵያ ከመጨቃጨቅ አልፈን ስለ አንድ አፍሪካ ፈር ቀዳጆች ለመሆን እንድንታደልምያደርጋል። የኢትዮጵያ ነገር እንቆቅልሿ የሚከብደው ጉዳዩ የውስጥ ብቻ ስላልሆነ ነው። ለሁሉ ነገር ወዳጅና ጠላት እንዳለ ሁሉ፥ ኢትዮጵያም ወዳጅና ጠላት አላት። አሻፈረኝ ብላ የጥቁር ሕዝብ ተስፋና ኩራት መሆኗን የሚያደንቁ እንዳሉ ሁሉ ነርቫቸውን የሚነካም አይጠፋም። የብዙዎች መተዳደሪያ የሆነው የውሃ ስርና መሰረት ጥንስሱ አባይ ከኢትዮጵያ ስለሚነሳ በዓይነ ቁራኛ መታየቷ አይቀሬ ነው። በዙሪያዋ እየተተራመሱ በመካከል እንደ ወጥ ቁጭ ብላ በእድገት ልትመነጠቅ የምትንደረደር ኢትዮጵያን ማየት የማይመቻቸው ይኖራሉ። በተለይ ሽብርተኛውን ከአሜሪካ ጋር እየተባበረች በአካባቢዋ አከርካሪ ሰባሪ መሆኗ ጥቁር ነጥብ በጠላቶች ዘንድ ማስጣሉ አይቀርም። ምዕራቡ ዓለም ከእጅ ወደ አፍ እርዳታ እያደረገ ለዘመናት ኖሮ ሳለ ዛሬ ቻይና በኢኮኖሚው ላይ ጫና ያለው የመሰረታዊ ልማት እንቅስቃሴ እንድታደርግ በተደረገውም ስራ ኢትዮጵያ ከተኛችበት የተነሳች እስክትመስል የሚታይበት ሁኔታ ሌላ ጠላትነት የሚያፈራ ሊሆን ይችላል። ይህ እንግዲህ በውስጥ በራሳችን ልጆች ከሚመጣው አለመግባባት መዘዝ ከሚደረገው የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው አካሄድ ጋር ሲደመር ነው ቋጠሮዋ የሚጠብቀው። የኢትዮጵያ ቋጠሮ ባለን ሁኔታና በሚጠብቀን ዕድል መካከል ያለው ውጥረት ነው። ያለንበት ስፍራና ልንሆንበት የሚጠራን ከፍታ አይገናኙም። በአንድ ዓይነት ሃይማኖትና በአንድ አይነት ብሔር የተዋቀረችው ሶማሊያ ከመፈራረስ አንድ አይነት መሆኗ አላዳናትም። አሜሪካ በሌላ በኩል ከዓለም ዘር ሁሉ የተውጣጡ ሕዝቦችን ይዛ በእግዚአብሔር ስር ያለ አንድ ሕዝብ ያውም ሊከፋፈል የማይችል በማለት ይምላሉ። ልዩነትን አስተናግደው ከዓለም የሚያስንቅ ዲሞክራሲን ለማራመድ ችለዋል። ይህ ሁሉ የሚያሳየን እንደ ትልቅ ነገር ይዘን የምንቆራቆስበት ትርክቶችከመጠላለፍ ያለፈ ያደረገልን ነገር የለም። ሕገመንግስታችን የትላንትን ፍርሃት የሚናገር እንጂ የነገን ራዕይ የሚያውጅ አይደለም። ትላንት ስለተበዳደልን ዛሬ እስከ መገንጠል የሚል መብት አስቀመጥን። የምንተነብየው ያ ነገር ይሆናል። ዛሬ ላይ ቆመን ነገን ስናይ ምን ይታየናል? ፍርሃታችን ሳይሆን ተስፋችን እንዲመራን ለምን አላረግንም? አንድ ሕዝብ ተብለን የሕዝቦች መብት አለመጠበቁን ለማስመር ሕዝቦች ብለን ለምን እንደመድማለን? ለመሆኑ ተጋብተን ተዋልደን የኖርን አይደለምን? መሬት ታች አውርደን ካየን እንደ ወንድምና እህት ተከባብረን ስንቱን አብረን አሳለፍን? ደግነት እና ትህትናችን ለምን ዋጋ አጣ? አብረን ደምተን ዳር ድንበር አስጠብቀን፥ እስላምና ክርስቲያን ተባብለን ሳንገፋፋ አብረን ስንቱን አሳለፍን? መንግስታት ሲቀያየሩብን ድህነት እና ችግርን እርስ በርስ ባንረዳዳ እዚህ እንደርስ ነበር ወይ? ሲሆን ሲሆን ኢትዮጵያ አንድ ሕዝብ ናት ማለቱ ራሱ ስህተት ነው። ምክንያቱም አንድ ቤተሰብ ነንና። ብዙ ሰው መላ ሲሰጥ ይታያል። ያ መላ መልካም ሆኖ ሳለ፥ ጆሮ ሰሚ ሳያገኝ በግራና በቀኝ መንገድ ላይ ወድቆ ባከነ። ችግራችን የመፍትሔእጦት አይደለም። የመግባባት መተላለፍ እንጂ። ስለዚህ መግባባትን ከመጨረሻው ላይ ቆመን ከመፍትሔው ጎራ ከመፈለግ፥ ግና ከመጀመሪያው ከችግሩ ጥንስስ ላይ ቆመን የችግሩን ስም በማውጣት ላይ እንስማማ። የችግራችንን ስም ሁላችንም የተስማማንበትን ስም አውጥተን ስናበቃ፥ያ የችግሩ ግንዛቤ መግባባት አንድ ቋንቋ ይሰጠናል። ያኔ ችግሩ ላይ ከተስማማን ሁላችንም ከአንድ ስፍራ እንጀምራለን ማለት ነው። በአንድ ስፍራ ለመሆናችን ምክንያቱ መላ ስላገኘን ሳይሆን ቋጠሮውን በአዲስ ግንዛቤ ስለገነባነው ነው። ያኔ ሁላችንም ቋጠሮውን ለመፍታትከአንድ ስፍራ ስለምንነሳ ወደ አንድ አቅጣጫ ለመሳተፍ ይቀላል። ኢትዮጵያ የታሪክ እስረኛ አይደለችም። ምክንያቱም ከታሪክ ተምረን አዲስን አቅጣጫ ለነገ ዛሬ መተለም ይቻለናልና። ይልቅስ መርዝ ሆኖ የተቀመመው ሰው ሰራሽ ትርክት ላይ የተጠመደው ቤተሰብነታችንን የሚንድ የኢትዮጵያ በሽታ ነው። ሁላችንም ለዶ/ር አብይ በፀሎትና በሥራ አጋርነታችንን በቃ! ይሁን አሜን ብለን እንደግፈው። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
በይቅርታ እንሻገር፥ በፍቅር እንደመር ለሚለው ወንድማችሁ ውጋት እየሆናችሁ፥ ዛሬ ላይ ሰው እንደ እንስሳ ሲጨክን እንድናይ ሆነ። አሁንም እየተሰበሰባችሁ “የኦሮሞ አንድነት” እያላችሁ ለይስሙላ አስሬ ከምትፈራረሙና ልባችንን ከምታደርቁ፥ “የኢትዮጵያ አንድነት” ብላችሁ የአኖሌን የጡት መቁረጥ የጠብ አውልት ለፍቅር በማፍረስ ጀምሩና አቃፊ ለመሆን ዳዴ በሉ። ያኔ ኦሮሞ ይከብራል፥ በመልካም ስምና ፍታዊነት እንደ ማንነቱ ይገዛል። የተጨቆነው ደጉ ኦሮሞ ሕዝብ አሁን በመንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ ሲገዛ፥ ተፈውሶ ፈውስን ለመላው ኢትዮጵያ ሊያመጣ አምላኩን የሚፈራ ሆኖ ሳለ፥ እናንተ በአስተሳሰባችሁ ገና ነፃ ስላልወጣችሁ፥ ትላንት በረከት ሆናችሁ፥ ዛሬ ወደ መርገምነት ተቀይራችዋልና፥ አንገታችሁን ማደንደን ትታችሁ ተመለሱ። ኢትዮጵያን እንበትናለን ብላችሁ፥ ኦሮሞ መግዛት አይችልም እያስባላችሁ ነው። የሚገዛ በመጀመሪያ አቃፊ መሆን አለበት። እናንተ እንደ ሕፃን ልጅ ሁሉ የእኔ ነው እያላችሁ፥ አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ሆናችሁ። የኦሮሞ ልጅ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ሲሰበስብ ከስር ስሩ ተከትላችሁ ትበትናላችሁ። ሲተክል ትነቅላላችሁ። ኦሮሞ መንገሱን ሳይሆን የፈለጋችሁት፥ እናንተ ራሳችሁ መንገስ ነውን? በናንተ ቤት ኢትዮጵያን ስትወጉ፥ ትልቁን የኦሮሞን ሕዝብ ስም ከመቸውም ጊዜ ይልቅ እያደማችሁ ነው። ወገናዊነትን እያቀነቀናችሁ ዛሬን አታላችሁ ትኖሩ ይሆናል፥ ግን ነገ የታሪክ ጥላሸት ሆናችሁ እንዳትታሰቡ እፈራለሁ። አሁንም ጊዜ ሳያልፍ የኦሮሞ መፍትኤ ሁኑ። እንዴት ብትሉ ሽማግሌ በመሆን ነው። እናንተን ለመመለስ ወደ እናንተ የሚቀርብ ተስፋ የማይቆርጥ እንደ እኔ ያለ ጉደኛ ብቻ ነው። ምክንያቱም እናንተ እርቅ ሳይሆን ጠብ ትርፋማ ንግድ ሆኖላችዋልና። ግን ይህ ንግድ መጨረሻው በኦሮሞ ሕዝብ መተፋት እንዳያመጣባችሁ ንቁና ሽማግሌ ሁኑ። ሽማግሌ ስትሆኑ በመጀመሪያ እናንተ ራሳችሁ በአጭር ንግስና ዘመናችሁ በሕይወት እያላችሁ ክፉ ዘር በመዝራታችሁ በምድራችን ስለታየው ሰቆቃ ይቅርታ ጠይቁ። ከዚያ የሞቱት የገዥ መደብ ሥር ተበደልን ስለምትሉት ሁሉ፥ እኛ ሕያዋን የሆንነው ለምድራችህ ፈውስ እንዲመጣ በሞቱት ሰዎች ፈንታ ቆመን ይቅርታ እርስ በርስ እንጠያየቃለን። ትላንት የበደሏችሁንና በሕይወት ያሉትንማ በሚያስገርም ፍጥነት ይቅርታ ሳይጠይቋችሁ፥ ወዳጅነት ፈጥራችዋል አሉ። ለኢትዮጵይ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው! ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ተፃፈ በእምዬ ኢትዮጵያ ስም። አስተዋይ ያስተውል። ያልሰራናትን ኢትዮጵያ ስንናፍቅ ጉድ ሆነናል። የራሳችንን ድርሻ መወጣታችንን ከማየት እንጀምር። ብዙሃን ዝምተኛው ኢትዮጵያዊ (silent majority) ፖለቲካው ቆሻሻ ሆኖበት ቁጭ ብሎ፥ ጥቂት በፖለቲካው ያረጁና ያፈጁ ፖለቲከኞች ራሳቸውን ሰውተው፥ አቡክተውና ጋግረው የሚያመጡልንን ኢትዮጵያ 50 ዓመታት ሙሉ ስናይኖረናል። ሁላችንም ያገራችን ነገር እየከነከነን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ እነዚህ ፖለቲከኞች ጋግረው ያመጡልንን ኢትዮጵያ አልመች ብሎን፥አንዱን ስናሞግስና ሌላውን ደግሞ ስንሰድብ ሰንብተናል። ከዓመት ዓመት ይህንኑ ስናደርግ፥ ዓይናችን እያየ፥ ኢትዮጵያ ከኮማወደ ሞት ዝቅ እያለች እየሄደች ነው። ይህ አካሄድ ታሪክ ብቻ ሆኖ መቅረት አለበት። ዛሬ! የፖለቲካ ፓርቲ አባልና ተሳታፊ መሆንን ሁላችንም የውዴታ ግዴታማድረግ አለብን። ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ሁላችንም በፖለቲካ ድርጅቶች ታቅፈን መደራጀትና ትግሉን በቃልና በሥራ መቀላቀል አሁን አሁን የግድ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆነ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆን፥ስለ ኢትዮጵያ ግድ ብሎት ማውራት እንደ ነውረኛ የሚያስቆጥር ባህልን በህብረተሰባችን ይፈጠር። ለኢትዮጵያ የሚሰራ በዝቶ፥ ቁጭ በይ ወሬኛ ይጠፋ ዘንድ አንዳችን ሌላኛውን እንዳደፋፍር። ፖለቲካ ኤሌክትሪክ/ቅጥፈት ነው የሚል ትርክትን አፍርሰን፥ ፖለቲካ የዜግነትና የክብር ግዴታ ነው በማለት ይተካ። ይቻላል! አዲስ ፓርቲ መመስረት፥ ወይም ሁሉንም ጨፍልቆ አንድ ማድረግ ጊዜው ያለፈበት ጉዳይ ነው። ሁሉም የየራሱን ፓርቲና አደራጃጀት ይዞ፥ ነገር ግን በአንድ ኢትዮጵያዊነት (ሰው መሆንኛ) ፍልስፍና ጥላ ስር ግንባር ፈጥረን፥ ሁነኛ አማራጭ ሆኖ መቅረብ ለኢትዮጵያ ከሞት ማምለጫ ብቸኛ መንገድ መሆኑ ግን አሁን ላይ ፍንትው ብሎ በራ። ሁሉም እኔ እኔ እያለ በሚወዳደርበት አውድ ውስጥ፥ የሁሉም እኔነት (ego)እንቅፋት በማይሆንበት ሁኔታ፥ በጥበብ ይህንንየአማራጭ ግንባር ሰብሳቢ እንዴት ወደ ብርሃን ማምጣት እንደምንችል እጠቁማለሁ። ከየት እንጀምር የሚለውን ጥያቄ ለመፍታት ታስቦ የሚደረግ ጥሪ ይህ ነው። እኔነትን (ego) እንቅፋት እንዳይሆን ጅማሬውን ታናሽ ማድረግና ከዚህ በፊት አምላክ ከሰራው ታሪክ ትምህርት መውሰድ ያስፈልጋል። “ቀጣዩ አሻጋሪ” ማን ይሁን ብለን ባለመግባባት ከምንለያይ፥ በመጀመሪያ “ቲም ኢትዮጵያን” ለመውለድ እንሞክር። ከዚህ “ቲም ኢትዮጵያ” ወደፊት አማራጭ ግንባሩንና ሰብሳቢውን (ቀጣዩ አሻጋሪ) በጊዜ ሂደት የሚታወቁ ይሆናል። ያም “ቀጣዩ አሻጋሪ” ለአማራጭ ግንባሩ ሰብሳቢ ይሆናል ማለት ነው። የሚቀጥለው ጥያቄ ይህ “ቲም ኢትዮጵያ” እንዴት ይወለድ የሚል ነው። አሁንም ከአንድ ሰው መጀመር ይቀላል። እያወራን እርስ በርስ ስንፈራራና ሳንተማመን መንገድ ላይ እንዳንቀር መላው ምንድነው? ፅሁፍ እየፃፍንና ፅሁፍ እናነበብን እንዲሁ ሜዳ እንዳንቀር ብልሃት ያስፈልገናል። ከምንራቆሰው ብሄር ውጭ የሆነና፥ በኢትዮጵያዊነት ላይ እንደ ወርቅ ተፈትኖ የነጠረ ከመካከላችን፥ ከኢሕአዴግ መንግስት ውጭ የሆነ ማነው? እኔ ይህ ሰው ኦባንግ ሜቶ ይመስለኛል። እኔ ከ ኦባንግ ሜቶ ድርጅት ጋር ምንም ግኑኝነት የለኝም። ከእርሱም ጋር አልተነጋገርኩም። እኔ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በፖለቲካ ያልተሳተፍኩና ለእርቅና መግባባት ከመሞገት ውጭ ማንንም የማላውቅ ታናሽ ሰው ነኝ። ኦባንግ ሜቶ ከፖለቲካው ውጭ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅን እንደሆነ አያለሁ። በተጨማሪ ደግሞ ከኦባንግ ሜቶ ብንጀምር፤ ከእርሱ የተሻለ ኢትዮጵያዊ አለ የሚል ሰው ቢኖር እንኳን፥ ኦባንግ ሜቶ ራሱ ችቦውን ለማስተላለፍ ብቃት ያለው ስብዕና ይኖረዋል ብዬ መገመት እመርጣለሁ። ቁምነገሩ ጊዜ የለንም። እጅግ አስቸኳይ ጉዳይ ስለሆነ ብቻ የመጣደፍ ጭንቀት እንዳለብኝ ታይቶ ስህተተኛ ከሆንኩም ይቅርታ ይደረግልኝ። ይህንን ሀሳብ በንፁህ ሂሊና ተወስዶልኝ፥ ከማውራት ለመላቀቅ የተደረገ ጥረት ተደርጎ እንዲወሰድና ማስተካከያ ይሰጥበት ዘንድ አደራ እላለሁ። ብሳሳትም፥ በሞት እና በሕይወት መካከል ላለችው እናት ሀገር ሞኝ ተደርጌ ብቆጠርም ክብር ነው እላለሁ። ታዋቂ ሰው ስላልሆንኩ፥ ይህ ሀሳብ ፍሬ የሚያፈራው በተዐምር ፈጣሪ እጁን ጣልቃ ካገባበት ብቻ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ ምክርዎን በዚህ ኢሜል ይላኩልኝ። ኢሜል፡ [email protected] የመጀመሪያውን አሻጋሪ ለቀቅ፥ ቀጣዮን አሻጋሪ ጠበቅ ምስጢሩ ሁለት አሻጋሪ እንደሚያስፈልገን ማስተዋል ነው። ነፃ አውጭ ሙሴው ዶ/ር ዐብይ ከባርነት ቀንበር የ “ኤርትራን ባህር” አሻግሮጥሪውን በዲሞክራሲ አዋላጅነትለማጠናቀቅ ሲጥር፥ እኛ በምድረ በዳ እንዳንቀር፥ የ “ዩርዳኖስን ባህር” አሻግሮ ወደ ተሰፋይቱ ኢትዮጵያዊነት ምድርየሚያስገባን፥ ከዶ/ር ዐብይ ትይዮ የሚሰለፍና አማራጭ ግንባሩን የሚመራ “ኢያሱ” እንዲወጣ ሁላችንም አንድ ልብ እንዲሰጠን ፀሎቴ ነው። እግዚአብሔር ዐብይን ለኢትዮጵያ ሰጠ። አሁን አምላክ ከእኛ የሚፈልገውየኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አንድ ሆነው ቀጣዩ አሻጋሪእንዲገለጥመተባበር መቻል ነው። ዐብይን የሚያምነው ሰው፥ እውነት ዐብይን ከወደደ፥ ለ “ቀጣዩ አሻጋሪ” መገለጥ ይስራና፥ ዐብይ የሚወዳትን ኢትዮጵያን ይርዳ። ዐብይን የሚጠረጥረው ሰው፥ እውነት ኢትዮጵያን ከወደደ ለ “ቀጣዩ አሻጋሪ” መገለጥ ይስራና የሚወዳትን ኢትዮጵያን ይርዳ። ዶ/ር ዐብይ ላይ ብቻ ተጠምዶ ሰው ቁጭ ካለ፥ በምድረ በዳ አልቆ፥ የእስራኤልን ታሪክ ዳግመኛ በራሳችን ላይ እንዳንደግም እንፍራ! አሁን አሁን ዶክተር ዐብይ መደገፍም ሆን መቃወም አይጠቅማቸውም። አይጠቅመንምም። ይልቁንስ እንልቀቃቸውናበራሳችን ሥራ እንጠመድ።ያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴሩም ጉልበት አግኝተው በበጎነት ይገለጣሉ እንጂ ክፉ ሆነው ክፉ አያደርጉም። ዶ/ር ዐብይ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው ብለው ምንም እንከን በሳቸው ላይ ላለመመዝገብ የተገዘቱ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ዶ/ር ዐብይ አስመሳይ መሰሪ ናቸው ብለው የሚምሉና ፍርድ ቤት የቀረቡ ይመስል፥ የማስረጃ ትንታኔ ላይ ተጠምደው ጊዜያቸውን ያቃጥላሉ። የተለመደው የፖለቲካ ጥበባችን የሚመክረን እውነታዎች በሁለቱ አካሄድ በኩል እየፈረጀን እስከመቼ እንደሚሸውደን አላውቅም። ብናስተውል በዚህ ሰሞን የተከሰተው የጃዋር ግርግር፥ ለኢትዮጵያ ታላቅ አዘን ቢያስከትልም፥ የፈሰሰው ደም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ከፈለግን፥ ከዚህ ሰቅጣጭ ሀዘን ውስጥ በሁለት ጎራ ተከፍለንየምንሞግትዶ/ር ዐብይ ተኮር ዜጎች (ተቃዋሚና ደጋፊ)፥ ዶክተሩን ለቀቅ አድርገንናበህብረት ሆነን ለአንድ ዓላማወደ ሥራ እንግባእላለሁ። ኢትዮጵያዊነት ስለተሰበከ ሀገር ሁሉ በፍቅርና በተስፋ እንደተነቃነቀ አምና አይተናል። ግን ምን ያደርጋል ከተበታተነ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ይልቅ፥ በወደቀራዕይና ዓላማ አንድነትን የፈጠረ ድርጅትየበለጥ ሃይል ኖሮት ለእርስ በርስ እርድ እያዘጋጀን ይገኛል። ግና! በሺዎች ዓመታት እንደ አልማዝ ተፈትኖ ነጥሮ የወጣው ኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ራዕይ ጥላ ስር ተሰባስበን፥ አንድ ሁነኛ አማራጭ ግንባር የምንፈጥርበት ቀን ደረሰ።ኢሕአዴግ የተለያየ ፓርቲዎችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጠፍሮናግንባር ፈጥሮ 27 ዓመት ሲነግስ አይተን ስናበቃ፥ ዛሬ ደግሞ ይህ ኢሕአዴግ የተለያየ ፓርቲዎችን በመደመር ንግግር ጠፍሮናግንባር (ውህደት) ፈጥሮ ሌላ 27 ዓመት ሊገዛ ሲደራጅ፥ በትናንሽ ራዕይና በተበታተነ ፓርቲዎች እርስ በርስ ፉክቻ መዳከር ሊያበቃ ነው።ዝምተኛው ብዙሃን ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ዐብይን በመደገፍና በመቃወም እየተዋከበ፥የኢትዮጵያን ትንሣኤ በምትሃትይመጣል ብሎመጠበቅ ሊቀር ነው ከእንግዲህ። ሌላው ቀርቶ ኢሕአዴግ አጋር ፓርቲዎች እያለ ለዘመናት የሚያላግጥባቸውን፥ዛሬ ዛሬ ሊያቅፋቸው ላይ ታች ሲል፥ ይህ አማራጭ ግንባር ዕውን ሆኖ እነዚሁኑ የተገፉ ሕዝቦች ለአባልነት ይጋበዛሉ። አሮጌ ነገር እያረጉ አዲስ ነገር መጠበቅ የሰለቸን ጊዜ ላይ ደርሰናልና እንንቃ! ዶ/ር ዐብይን የሽግግር መንግስት ምናምን እያልንበመግለጫና በጥያቄ ከምናዋክባቸው፥ዶክተሩን ለቀቅ አድርገን፥እኛ “የሽግግር” አማራጭ ግንባር ለውድድር እንዲቀርብ የምንፈጥርበት ወቅት ይሁን።ኢሕአዴግ በፌድራሊዝም አግባብ ሲጣሉ፥ እኛ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተገነባውንና ፍፁምነት ጭምር የተላበሰውን“ኢትዮጵያዊ ፌድራሊዝምን”እናስተዋውቃለን።ጠቅላይ ሚኒስቴሩን እንዲህና እንዲህ አድርጉ እያልን አዳዲስ አሳቦችን እንዲቀበሉን መወትወት ትተን፥ ያንኑ አዳዲስ ሀሳቦች በራሳችን ላይ አውለን አማራጭ ግንባር ሆነን እንገለጣለን። እርማችንን እናውጣና ሀቁን እንቀበል እስቲ ሀገራችንንከማየት እንጀምር። ሀገራችንጃንሆይ ያስራቧት፥ ደርግ ያቆሰላትና ኢሕአዴግ ኮማ ውስጥ የከተታት እምዬ ናት። ጠላቶቿ ግባ መሬቷን ከአሁን አሁን አየን እያሉ ቢጠብቁም፥ ፈጣሪ ከእሷ ጋር ጉዳይ አለውና ይሄው ኢትዮጵያ እየተባለች ስሟ ከመጠራት እስካሁን አልቀረም። ምድረ በዳ ሆና ባንዲራዋ በሰማይ የሚታይ ሆናለች። ሰው የዶክተር ዐብይን ልብ ለማወቅ ይመራመራል። የትኛውም ልብ ይኑራቸው አሁን ያለችሁን የኮማ ኢትዮጵያ ነፍስ ሊዘሩ አይችሉም። ይመስለናል እንጂ ማንም አይችልም።ወደድንም ጠላን ኢትዮጵያ በሰው እጅ ሥራ እንዳንታሰራራ ተደርጎ በኮማ ውስጥ እንድትገባ ተደርጋለች። እርማችንን እናውጣና ይህን ሀቅ ማለትም በሰው እንደማይቻል እንቀበል።ምክንያቱም ያሳለፍነው ጉድ ከሰውነት አውጥቶን እንደ ባለ አእምሮ ማሰብ እንዳንችል አድርጎናል። ሀገሪቱን የሚዘውሩት ሊሂቃን ተብዬዎች ሁሉ፥ ሁሌ ጥል ላይ ያለንና ሁከት ውስጥ የምንዋኝ ያልታወቀልን “እብዶች” ነን። በደመ ነፍስ የምንመላለስ ሆነናል። መርገም ይዘን በረከት እንዲወርድልን ስንባዝን ከርመናል። ንፁህና ትልቅ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በእኛ ዳተኝነት ታግቶ፥ መጨረሻዬ ምን ይሆን ብሎ ጉዳችንን ከማየት ያለፈ ነገር ማድረግ እንዳይችል ሆኖ በስጋት ተቀምጧል። ልብ እንግዛና የኢትዮጵያን አምላክ ከማየት እንጀምር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋው ፈጣሪ እንደሆነ እሙን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተሰብ እንደሆነ እውነትነው። ነገር ግን ባለፈው 50 ዓመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚዘውሩት አምላክን ዜሮ እንዳረጉት የአደባባይ ሚስጢር ነው። በእጃቸው ያለው ደምና በልባቸው ያለው መከፋፋት አምላክን ለረድኤቱ እንዳይጠሩ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። ያለፈውን በደልና ቁርሾ ማውራትና በቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንጂ፥ በአምላክ ፍቅርና ረድኤት በይቅርታ ያለፈውን ፋይል ዘግቶ መፈወስ እንዳለ አይታሰብም። የጎሳውን ወገን “ወንድማችን” ይላል እንጂ፥ መላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ እንደሆነ ዘንግቶ፥ በወንድማማች መካከል ጠብ መዝራት ፋሽን ነው። እርግማን ተይዞ በረከት መጠበቅ ሞኝነት ነው። የበረከትን ምንጭ የሆነው አምላክ ተንቆና ገሸሽ ተደርጎ፥ መድሃኒት እንዲመጣ መልፋት ባዶነት ነው። እንዲሳካልንና ምድራችን የተዐምር ምድር እንድትሆን ከፈለግን፥ እኛ ከቁጥር የማናስገባውን የኢትዮጵያ አምላክ ሕዝቡ ታምኖበታልና፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘወትር እንደሚያደርገው ሁሉ እኛም ራሳችንን ዝቅ ማድረግ ያስፈልገናል። ለሰው የማይቻል ለፈጣሪ ይቻላልና። ሁላችንም በመመለስየኢትዮጵያን አምላክ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንዲሆን በአደባባይ ለሁሉ እናውጅ። ያኔ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የሚለው ትንቢት እውነት ይሆናል። የአሜሪካ አባቶች እግዚአብሔር ላይ ተደግፈው የእግዚአብሔርን ስም በዶላራቸውና በሳንቲሞቻቸው ላይና በብሄራዊ መሀላቸው ውስጥ አስገብተው ፈጣሪን ሲያከብሩ፥ እነሆ የዓለም ንጉስ ሆነው አረፉት። የሚያሳዝነው ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ፥ መሪዎቹበፈጣሪ የሚያፍሩመሆናቸውነው። የፈጣሪ በረከትና ረድኤት እንዲደርሰን የፖለቲካ መሪዎቻችን ራሳቸውን ከማማው ላይ አውርደው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታመንበትን ፈጣሪ ከፍ እንዲል ያድርጉ። አምላክን በንግግር መጨረሻ ላይ ጣል የምናደርገው ብቻ ሳይሆን፥ አማራጭ እንዲሆን በሕብረት የምንፈጥረው ግንባርየአምላክን ረድኤት እንደ ዋና መሪ ቃል ማስቀመጥአለበት። አምላክን የምንማፀነው፥ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ሳይሆን (ሃይማኖት የግል ነው)፥ ያለ ፈጣሪ ረድኤት የኢትዮጵያ ትንሳኤፍፁም በሰው ሃይል እንደማይሳካ ከልብ ስለገባን መሆን አለበት። ይህ ድርጊት ደግሞ መድሃኒትነቱ በእኛ ብቻ የሚወሰን አይደለም። ለምሳሌ መሪ ቃላችን፥ “ፈጣሪ ኢትዮጵያን አስባት” ብለን ብንነሳ፥ አምላክ ይህንን ለምልክት አድርጎት የሚባርከን እኛን ብቻ ሳይሆን፥ እኛን ለዓለም በረከት በማድረግ ምድርን ሁሉ በክብሩ ይሞላል። በቸልተኝነት አይለፍብን፥ ይልቁንስጊዜውን ከማየት እንጀምር። በአብዮትትርምስ ውስጥ የነበረ ትውልድ በሞት አልቆ አዲስ ትውልድ ሊመጣ ያለበት አፋፍ ላይ ደርሰናል። ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ የጃንሆይ ጊዜ ግርግርን የሚያውቅ ሰው በሕይወት የሌለበት ዘመን ሩቅ አይደለም። ባለፉት አምሳ ዓመታት ስለነበረው ቀውስ ሂሳብ በይቅርታ ዘግተን፥ አዲሱን ትውልድ መክረንና መርቀን፥ የኢትዮጵያን አይቀሬ ታላቅነት በጭላንጭል አይተን፥ ወደማንመለስበት ሞት ኢትዮጵያን ተሰናብተን በእፎይታ እንድንሄድ ፈጣሪ ምህረት እንዳደረገልን ስለ ጊዜው ምንነት ማወቅ ተስፋ ሰጭ ነው። ጊዜው በጠላታችን ሤራ ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ቀጠሮ የተያዘበት ብቻ ሳይሆን፥ በይበልጥ ጊዜው ለውድ እናት ሀገራችን ልዩ የመዳን ቀን ለመሆኑምልክቱ ብዙ ነው። አብዮት ሳይፈነዳ በለውጥ ጉዞ ላይ መሆናችንመለኮታዊ እጅ እንዳለበት የሚጠራጠርና ለውጡን እኔ በአመፅ አመጣውት ብሎ የሚፎክር ፊት ፊቱን ብቻ የሚያይ ፍጡር ነው። በመጀመሪያ አካባቢ ሕዝብን በተስፋና ደስታ ፍንጣቂ ኢትዮጵያዊነትን ቦግ ብሎ እንዲበራ ያንተገተገው የዶክተር ዐብይ ስብዕናብቻ ነው ብሎ የሚያስብ፥ የማይታየውን የመለኮት እጅ የማያገናዝብ ሰው ነው። በመጨረሻ ያገሩ ሰዎች የሆንን ስንቀዘቅዝ፥ በዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ያስታቀፋቸው፥ ይህ ስኬት ስለ ዶክተሩ የሚናገርብቻ ሳይሆን መለኮት “አስተውሉ! ጊዜውን!” እያለን ለመሆኑ ማወቅ የሚሳነው የማያስተውል ሰው ብቻ ነው። ባጭሩ የነገሩ ድምዳሜ ይህ ነው፡ ያም ጊዜው በማያሻማ ሁኔታ የኢትዮጵያ ነው። የምንተኛ እንንቃ! የስብራታችንን ጥልቀት ላስተዋለው፥ የጨለማውን ድቅድቅነት ለተመለከተው፥ ሊነጋ እንዳቅላላ እርግጠኛ መሆን ይችላል። ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡ · የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ · አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው። · ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ኢትዮጵያን እንበታትናለን ብሎ ሲሰራ የነበረው ዕብሪተኛ ሰው ባለጊዜ ሆነና፥ ራሱ ብቻውን መንግስት ሆኖ መላውን ኢትዮጵያ እንደ ጎልያድ በማን አለብኝነት ሲያስጨንቅ የሚታይባት ምድር ኢትዮጵያ ናት። አንድ ቤተሰብ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በክልል እያጠሩ ባላንጣ መንግስታትን ፈጥረው፥ ጨለማውን ብርሃን እያሉ ሲጠሩ የማይታፈርበት ምድር ኢትዮጵያ ናት። ከነገድ ከቋንቋ ዋጅቶ በክርስቶስ ፍቅር አንድ ስለመሆን የሚሰብከው ሃይማኖት ተከታይ ነኝ እያሉ፥ በወንድማማች መካከል ጠብ የሚዘሩ ጉደኞች የሞሉባት ምድር ኢትዮጵያ ናት። በመርህ ላይ ሳይሆን በዘረኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የመንጋ አንድነት ያለው ፓርቲ፥ መላውን ኢትዮጵያ አንድ የሚያደርግበት ምሪት ይሰጣል ተብሎ ጉም የሚጨበጥበት ምድር ኢትዮጵያ ናት። ወዶም ሆነ ተገዶ ሁሉም በየጎሳው ዙሪያ አንድነቱን አጠናክሮ እየተደራጀ ራሱን ለማዳን ሲዳክር፥ ራሱን ለእርስ በርስ ዕልቂት እያመቻቸ መሆኑ እየታወቀ፥ የ “ሰው” ነት ፖለቲካ ቦታ የማይሰጠው ምድር ኢትዮጵያ ናት። እኩይ የሆነው ዘረኝነት ኢትዮጵያን ሊያሰጥም ጫፍ የደረሰበት ጊዜ ሆኖ ሳለ፥ ሩዋንዳ ልንሆን ነው ብሎ ከመፍራት ያለፈ፥ በማስተዋል ለመጠበቅ ምንም እርምጃ የማይወሰድባት ምድር ኢትዮጵያ ናት። ይህ ሁሉ እውነት ነው። ግን ከዚህ እውነት የሚበልጥ ሌላ እውነት ደግሞ አለ። የኢትዮጵያ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው! ዕድሜ ልካችንን በመከራ ውስጥ አልፈን ስናበቃ፥ የብርሃን ጭላንጭል አሳይቶ እንቁልጭልጭ የሚጫወትብን ጨካኝ አምላክ የለንም። እግዚአብሔር በምድራችን የጀመረውን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርስ መንገድ ላይ አይጥለንም። እግዚአብሔር ያያል። እግዚአብሔር ይፈርዳል። ፈጥኖ ይፈርዳል። በቀናት ውስጥ ክብሩን ይገልጣል። ዲያብሎስ የደገሰልን የዕልቂት እኩይ ሤራ ይገለበጣል። ኢትዮጵያ ወጀቡን አልፋ ትሻገራለች። ታበራለች። መከራ ያየነው ከዓለም በኃጢአት አንደኛ ስለሆንን አይደለም። የቃል ኪዳን ሀገር የሆንነው ከዓለም በፅድቅ አንደኛ ስለሆንን አይደለም። ያለፈው መከራችንም ሆነ የሚመጣው ጉብኝታችን ምክንያቱ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር እንዲገለጥብን ብቻ ነው። ጠላት ለኢትዮጵያ መበታተን ያጠመደው ክፉ ወጥመድ ለእኛ ጭንቀት ቢሆንብንም፥ ለፈጣሪ ክብሩን እንዲገልጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ምድር ሁሉ በኢትዮጵያ አምላክ አለ እስኪል ድረስ ሥራውን ሊሰራ ፈጣሪ ራሱ ይወርዳል። ወጥመዱን ይሰብራል። ኢትዮጵያንም ያስመልጣል። ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡ · የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ · አንተምየዘንዶውንራሶችቀጠቀጥህ፤ለኢትዮጵያሰዎችምምግባቸውንሰጠሃቸው። · ኢትዮጵያእጆችዋንወደእግዚአብሔርትዘረጋለች። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ዕድሜ ልካችንን በመከራ ውስጥ አልፈን ስናበቃ፥ የብርሃን ጭላንጭል አሳይቶ እንቁልጭልጭ የሚጫወትብን ጨካኝ አምላክ የለንም። እግዚአብሔር በምድራችን የጀመረውን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርስ መንገድ ላይ አይጥለንም። እግዚአብሔር ያያል። እግዚአብሔር ይፈርዳል። ፈጥኖ ይፈርዳል። በቀናት ውስጥ ክብሩን ይገልጣል። ዲያብሎስ የደገሰልን የዕልቂት እኩይ ሤራ ይገለበጣል። ኢትዮጵያ ወጀቡን አልፋ ትሻገራለች። ታበራለች። መከራ ያየነው ከዓለም በኃጢአት አንደኛ ስለሆንን አይደለም። የቃል ኪዳን ሀገር የሆንነው ከዓለም በፅድቅ አንደኛ ስለሆንን አይደለም። ያለፈው መከራችንም ሆነ የሚመጣው ጉብኝታችን ምክንያቱ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር እንዲገለጥብን ብቻ ነው። ጠላት ለኢትዮጵያ መበታተን ያጠመደው ክፉ ወጥመድ ለእኛ ጭንቀት ቢሆንብንም፥ ለፈጣሪ ክብሩን እንዲገልጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ምድር ሁሉ በኢትዮጵያ አምላክ አለ እስኪል ድረስ ሥራውን ሊሰራ ፈጣሪ ራሱ ይወርዳል። ወጥመዱን ይሰብራል። ኢትዮጵያንም ያስመልጣል። ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡ · የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ · አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው። · ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፤ አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው። ብርሃን ፈነጠቀ ዶ/ር አብይ መጣ፥ ኢትዮጵያን ሊታደግ እርሱ እንቅልፍ አጣ፥ ሁሉም ደገፈና አንድ ላይ ሰልፍ ወጣ፥ ልናርፍ ነው ብሎ ከነበረን ጣጣ። ቃሉ የሚጣፍጥ የሌለው ወደር፥ ትህትናው ግሩም ልዩ ከምድር፤ ፅናቱ የሚገርም ደግሞም እይታው፥ ድፍረቱ ትጋቱ እጅግ የሚደንቀው። ጠላቱ እያደር እየበዛ ሲሄድ፥ ወደድኩህ ያለውም ሊያወጣው ከመንገድ፤ ከወዲህ ከወዲያ ሁሉም ሲጎትተው፥ ስምም እያወጣ ቢጎነታትለው፤ ዝም ብሎ ነጎደ አልተነቃነቀ፥ ሁሉንም እያየ አውቆም እያወቀ። የኢትዮጵያ ነገር መላ እንደሌለው፥ አምላኳ አወቀላት ጉዳዩ ሌላ ነው፤ ጠላቶቿ በዙ እጅግ ጨከኑባት፥ ስለዚህ ወረደ አምላክ ሊፈርድላት፥ ምድር ዝም ትበል ይታይ ሲለይለት። ትዕግስት አይጠቅመንም ቶሎ ያልቃልና፥ ተስፋም አይረዳንም ስጋት ያንቃልና፤ ይልቁንስ እንይ የማይታየውን፥ በእውቀት እንወቅ አይለፈን ይህ ቀን። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ፖለቲካ ምድራዊ ነው። ሃይማኖት ሰማያዊ ነው። የምድሩን ማመስ አልበቃቸው ብለው፥ ተንጠራርተው ሰማይን መንካታቸው፥ እነርሱ ራሳቸው የሚበተኑበት ወቅት ጅማሬ መሆኑን ማን በነገራቸው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከዓለም ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ሌላውን በውጭ ያሉትን ኦርቶዶክስን ጨምሮ) ለየት ያለ ነው። በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጥቅም ላይ የሚውለውን የግዕዝን ቋንቋ በመጠቀም፥ በግዕዝ ቅዳሴ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ ዛሬ በመጠበቅ፥ የተለያየ ቋንቋ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን በእኩልነት ባማከለ መንገድ ማገልገል የቻለች፥ በምንም የማትቀያየርና የማትለዋወጥ አዕማድ የሆነች ቤተክርስቲያን ናት። ከዓለም ብቸኛ የሆነች ይህች ቤተክርስቲያን ታቦትን በቤተክርስቲያን ውስጥ፥ ደግሞም ታቦትን እያወጣች (እያነገሰች) የምትገኝ፥ ለዓለም “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለውን የተስፋ ቃል የሚያስረግጥ፥ የቃል ኪዳን ሀገር መሆኗን ለፍጥረት ሁሉ በአደባባይ የምታውጅ ናት። ኦርቶዶክስ እንደ እኔ ላሉ የወንጌላውያን እምነት ተከታዮች እንደ እናት ቤተክርስቲያናችን የምትታይ ብቻ ሳትሆን፥ ለኢትዮጵያ ሀገር እንደ እናት ሆና በፀሎት የምትማልድ የኢትዮጵያ ስጦታ ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የማንም ጥብቅና አያስፈልጋትም። የነካት ከመሠረታት አምላክ ጋር ይጋፈጣልና ተውት። ኢትዮጵያዊነትን ለማለምለም ትንታጎች መነሳታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ታዲያ እነዚህን የኢትዮጵያዊነት መልክተኛ ሆነው የሚንቀሳቀሱትን ለማዳከምና ተስፋ ለማስቆረጥ የሚሮጡ ካሉ እግዚአብሔር ይታረቀቻው። አንዳንድ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ነን የሚሉ ወደ ልባቸው ተመልሰው፥ እነርሱ ባያውቁትም ያከበረቻቸውን ኢትዮጵያን ቢያቅፉና ለኢትዮጵያዊነት ልምላሜ ደፋ ቀና ቢሉ፥ ለሂስና ለትችት አይጋለጡም ነበር። ሰውን የምንቃወመው ለመግደልና ለማጥፋት ሳይሆን ለመመለስ ነው። ፅንፈኞችንና አክራሪ ዋልታ ረገጦችን የምንቃወመው፥ ኢትዮጵያን ከማፍረስ ሙሉ ለሙሉ ታቅበው፥ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ ጉዞ እስኪጀምሩ ድረስ ነው። ከመካከላችን ለዘላለም ጠላታችን የሆነው ሥጋና ደም የሌለው ሰይጣን ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ ሁላችንም የወንድማችን ጠባቂ መሆን ይገባናል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ! ኢሜል፥ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ስለ ኢትዮጵያ በፍቅር ተነድፈን የምንጠብቀው አንድም ትንሳሄ (ተስፋ) ወይም መበታተን (ስጋት) ነው። ግን ሁለቱም እየሆነ አይደለም። ወደፊትም እነዚህ አይሆኑምና ከመንፈስ መዋዥቅ ለመውጣት ምናልባት ራሳችንን መርምረን የምንጠበቀውን ተስፋም ሆነ ስጋት ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አስታርቀን የሚሆን የሚሆነው ላይ ማተኮር ይሻል ይሆን እላለሁ። እንደ ባለ አዕምሮ ሲታይ በኢትዮጵያ ምድር እንኳን ምርጫ ማድረግ ቀርቶ፥ በሰላም አብሮ መኖር ያልተቻለበት፥ በመፈናቀል አንደኛ ደረጃ በመያዝ ዓለምን የምትመራ ሰላም የደፈረሰባት ምድር እንደሆነ ሁሉም ያውቃል። የፖለቲካ ፓርቲ የተባሉትም ምንና ስለምን እንደሚቆሙ ውሉ የማይታወቅበትና መድረክ አግኝተው በማያስተዋውቁበት አሁን ወቅት ላይ ቆመው በማግስት ምርጫ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለው ማወጃቸው ይገርማል የሚል ያልገባው ብቻ ነው። ግራ የሚገባን የምንጠብቀው ከሚሆነው ጋር ስለሚጋጭ ነው። ዶ/ር አብይ መራሹ ፓርቲ (ግንባር) ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ (ማለትም ሶማሌ፥ ጋንቤላ ወዘተ ጨምሮ) አዲስ ስም ይዞ ብቅ ሊል በስራ ላይ መሆኑን ተነግሮናል። ተቃዋሚ (ተፎካካሪ) ፓርቲዎችም እየተደመሩ (እየተዋሃዱ) በተባባሪነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ እያየን ነው። ኢትዮጵያዊነት እና ዘረኝነት (እንደ ውሃና ዘይት መቀላቀል ባይችሉም) በምድረ ኢትዮጵያ በአብሮነት ታቅፈው እየተሰበኩ እዚህ ደርሰናል፥ ይቀጥላልም። ሀገር ላይ ብሔራዊ መግባባት ይኑር እያልን በየቦታው የምንጮህ ሁሉ ዲሞክራሲ ኖሮ በመናገራችን ብቻ ረክተን መቀመጥ ሳይሻለን አይቀርም። ምርጫው የዛሬ ዓመት እንዳሰቡት ይካሄዳል። የዛሬ ዓመት አዲሱ ኢሕአዴግ ራሱን ለውጦና ሌላውን ውጦ ለምርጫ ያለ ሁነኛ አማራጭ ራሱን ለሕዝብ ያቀርባል። ለዚያ ዓይነት ምርጫ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ምርጫውን ለማካሄድ እንቅፋት አይሆንም። እኛ በባዶ ሜዳ የምንጨነቀው የሚሆነውን ሳይሆን የማይሆነውን እያሰበን ግራ ስለሚገባን ነው። ሕገ መንግስቱንም በውል ያወቅነው አይመስለኝም። ጭራሽ ይጥፋና አዲስ ሕገ መንግስት እንፃፍ የምንልም ሆነ በሕጋዊ መንገድ በሂደት ይሻሻል ብለን የምንከራከረው አሁንም በባዶ ቦታ ነው። ሁለቱም እንዳይሆን ተደርጎ ተቆልፎ ነው የተሰራው። በሕጋዊ መንገድ ይሻሻል ቢባል፥ በተለመደው የማሻሻያ ሂደት ሳይሆን በልዩ ድንጋጌ እንዳይቻል ተደርጎ እንደተቀመመ የሚያውቅ ማን ነው? ጭራሽ ይጥፋና አዲስ ሕገ መንግስት እንፃፍ ቢባል፥ ለሶስት አስርተ ዓመታት በኢትዮጵያ የተዘራው መርዝ ምን ያህል እንደቦረቦረን የሚያውቅ ማን ነው? ከዚህ ሁሉ ወደ ብሔራዊ መግባባት መጥተን መውጫ መንገድ እንዳንፈልግ መካከለኛውንና የሚሆን የሚሆነውን ማየት ደግሞ እንደተሰወረብን የሚያውቅ ማን ነው? እውቀቱ ጠፍቶን ሳይሆን፥ ከትንሳሄ ተስፋና ከመበታተን ስጋት እየዋዥቅን የምንላተመውና በመሬት ላይ ያለው እውነታ ከምንጠብቀው ጋር የሚጋጨው፥ የኢትዮጵያ ፍቅር አሳውሮን ይሆን? የኢትዮጵያ ነገር የሚፈታው ዛሬ ሳይሆን በትውልድ ዘልቆ ቢሆንስ? ለዚያ ራሳችንን አዘጋጅተን፥ ለሚሆን ነገር ብንተልም ይበጅ ይሆንን? የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያን ያስባታል። ትዕግስት ይስጠን። ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ ወሎ ኦሮሞ ነው ሲል፥ታሪክ ላይ ተደግፈን ስለ ወሎ ባለቤትነት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከመሞከር በፊት የጥያቄው ጤንነት ይታሰብበት። ጭር ሲል አልወድም ሆነና ነገሩ፥ ጫጫታው ይድራልኝ አለ በመንደሩ። ያለ አዕምሮ ጠብ ጫሪ፥ “ወሎ ኬኛ” ባለ አዕምሮ አቃፊ፥ “ኢትዮጵያ ሀገሬ ነው። ወሎ ወገኔ ነው” ትላንት አዲስ አበባ ዛሬ ወሎ ነገ ደንቢ ዶሎ ሰው መሆን ቀሎ ሕፃን፥ ሁሉም የእኔ ነው ብሎ ያላዝናል። ጎልማሳ፥ እንዴት በአብሮነት እንኑር ብሎ ይመክራል። ሽማግሌ፥ ለተተኪው ትውልድ ሰላም እንዲበዛ ይተጋል። ጣና ኬኛ ወለጋ የኛ ኬኛ የኛ የኛ ኬኛ ኢትዮጵያኛ ኢሜል፥ [email protected] ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
የተከበሩ ዶ/ር ዐብይ፥ ይስሙኝና! ዶ/ር ዐብይ የኢትዮጵያዊነትን ትንሣኤ በውብ ቃላት ከማወደስ የሚያልፍና በሥራ ወደዚያ ለማሻገር የሚያሽችል ፍላጎት እንዳላቸው አምናለሁ። የጠቅላይ ሚኒስቲሩን ጆሮ ባገኝ፥ የምነግራቸው ውዳሴ ወይም አፍራሽ ወቀሳ አይደለም። በዚያ ፈንታ ድካማቸውን የሚቀርፍ የሚያንፅና የሚገነባ ሀሳብ ለመወርወር ግን እቸኩላለሁ። ድካማቸውን ስዘረዝር የታዘብኩት ዋና ነገር የድካማቸው ፍሬ ነገር ራሱ የተመሠረተው በእሳቸው በጎ ሥራ ላይ ነው። ይህ ማለት የጠነሰሱትን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርሱት በተንጠልጠል መንገድ ላይ እንዳይቀር ለማሳሰብ ነው። ዶ/ር ዐብይ በንግግር ያስዋቡትን ኢትዮጵያዊነት በሥራ ለመተርጎም ዛሬ ውለዱ ልንላቸው ባይቻልም፥ ብሔራዊ መግባባት እንዲኖር ብሔራዊ ውይይት እስካሁን እንዲኖር አለማድረጋቸው ቅር ያሰኛል። ለ 97 ምርጫ ሰው ሁሉ የፖለቲካ ውይይት ሲደረግ የነበረውን ዓይነት አውድ፥ ለኢትዮጵያዊነት ልምላሜ ብሔራዊ ውይይት ለምን ዛሬ አይፈጥሩልንም? ሁሉም ዳርና ዳር ቆሞ የተቀበራረቀ ነገር ከሚጮህ፥ በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ተብሎ ስለ ቀጣይ ኢትዮጵያዊነት ትምህርታዊ ውይይትና የሀሳብ ፍጭት በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው መቼ ነው? ይህ ብሔራዊ የመግባባት ሂደት መርሀ ግብር በአራት ደረጃ ሊቀመጥ ይችላል። ይህም ጉዞ በመጨረሻ ወደ ምርጫ ሲያደርሰን፥ ያኔ ይህ እርምጃ ለፖለቲካዊ መፍትኤ መንገድ ጠራጊ መሆኑን ባየን ነበር። 1ኛ ደረጃ መርሀ ግብር / የሃይማኖት አባቶችን ለኢትዮጵያ ትንሣዬ ይጋብዙ። ዶ/ር ዐብይ ኦርቶዶክስ፥ ሙስሊምና ፕሮቴስታንት ሃይማኖት አባቶችን በማስታረቅ ፋና ወጊ ናቸው። ሲሆን ሲሆን የሃይማኖት አባቶች ለመንግስት የሞራል ኮምፓስ መሆን ሲገባቸው፥ በሁሉም ክፍል ያሉ የሃይማኖት አባቶች ከሰማይ የተሰጣቸውን ጥሪ ሳይወጡ ቀርተው፥ በተገላቢጦሽ መንግስት የሃይማኖት አባቶች መፍትሄ ሆኖ ተገኘ። ታዲያ ዶ/ር ዐብይ ይህንን ያላቸውን ቅቡልነት ለኢትዮጵያ መፈወስ ጭምር ለምን አይጠቀሙበትም? ብሔራዊ የንሰሀና የእርቅ አውድ በምድራችን እንዲፈጠር፥ እነዚህ የሃይማኖት አባቶች በኢትዮጵያዊነት ተቀናጅተው፥ በየቤተ እምነታቸው ህዝብን ይዘው በፈጣሪ ስር እንዲወድቁ ለምን አያሳስቡም? ከራሳችን እና እርስ በርስ ተጣልተን ስንባላ፥ ሰከን አድርጎን ወደ ልባችን የሚመልሰን ፈሪሃ ፈጣሪ አይደለምን? የሁሉም ችግር ስር ብንጎረጉር መንፈሳዊ ነው። ስለዚህ በዚህ በአምላክ ረድሄት ጉዞ ብንጀምር የሚቀጥሉት መርሀ ግብር ደረጃዎች ውጤታማ ይሆናሉ። 2ኛ ደረጃ መርሀ ግብር / ምሁራን በእውነት ትርክት ታሪክን እንዲያስታርቁ ይጋብዙ። ዶ/ር ዐብይ የዲሞክራሲ ነፃነት እንዲያድግ መፈለጋቸው እርግጥ ነው። ግን ይህ ዲሞክራሲ እንዲዳብርና ስኬታማ እንዲሆን ጠራጊ መንገድ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። እንዲሁ ልቅ የሆነና ስትራቴጂ የሌለው አካሄድ ዙሪያ ጥምጥም ይወስደናል እንጂ መልካም ቦታ አያደርሰንም። ለምሳሌ ፖለቲከኞች/አክቲቪስቶች ወሬያቸው እጅ እጅ ሳይል መላ ይፈጠር። እስቲ ለለውጥ ያህል ምሁራን ደግሞ ማስረጃ እየጠቀሱ እንዲያስተምሩ ድምፅ ማጉሊያውን ይያዙ። ምሁራን እውቀትን ተደግፈው ሲወያዩና ሲከራከሩ እንስማቸው። ብሄራዊ መድረክ ተሰጥቷቸው ኢትዮጵያን ያሳዩን። በየጎራው የሚሰማው ድምፅ፥ የፈጠራ ታሪክ ሆነ እውነተኛ ታሪክ፥ በሕዝብ ህሊና እንዲዳኝ ለሁላችንም ጆሮ የሚደርስ፥ አንድ ወጥ የውይይት መድረክ እጅግ ያግዛል። እውነት በእርግጥ አርነት ያወጣናል። በሌላ በኩል ደግሞ እውነት ብቻውን አይፈውሰንም። ለዚህም ይህ መርሀ ግብር ወደ ሦስተኛው መርሀ ግብር ይሻገር ዘንድ ያስፈልገዋል። 3ኛ ደረጃ መርሀ ግብር / የሀገር ሽማግሌዎች እርቅና ሰላምን እንዲያሰፍኑ ይጋብዙ። ዶ/ር ዐብይ የእርቅ ኮሚሽን ማቋቋማቸው እጅግ ቢደነቅም፥ መግለጫ ማውጣት ሳይሆን የሽምግልናውን ሥራ ዛሬ መስራት ያዋጣናል። በፓርላማ ከተቀመጡት የሕዝብ ተወካዮች ይልቅ፥ ኢትዮጵያ ዛሬ የሚያስፈልጋት በእርቅ ኮሚሽኑ ክንዋኔ ከየወረዳው የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጉባሄ ቢፈጠር ነው። በሃይማኖት አባቶች ብሔራዊ የፆምና ፀሎት ጥሪ ሕዝብ ልቡን ወደ ፈጣሪ ከመለሰ፥ የሀገሩን ችግርና መፍትሄ በምሁራን ትንታኔ ግንዛቤን ካገኘ በሁዋላ፥ ያኔ ሕዝብ ለእርቅ ሂደት ራሱን አዘጋጅቶ ይገኛል። ያኔ ሀገር በቀል የሆኑት ሕዝባዊ ሽማግሌዎች መፍትሄ ይሆናሉ። ለዚህ የእርቅ ሂደት ብሔራዊው መድረክ በሶስተኛ መርሃ ግብሩ ይህን አጀንዳ ያስኬደዋል ማለት ነው። ስለ ኢትዮጵያዊነት ፈውስ ፖለቲከኞች መፍትኤ አያመጡም። የኢትዮጵያዊነት መታመም መንስሄው ሕዝቡ አይደለም። ፖለቲከኛ ነን ባዮች እንጂ። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት እንዲፈወስና መካከለኛ ቦታ እንዲይዝ ከተፈለገ፥ ከፖለቲካው ትህይንት በፊት፥ ሕዝብ መሪነቱን ቦታ እንዲይዝ የሃይማኖት አባቶች፥ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ይቅደሙ። 4ኛ ደረጃ መርሀ ግብር / ፖለቲከኞች በዲሞክራሲ ምርጫ እንዲፎካከሩ ይጋብዙ። ከዚህ በፊት ይተጠቀሱትን ሶስቱን ሕዝባዊ መርሀ ግብሮችን ስናካሄድ፥ ጊዜው ይሄድና ወደዚህ አራተኛ ደረጃ ያደርሰናል። ያኔ ፖለቲከኞች ካረፉበት ቤት (ካስቻላቸውና ዝም ብለው ከተቀመጡልን) የየራሳቸውን ፕሮግራም ለማስተዋወቅና ለሕዝብ ምርጫ ራሳቸውን ለማቅረብ የሚፎካከሩበት ብሔራዊ መድረክ ይሆንላቸዋል። ለነዚህ አራት ውይይቶች ግብሃት እንዲሆን ብሔራዊ የመግባባት ሚዲያ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋል። ምክንያቱም ለዚህ ግብሃት የሚሠራው አንድ የመንግስት ሚዲያ ከመንግስት ቁጥጥር ስር ብቻ ሆኖ ማድረግ ፍትሀዊ አይሆንምና ነው። የተከበሩ ዶ/ር ዐብይ፥ ይሰማል? የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ! ኢሜል፥ [email protected] |